Wednesday, March 29, 2017

በአሜሪካ ኒውጀርሲ የአራት ወር ነብሰጡር የነበረችው ኢትዮጵያዊት ህይወቷ አልፎ ተገኘ


(አድማስ ራድዮ) ሜሮን ለማ የተባለች የ35 ዓመት ወጣትና የነርሲንግ ምሩቅ ባለፈው እሁድ ማርች 19 ቀን ፣ በምትኖርበት ኒውጀርሲ በሚገኝ አፓርመንት ውስጥ ህይወቷ አልፎ መገኘቱ ተነገረ። አሟሟቷን ፖሊስ እያጣራ ቢሆንም፣ ቤተሰብ በሰው ሳትገደል አልቀረችም የሚል ግምት እንዳለው ይነገራል።
ሜሮን የነርሲንግ ተማሪ እንደነበረችና ብቻቸውን እንዳሳደጓት የሚናገሩት የሜሮን እናት ከኒውጀርሲው ስቶከን ዩኒቨርሲቲ በህዝብ ጤና አጠባበቅ መመረቋንና ከዚያም በነርሲንግ ሙያ ፈቃድ አግኝታ መስራት መጀመሯን ገልጸዋል። አያይዘውም እሁድ አመሻሽ ላይ ፖሊስ ቤታቸውን አንኳክቶ ሜሮን ልጃቸው መሆኗን ካረጋገጠ በኋላ አፓርትመንቷ ውስጥ ሞታ እንደተገኘች እንደነገራቸው እናት ይገልጻሉ። ሜሮን የአራት ወር እርጉዝ እንደነበረች የቅርብ ቤተሰቦች ለአድማስ ሬዲዮ ገልጸዋል።
ፖሊስ እሁድ አስክሬኗን ሲያገኝ ህይወቷ ካለፈ ሁለት ቀን ሞልቶ ነበር። በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስክሬኗን ወደ አገር ቤት ለመላክና የአሟሟቷን ሚስጥር ለማወቅ ፖሊስ የሚያደርገውን ክትትል ለማገዝ የጎ ፈንድ ሚ አካውንት መክፈታቸውን ለአድማስ ሬዲዮ ገልጸዋል። የፍትሃት ጸሎት በመጪው ቅዳሜ ፣ በቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን Memorial service at St. Emmanuel Ethiopian Orthodox Church , 6825 Green way avenue, Philadelphia, Pennsylvania 19142 , starting 9:30am እንደሚደረግም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment