Monday, March 20, 2017

በአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አሳሳቢ ሆኗል

   


በአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አሳሳቢ ሆኗል፤ Muluken Tesfaw

• ከግማሽ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ የላቸውም
በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞን በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሠሩ አብዛኛዎቹ ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ እንደሌላቸው መረጃዎች አመለከቱ፡፡ ሀሰተኛ የትምህርት ዝግጅት ማስረጃ በማቅረብ የሚቀጠሩት አብዛኛዎቹ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች እንደሆነም የመረጃ ምንጫችን ገልጧል፡፡
አብዛኛዎቹ የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ቅጥር እንደ ነቀምትና ሻሸመኔ ባሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደሚፈጸም የጠቆሙት ምንጮቻችን በፎርጅድ የተሠሩ የትምህርት ማስረጃዎች ለቅጥር ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
ጉዳዩ ያሳሰበው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ 60 የሚሆኑ ከነቀምትና ከአሰላ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ተመርቀና ብለው ያስገቡትን መረጃ እንዲመረመር ለትምህርት ተቋማቱ ቢላክም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የትምህርት ማስረጃቸው ሊገኝ አልቻለም ተብሏል፡፡
የዐማራ ተወላጆች ኦሮምኛ አይችሉም እየተባሉ በዞኑ እንደማይቀጠሩ የገለጹት ምንጮች ቀደም ሲል በመምህርትነት የመጡ አሁን የዞኑን የካቢኔ በመቆጣጠር ለማንኛውም ቅጥር በኦሮሚያ አካባቢ እንደሚከናወን ነው የተነገረው፡፡

No comments:

Post a Comment