Saturday, March 25, 2017

በደሴ ማረሚያ ቤት 18 ሰዎች የተወሰዱበት ቦታ እንደማይታወቅ ተገለጸ

   


በደሴ ማረሚያ ቤት 18 ሰዎች የተወሰዱበት ቦታ እንደማይታወቅ ተገለጸ፤
Muluken Tesfaw
የደሴ ማረሚያ ቤት ምንጮች እንደገለጹት በመጋቢት 9 ቀን 2009 ዓም የወኅኒ ቤቱን መሰበር ምክንያት በማድረግ 18 በሕግ ጥላ ሥር የነበሩ ታራሚዎች የተወሰዱበት እንደማይታወቅ ተነገረ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች በሁለት ቡድን ተከፍለው እርስ በእርስ እየተካሰሱ ነው፡፡ አንደኛው ቡድን በኮማንደር ሙሉ የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በኮማንደር መኮነን የሚመራ ነው ብለውናል፡፡
መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ ሲሰበር አቶ ይማም መሐመድ የተባለ ታራሚ በጥይት የተገደለ ሲሆን በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በጥይት ተመተው ሕክምና ላይ ካሉት መካከል እነ ሰኢድ ሐሰን አስፈላጊው ሕክምናና ክትትል ተከልክለው ሕይወታቸው አስጊ እንደሆነ ነው የገለጹልን፡፡
በዕለቱ አምልጠዋል በተባሉት በእነ ሙሉጌታ ይመር፣ በላይ አገኘሁ፣ በፈቃዱ ክብረትና ሌሎችም ላይ ማደኛ ወጥቶ የአካባቢው ሕብረተሰብ ደብቋቸዋል በሚል እንግልት እየደረሰባቸው ነው ብለውናል፡፡

No comments:

Post a Comment