Friday, March 10, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 በወገራ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ እስረኞችን አስለቀቀ | ሌሊቱን ለሰዓታት የፈጀ ውጊያ ተደርጎ ነበ




(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ጦር በወገራ ችንፋስዝ በገና ሲናሬ በተባለ ከተማ ውስጥ ድንገተኛ ውጊያ ከፍቶ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቁን የግምባሩ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::
ምንጮቹ እንንዳሉት ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት ድረስ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ወታደሮች መካከል በተደረገው ውጊያ ቁጥራቸው ያልተገለጸ የሕወሓት ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ ሆነዋል::
አርበኞች ግንቦት 7 እስረኞችን ካስለቀቀ በኋላ በርካቶቹ እንደተቀላቀሉት የተገለጸ ሲሆን በሕወሓት መራሹ መንግስት ሠራዊት ላይ ሌሊቱን ሙሉ ሲዋጋ አድሮ ወደ መጣበት መመለሱን የግምባሩ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታወቀዋል::
በድንገተኛው ጥቃት ኃይል ያጣው የሕወሓት ሠራዊት በአምስት ኦራል መኪና ወታደሮችን ጭኖ ወገራ ማስገባቱ ተሰምቷል::

No comments:

Post a Comment