Monday, March 13, 2017

“የታላቁ የኦሮሞ ሕዝ ወገን ነኝ – የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የኩራት ልጅ ነኝ ” ደበላ ዲንሳ (ያሬድ ጥበቡ

   


debella-dinssa
ሌ/ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ “ሞቶ መኖር” በተሰኘው ግለታሪካቸው እንዲህ ይሉናል ።
” ነሐሴ 15 ቀን 1933 ዓም ከአባቴ ከአቶ ዲንሳ ወጌና ከእናቴ ከወ/ሮ ክትሌ አምበሊ በወለጋ ጠቅላይ ግዛት በጊምቢ አውራጃ፣ ሎያ ገፈሬ በሚባል የገበሬ መንደር [ተወለድኩ]… በብሔረሰብ በኩል ከታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ወገን ስሆን በልጅነቴም ሆነ በእምነቴ ደግሞ የታላቆች ታላቅ የመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ የኩራት ልጅ ነኝ ።
መወለድ ለማንም ሰው የተፈጥሮ ሕግ እንጂ በራስ ፍላጎት በምርጫ ካርድ አይወሰንም ። ከየትኛውም ብሔረሰብ መወለድ ለአገራዊና ህዝባዊ መብታችን የፍርሃትና የስጋት ምንጭ መሆን አይችልም ። ኦሮሞ ሆኜ ለመወለድ ያቀረብኩት የምርጫ ማመልከቻ አልነበረም።
…አባቴ ከወለጋ ጠቅላይ ግዛት ተነስቶ ጎጃም ድረስ በንግድ ሥራ ዘልቆ ገብቶአል ። ጎጃም ድረስ አሞሌ ጨው በማመላለስ ነግዶ በሦስት ጠገራ ብር መሬት መግዛቱን አጫውቶኛል ። …የአባይን ወንዝ ለመሻገር ከወገብ በላይ በመጫኛ ታስሮ ከሰማይ እየተሳበ በዋናተኞች ተደግፎ ይሻገር እንደነበር ሲነግረኝ ይገርመኝ ነበር ።
የጎጃም ህዝብ እንግዳ ተቀባይና ሃይማኖተኛ ነው ።ጎጃም ምግብ በነፃ የሚሰጥ ህዝብ ስለነበር ስንቅ ይዞ መጓዝ፣ የት እተኛለሁ ብሎ መተከዝ፣ አልነበረም ። ከአልጋው ወርዶ እንግዳ የሚያስተኛ ቸርና ደግ ህዝብ መሆኑን ሲነግረኝ አባቴ አውርቶ አይጠግብም ነበር ። የጎጃም ሰዎች እኔ ተወልጄ ባደኩበት ጊምቢ አውራጃ ሚስት አግብተው፣ ርስት ገዝተው፣ ልጅ አፍርተው የሚኖሩት በሠላምና በደስታ ነው ።”
ለኦሮሞ ፈርስት አንደኛ አመት ማስታወሻ የቀነጨብኩት ። የደበላ ቆሌ ይከተላችሁ ለማለት ።

No comments:

Post a Comment