Wednesday, March 22, 2017

የኢትዮጵያ ድንበር ክፍት የሆነላቸው የሙርሊ ጎሳ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳን መንግስት ይረዳሉ።ግብጾች በደቡብ ሱዳን የሰውነት አካላት ገበያ ጀምረዋል።


   


የኢትዮጵያ ድንበር ክፍት የሆነላቸው የሙርሊ ጎሳ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳን መንግስት ይረዳሉ።ግብጾች በደቡብ ሱዳን የሰውነት አካላት ገበያ ጀምረዋል። Minilik Salsawi
መንግስት አልባ በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ ድንበሩ ክፍት የሆነላቸው ከደቡብ ሱዳን ተነስተው ወደ ጋምቤላ በመግባት ሕጻናትን በማፈን ነዋሪዎችን በመግደል ቤቶችን በማቃጠል ስራ ላይ የተሰማሩት የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ አባላት በደቡብ ሱዳን መንግስት በገፍ የሚረዱና የመሳሪያ ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ሳልቫ ኬር ግብጽን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ ወደ ሙርሊዎች አከባቢ ወታደራዊ ቡድን በመላክ እንዳጠናከሯቸው ታውቋል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከባባድ መሳሪያዎችን ከመታጠቃቸውም በላይ የወያኔ ሰራዊት ወደ ቦታው ቢገባ ሊመክቱ የሚችሉበትን ዝግጅት ማድረጋቸው ታውቋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ የግብጽ ሕገወጥ የሰውነት አካላት ኣዘዋዋሪዎች በደቡብ ሱዳን መንቀሳቀስ መጀመራቸው ታውቋል። በሲና በረሃ በርካታ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን የሰውነት አካሎቻቸው በማውጣት ከወያኔና ከሻእቢያ ባለስልጣናት ጋር ተመሳጥረው በሱዳንና በኤርትራ በረሃዎች እየገፉ ወደ ግብጽ በረሃዎች በመውሰጥ እየገደሉ የሰውነት አካሎችን የሚዘርፉ የተደራጁ ወንበዴዎች በደቡብ ሱዳን መክተማቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment