Monday, March 27, 2017

ሳምራዊትና ግንቦት ሰባት – ዳዊት ሰለሞን

   


17499213_10212118302983581_1988321846773679308_nየአሁኑን አያድርገውና የሳምራዊት ፎቶግራፍ የጀግንነት ፣የእምቢ ባይነትና የፅናት ምልክት ነበር ።
የአዲስ አበባ መፅሔቶች ሳይቀሩ የሳምሪን ፎቶ በፊት ለፊት ገፆቻቸው እስከማውጣት ደርሰው ነበር ።የእርሷን ፎቶ መጠቀም በሽብርተኝነት ሊያስወነጅል ቢችልም መፅሔቶቹ በቆራጥነትዋ ተረትተው ህይወታቸውን ለአደጋ አሳልፈው እስከመስጠት ደርሰው ነበር ።
አሁን ሳምራዊትን በሚመለከት አዲስ ዘፈን ወጥቷል ።ፎቶግራፍዋ እንደቀድሞው በክብር የሚጠቀሙበት ዘመን ያከተመ መስሏል ።በነበራት ስያሜ ላይ ተደርቦ የነበረው አርበኚት የሚለው ተገፍፎ ሳምራዊት የወያኔ ሰላይ እየተባለች ነው ።
ግን እንደው መቼ ይሆን በሰዎች ህይወት መፍረድ የምናቆመውና ቢያንስ በፊት ላደረጉት (ለሞከሩት )ነገር ዋጋ የምንሰጠው ?
ሳምራዊት ኤርትራ የወረደችው እኛን ወክላ ወይም እኛ ተዋጊልን ብለናት አይደለም ።በቃ ከትግሉ መውጣት እንዳለባት የወሰነችው በራስዋ ድምዳሜ ነው ።ወደ ትግሉ ለመግባት እንደወሰነች ለመውጣትም ወሰነች ።አለቀ።
ቢያንስ ያመነችበትን ነገር ለመፈፀም ኤርትራ ወርዳ ያለፉትን አምስት ዓመታት አሳልፋለች ።ይህንን ለማድረግ ወኔውም አቅሙም ያልነበረን ሰዎች ደርሰን የይሁዳ ካባ ስንደርብላት አለማፈራችን ይሰቀጥጠኛል።
አሁንም ለግንቦት ሰባት የሚበጀው የልጅትዋን ስም በወያኔነት ጥላሸት በመቀባት ውለታ ቢስ መሆን ሳይሆን እጅ ለመስጠት ያበቃትን ነገር በአባላቱ መካከል በግልፅነት መወያየትና መፍትሔ መፈለግ ነው ።

No comments:

Post a Comment