Monday, March 27, 2017

ጎንደር ላይ አምቡላንስ እየተሯሯጡ ነው – አስናቀው አበበ




በጎንደር ከፍተኛ ዉጥረት አለ። በጎንደር ዙሪያ ብዙ መረጃዎች ከሚያቀርቡ ጦማሪያን መካከል ጦማሪ አስናቀው አበበ
የሚከተለዉን ጦምሯል፡
=============================
ጎንደር ላይ አምቡላንስ እየተሯሯጡ ነው! ጥንቃቄ!
ወልቃይት ዳባትና ጎንደር ከተማ ውጥረት ነግሷል!
ደባርቅ ላይ ሰውን ሲያጉላሉት ሰንብተዋል!
መብራት አጥፍተውም የወታደራዊ መኪኖች እንቅስቃሴ መኖሩን አሁን የአይን እማኞች ከቦታው አድርሰውናል። መብራት አጥፍተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ችግር ሲፈጠር ለመሆኑ የታወቀ ነው።

በተያያዥም በወልቃይትና በዳባት አካባቢ እጅግ ውጥረት እንደነገሰ ለማወቅ ተችሏል።
ጎንደር ከተማ የተሰባሰቡ የህወሃት ወታደራዊ ባለስልጣና ጎንደር ከእጃችን እየወጣች ነው በማለት የአካባቢውን ተላላኪ ባለስልጣናት እያተረማመሷቸው መሆኑ ታውቋል።
“በየ አስራ አምስት ሜትሩ የፌዴራል ፖሊስ ይታየኛል። ሁሉም የታጠቁ ናቸው። ሌላው ዋናው ነገር ቀይ ቦኔት ያደረጉ ወታደሮች ከተማዋን አጥለቅልቀዋታል። መትረየስ እና ብሬን የጠመዱ ፖትሮሎች በዝተዋል። ፌደራሎቹ የጠረጠሩትን ሰው አቁመው ይፈትሻሉ፡፡ ውጥረቱ ከምገልፅልህ በላይ ነው” ሲል አንድ የጎንደር ነዋሪ ገልጿል።
~~~~~~~~
የነፃነት ጥያቄ በአፈና አይፈታም

No comments:

Post a Comment