Sunday, March 26, 2017

በወልቃይት አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት አለ




ከሙሉቀን ተስፋው
መጋቢት 17 ቀን 2009 ዓ.ም፤ በወልቃይት ከተማ ማምሻውን ከፍተኛ ሽብርና ውጥረት ተፈጥሯል፤ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ያወቅነው ነገር የለም ብለዋል የመረጃ ምንጮቻችን፡፡ ከፍተኛ የሆነ የትግራይ የፀጥታ አካላት ምሽቱን የገቡ ሲሆን ሕዝቡም በጊዜ ወደ ቤት እንዲገባ ተነግሮታል፡፡ የግል ሞተሮችን ማንቀሳቀስም ሆነ በእግር መሔድ ተከልክሏል እንደ እንደ መረጃውን እንደላኩልን ሰዎች፡፡
በመነግድ ላይ ከሥራ ሲመለስም ሆነ ወደየትኛውም አካባቢ ሲጓዝ የተገኘ ሰው መታወቂያውን ይቀማል ብለውናል፡፡ ከወልቃይት የገጠር አካባቢዎች ለሥልጠና የመጡ ምሊሻዎች የፀጥታ ችግር አለ ተብለው በአስቸኳይ ተበትነዋል፡፡

No comments:

Post a Comment