

(ዘ-ሐበሻ) | የትውልድ ሃገሩን ኢትዮጵያ በብዙ ሺህ ማይል ርቀት ጥሎ በሰሜን አሜሪካ ቴነሲ ግዛት ኑሮውን ያደረገው የ41 ዓመቱ ጎልማሳ ጌትም ሽመልስ ደምሴ ሕይወቱን ለማሸነፍና ቤተሰቡን ለመርዳት አይቤክስ የተባለ ሬስቶራንት ከፍቶ ሲሰራ ነበር::
ቅዳሜ ለ እሁድ አጥቢያ ግጥም ሬስቶራንቱን እኩለ ሌሎት 12:00 አካባቢ እየዘጋ ባለበት ሰዓት; የዓይን ምስክር እንዳሉት “ጥቁር በጥቁር የለበሰና ማስክ ያጠለቀ ሰው ሬስቶራንቱ ውስጥ በመግባት ተኮሰበት:: ከአንድ ጊዜ በላይ እንደሆነ በተገመተ ተኩስ ሰውነቱ የተመታው ግጥም ሕይወቱ ማለፉን የናሽብል ቴነሲ ፖሊስ አስታውቋል::
እንደ አይን ምስክር ገለጻ የሬስቶራንቱ ባለቤት ላይ ተኩሶ የገደለው ሰው ቁመቱ 5 ጫማ በ7 ኢንች ይሆናል:: እንደዚሁም ቆዳው ጠየም ያለ እንደሆነ ተናግረዋል:: ጥቁር ጅንስ እና ጥቁር ረጅም እጅጌ ሙሉ ሸሚዝ ለብሷል::
ፖሊስ በምርመራ ላይ ያለ መሆኑን አስታውቋል:: እንዲሁም ጥቁማ መስጠት የሚፈልግ ካለም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል:: ጥቆማ መስጠት ለምትፈልጉ የስልክ ቁጥሩ 615-742-7463 ነው::
8
No comments:
Post a Comment