Wednesday, March 22, 2017

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይውት ሊቀጥፍ የሚችል ረሃብ ተሰግቷል




በሶማሊያ ሞቃድሾ ውስጥ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ሕፃናት በእናታቸው እቅፍ ውስጥ። ፎቶ ፋይል በየካቲት ወር የተነሳ
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሦስት የአፍሪ ሀገሮችና በየመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይውት ሊያጠፋ የሚችል ረሃብ ለመግባት የቀረው የአራት ወራት ጊዜ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
የስዊዘርላንድ የሰብዓዊ አገልግሎት በሶማልያ፣ በየመን፣ በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ሊደርስ የሚችል መቅሰፍትን ለማስወገድ ከተፈለገ ፈጣን ምላሽ ያሰፈልጋል ሲል አሳስቧል።የረድኤት አገልግሎቶች የእርዳታ ሥራቸውን እንዲያቀላጥፉ ጥሪ አድርገዋል። “ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም በነዚህ ሀገሮች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ከማለቃቸው በፊት የረደኤቱን ጥረት መደረግ አለበት” ሲሉ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የሥራ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስቲልሃርት አሳስበዋል።

No comments:

Post a Comment