Thursday, March 30, 2017

በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም



በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም።
ዘለቄታነቱ ሳይረጋገጥ የተጨበጨበለት የኢኮኖሚ አብዮት ግቡን ለመምታቱ ምንም ማረጋገጫ የለም።በትግራይ በሕወሓት መሪነት የብረታ ብረት ፋብሪካ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ፋብሪካ፣ የሰፋፊ እርሻ ልማት ሥራዎችና ሌሎች ሲገነቡ ስራ ላይ ሲውሉ ነባር ፋብሪካዎች ሲከስሩ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በኦሮሚያና በኣማራ ሲያራግፉ ጥሬ እቃዎችን ሲበዘብዙ የኢኮኖሚ አብዮት አለመባሉ አሁን ላይ ለተከሰተው መደለያ ዘላቂነቱ ታማኝነት የለውም።
ባለፉት ሐያ አምስት አመታት የኢንዱስትሪና ኢኮኖሚ አብዮት ለኦሮሚያና አማራ ክልል ለምን አልታሰቡም ? የሕዝብን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረው የኢንዱስትሪና ኢኮኖሚ አብዮት ቀጣይነቱ ምን ድረስ ነው ? ባለፉት አመታቶች ሕወሓት ከፍተኛ ሐብቶችን ከኦሮሚያና አማራ ክልሎች ሲያሸሽ ኖሮ የውጪ ባለሐብቶችንና ራሱ የቀፈቀፋቸውን የወጥ ብሄር ሰዎችን ሰብስቦ ከፍተኛ ብዝበዛ ሲያካሂድ ኖሮ ድንገት ሕዝቡ ቢነሳ የፈጠረው አዲስ የኢኮኖሚ አብዮት ዜማ አነጋጋሪ ሆኗል።
በሃገሪቱ ብዙሃን ወደ ድህነት የተወረወሩበት ጥቂቶች በዘር ኔትወርክ የከበሩበት የሕዝብ ሓብትና ንብረት አሁንም ገና ከፓርቲ የንግድ ድርጅቶችና ከባለስልጣናቱ እጅ ያልወጣበት ደረጃ ላይ ሆኖ ስለ ኢኮኖሚ አብዮት ማሰብ ራስን ከለውጥ መስመር ላይ ማውጣት ነው።ስልጣን ላለማጣት የሕዝብ ተቃውሞ ለማዳከም የታቀደ ሴራ መሆኡ ሕወሓት በራሱ የፈጠረው ታክቲክ ነው። የኦሮሚያና የኣማራ የኢኮኖሚ አብዮት ጡዘት ተከትሎ ጥያቄ ያነሱት የሕወሓት የሚዲያ ድረገጾች እነትግራይ ኦንላየን የመሳሰሉት አስመሳይ ሚላሳቸውን ሲያሾሉ ቢነሱም የሌሎችን ክልሎች አድገት እንደማይፈልጉ ማሳየታቸው በራሱ የሕወሓትን ተንኮል ያጋለጠ ጉዳይ ነው።
አሁንም ቢሆን በቂ የሆነ ዝግጅት ያልተደረገበት ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ታስቦ የማያውቅ ለደባ የተወጠነ የኢኮኖሚ አብዮት ዘላቂነት የሌለው ባዶ ጩኽትና ኪሳራ ሲሆን በተዘዋዋሪ ለፖለቲካ ዱላ የሚውሉ መንደርደሪያዎችን የሚያመቻች የኢኮኖሚ ጅራፍ ነው። ሕዝቡ እንዳይታለል በንቃት ተከታትለን የሕወሓትን የማጭበርበሪያ ስልቶች ማክሸፍ ይጠበቅብናል። በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment