አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩ እየተጣራ ነው
የአማራ ክልላዊ መንግስት 462 ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ አመራሮች ላይ የሙስና እና ተያያዥ ችግሮችን የተመለከቱ ጥቆማዎች ከህዝቡ ቀርቦለት እየመረመረ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በሌላ በኩል ብአዴን የቀድሞ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማባረሩንና የቀድሞ የአዊ ዞን አስተዳደር እና የወጣቶችና ስፖርት ኃላፊ የነበሩትን አቶ ባዘዘው ጫኔን ጨምሮ ለሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከባድ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የኮሙኒኬሽን ሃላፊው ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ የክልሉ መንግስት “በጥልቅ ተሃድሶው” የተለያዩ ችግሮችና ድክመቶች አሉባቸው ያላቸውን ከአንድ ሺህ በላይ አመራሮቹን ማባረሩም ታውቋል፡፡
የሰሞኑ የብአዴን ጉባኤ አወዛጋቢውን የወልቃይት ጉዳይ ተወያይቶበት እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ንጉሱ፤“የወልቃይት ጉዳይ የአማራ ክልል ዋነኛው ጉዳይ መሆን የለበትም፣ጥያቄው መቅረብ ያለበት ለትግራይ ክልል መንግስት ነው” የሚል ውሳኔ ቀደም ሲል መወሰኑን ጠቁመው፣ የትግራይ ክልል መንግስት ይሄን ተገንዝቦ፣ህዝቡን ማዕከል አድርጎ ምላሽ እንዲሰጥ ይጠበቃል፤ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ጉባኤው አልተወያየም ሲሉ መልሰዋል፡፡
No comments:
Post a Comment