Sunday, March 19, 2017

ድርድሩ እየከሸፈ ትጥቅ ትግሉ እየጠነከረ ነው #ግርማ_ካሳ

   


1734271
አገር የሚገነባው በድርድር ነው። ችግሮችን በድርድር መፍታት የስለጠነ ፖለቲካ ነው። ግን በአንድ እጭ አይጨበጨበም እንደሚባለው.አገዛዙ ድርድሩን የሚያከሽፈው ከሆነ ዜጎች መብታቸው ለማስከበር፣ ከቤታቸው ላለመፈናቀል፣ በግፍና በጭካኔ ላለመታሰር፣ ላለመደበደብ፣ ራሳቸውን ፣ ቤተሰባቸውን ከመንግስታዊ ወንበዴዎች ለመመከት፣ በአጭሩ ራሳቸው ለመከላከል ነፍጥ ማንሳታቸው አይቀርም። ያም ነው እየሆነ ያለው። ዜጎች ወደ ጫካ፣ ወደ ትጥጥ ትግል የመሄዳቸው ብቸኛ ምክንያት የአገዛዙ ግትርነት ነው። አራት ነጥብ።
ሕወሃት/ኢሕአዴግ በአገሪቷ ያለውን ችግር በሰላምና በዉይይት እንዳይፈታ አሁንም መሰናክሎችን እያስቀመጠ ነው። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ከተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን የገለጸው ገዢው ፓርቲ፣ ድርድር አመኔታ እንዲኖረው የሚረዱ ተግባራትን ከማድረግ ይልቅ እንደዉም በተዘዋዋሪ መንገድ ድርድሩ እንዲከሽፍ እየተንቀሳቀስ ነው ያለው። በአንድ በኩል እንወያይ እያለ በሌላ በኩል ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩን ማንገላታቱን አላቆመም።
ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው በደረሰኝ መረጃ ትንሽም ቢሆን የአገራችንን ፖለቲካ ወደ ተሻለ የሰላም አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል የተባለው ድርድር ፣ እየከሸፈ የመጣበት ሁኔታ ነው ያለው። ሕወሃቶች በኢሕአዴግ ውስጥ ባሉ፣ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ከዉስጥ ግፊት ሲያደርጉ የነበሩ፣ ለዉጥ ፈላጊ ሃይሎች ላይ (በተለይም ብአዴን ዉስጥ) ከፍተኛ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ከአንድ ሺህ በላይ የብአዴን አመራር አባላት ከሃላፊነታቸው ሕወሃቶች በሃይል ያነሱ ብዙ የብአዴን አባላትም እየታሰሩ ናቸው።
በዚህ መልኩ በሰላም ችግሮችን የመፍታት እድሉ እየደበዘዘ ሲመጣ በሌላ በኩል ግን የትጥቅ ትግሉ አድማሱን እያሰፋ የመጣበት ሁኔታ ነው ያለው። በአማራው ክልል በተለያዩ ቦታዎች በጎበዝ አለቆች የሚመሩ የትጥቅ ትግል እንቅቅሳሴዎች እየተደረጉ ሲሆን፣ ከጎበዝ አለቆች አንዱ የሆኑት የሰባ አንድ አመቱ አባት አቶ ጎቤው መልኬ በቅርብ ዘመድ በነበረ ግን በሕወእሃት በጥቅም በተገዛ ሰው መገደላቸው ይታወሳል። በአቶ ጎቤ ይመራ የነበረው ጦር ፣ አርበኛ ሻንቆ የሚባል አዲስ መሪ መርጦ መንቀሳቀሱን የቀጠለ ሲሆን፣ ይህ ጦር፣ በሰሜን ጎንደር ዞን መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም በሕወሃት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ባደረገው ዉጊያ 13 የሕወሃት ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን አንድ ደግሞ ከደረሰበት ቁስል የተነሳ ተማርኳል።
ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓም ጠዋት ደግሞ የአመጽ ትግሉ አድማሱን ከጎንደር ወደ ወሎ በማስፋት፣ የአማራ ተጋድሎ ጎበዝ አለቆች የደሴን ማረሚያ ቤት ሰብረው በመግባት በርካታ እስረኞችን ማስፈታታቸው ከስፋራው የደረሰ ዘገባ ይጠቁማል። በማረሚያ ቤቱ አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ እንደነበረ በስፋራው የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም ገልጸዋል።
በቀለኞች የሆኑት ሕወሃቶች፣ የእስረኞችን ማምለጥን የእስር ቤቱን መታሰር ተከትሎ፣ እነርሱን በታማንኘት ሲያገለግሉ የነበሩ የእስር ቤት የጥበቃ ሃይሎች ፣ “እገዛ አድርጋቹሃል” በሚል እንዳሰሯቸውም ለማወቅ ተችሏል። ይሄን የሚያመለክተው ሕወሃት በአማራው ክልል ነገሮችን የመቆጣጠር አቅሙ መሽመድመዱን ነው። የራሱ አባላትን መጠራጠርና ማሰር፣ በራሱ እግር ላይ መተኮስ ከጀመረ የአገዛዙ ፍጻሜ መጀመሩን የሚያሳይ ነው።
ብዙዎቻችን ለድርድሩ መሳካት ብዙ የጻፍነው፣ ግፊት ያደረግነው፣ አሁንም ግፊታችንን እና ተማጽኗችንን የምንቀጥለው፣ አገዛዙን ለመለማመጥ አይደለም። በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ከሚሞት ችግሮችን በዉይይት ቢፈቱ ምንጊዜም የተሻለ ነው ከሚል ነው። ሕወሃት የበሰበሰ አገዛዝ ነው። የሕወሃት የዘር ፖለቲካ ሕዝብ ከሕዝብ እያፋጨ ነው። የሕወሃት ኢኮኖሚ ጥቂቶችን ሚሊየነሮች ብዙሃኑን ድሃ ያደረገ ነው። የግፍ ጽዋዉ መልቶ ከመስፈሱ የተነሳ፣ ሕዝብ ጫፍ ላይ የደረሰበት ሁኔታ ነው ያለው። ከዚህ በኋላ በምንም ተአምር ሕወሃት መቀጠል አይችልም። መቀየሩ የማይቀር ነው። ግን የበሰበሰው ዛፋ ሲወድቅ አብሮ ብዙ ጥፋት እንዳያደርስ፣ በጥንቃቄ መሆን ስላለበት ነው፣ የስልጣን ወይም የስርዓት ሽግግሩ ሰላማዊ ይሆን ዘንድ፣ በዉይይት ነገሮች ይፈቱ ዘንድ የምንጽፈው።
አሁንም አገዛዙ 11ኛው ሰዓት ላይ እንዳለ ተረድቶ ለብሄራዊ መግባባት ራሱን በቅንነት እንዲያዘጋጅ በአስቸኳይ የታሰሩትን ሁሉ እንዲፈታና የሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲያከብር እጠይቃለሁ። አገዛዙ ይሄ ሙሉ ለሙሉ ሊከሽፍ ጫፍ የደረሰው ድርድር እንዳይከሽፍ ማድረግ አለበት። ያን ማድረግ ካልቻለ ግን፣ በተለይም በአማራው ክልል የሚወድቁ ታጣቂዎቹ የሚቀበሩበትን መቀበሪያ ስፋራ በስፋት ማዘጋጀት ይኖርበታል።
ባለኝ መረጃ በአማራው ክልል በጎንደር፣ በጎጃምና በወሎ በብዙ ቦታዎች በርካታ ሚስጥራዊ ወታደራዊ ካምፖች ያሉ ሲሆን፣ እጅግ በጣም ብዙ ታጣቂዎች እየሰለጠኑ ነው። ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ፣ በሻለቃ ደረጃ የነበሩም የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በጎበዝ አለቆች የሚመራዉን የአማራ ተጋድሎን እንቅስቃሴ የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ጎበዝ አለቆችንም የማያያዝ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ለጉዳይ ቀርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment