Friday, March 17, 2017

ለኤርትራዊያኑ መሰደድ ሰበቡ “ኢትዮጵያ ነች” – የማነ ገብረመስቀል

 

ከኤርትራ በየቀኑ ሁለት መቶ የሚሆን ሰው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሰደድና ከመካከላቸውም አምስት ከመቶ የሚሆኑት የሃገሪቱ ወታደሮች የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ እንደገለፁበት ዓይነት ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ለተሰማ መግለጫ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ሰጥተውት በነበረ ምላሽ ለኤርትራዊያኑ መውጣት ሰበቡ “ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል፡፡
“ኤርትራ ውስጥ የፖለቲካ ማሳደድ የለም” ያሉት የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሰዎች የሚወጡት ጨቋኝ መንግሥት ስላለ፣ ወይም በተሣሣቱ የምጣኔ-ኃብት ፖሊሲዎች፣ ወይም ለኑሮ የማይመች ሁኔታ በመኖሩ ሳይሆን “በጦርነትና ከኢትዮጵያ በሚመጣው የጦርነት ሥጋት ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡
በመሆኑም ለኢትዮጵያ ግዙፍ ድጋፍ ይሰጣሉ ያሏቸው የአውሮፓ መንግሥታት ጫናቸውን “ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሠጠን ለማድረግ ማሳደር አለባቸው፤ እንደ ሕዝብ፣ እንደሃገር በሰላም የመኖር መብት አለን” ብለው ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment