Friday, March 10, 2017

የህወሓት ተለጣፊው ብአዴን እና ህወሓት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ተሰማ፣- ሚኒልሊክ ሳልሳዊ

    March 9, 2017 23:47      




መላው የአማራ ህዝብ ባነሳቸው የማንነት ጥያቄወች ዙሪያ መላ ህዝቡ በውስጥም በውጭም እየተደራጀ በሚያካሂደው ተጋድሎ የተርበደበደው ህወሓት የብአዴንን አመራርና አባላት በጠላትነት ፈርጇል።
እርግጥ ነው እንደምንሰማው ብአዴን ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር የህወሓትን ረጅም እጅ ለመቁረጥ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንና ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄወች በመልካም ነገር እንደሚመለከቱት እየታወቀ መጥቷል። ህወሃት ይህንን የገጠመውን ተጨማሪ ፈተና ለማለፍ በህወሃት አገልጋይነታቸው የታወቁትን እነ በረከት፣ አዲሱ ለገሰ፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ከበደ ካሳና ደመቀ መኮነንን በዋነኛት በመያዝ ሰሞኑን የክልሉን ብአዴን አመራርና አባላት በስብሰባ ሲያምሱ ሰንብተዋል።በተካሄደው ስብሰባም ጸረ-ህወሓት አቋሞች በስፋት የተንጸባረቁ ሲሆን የወልቃይትና የራያ ጉዳይም በሸወርዋራው ተነስተዋል።የህወሃትን ተልዕኮ ለማስረጽ የመጣው ቅጥረኛ ጉጅሌም በመድረኩ ሙቀት በመደናገጥ የማባበልና የማሸማገል ስራ ላይ አተኩረው መሰንበታቸው ታውቋል።ስብሰባወቹ ሳይግባቡ ተግባብተው የተጠናቀቀ ቢሆንም ከስብሰባ በኋላ የወጡ የጹሁፍና የተሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫወች በህወሃት ጫና የቀረቡ እንጅ የብአዴንን የአባላትና የአመራር የስብሰባ ውጤት የተመለከቱ እንዳልሆነ ከውስጥ የሚወጡ መረጃወች አረጋግጠዋል።
ህወሃት በጸጥታ መዋቅሩም ማለትም በመከላከያ፣ በፖሊስና በደህንነቱም አካባቢ አስተማማኝ ያልሆነ ሁኔታ እንደተፈጠረበት ቅርብ የሆነ መረጃወች እያረጋገጡ ነው።እናም ህወሃት አጋሬና አሽከሬ የሚላቸው ድርጅቶች በምግባሩ በደንብ እየጠሉትና እየከዱት መሆናቸው ሲታወቅ የጸጥታ ሃይሉም ውስጥም እየተፈጠረ ያለ ትርምስ ተደማምሮ ለከፍተኛ ስጋት ተደርጓል።
በዚህ የህወሃት ቁስል ላይ የትምህርት ተቋሞች፣ በገጠርና በከተማ የሚኖረው ህዝብ አመጽ ሲደመርበት የነጻነታችን ቀን የመጀመሪያው መጨረሻ ላይ መሆናችን እንረዳለን።የሚጎለን ነገር ቢኖር!በአገር ቤት እየተካሄዱ ያሉ የማንነት ተጋድሎወችን በአግባቡ መደገፍና በተለይም የአማራ የፖለቲካ ሃይሎች ልዩነቶቻቸውን አጣበው ድክመቶቻቸውን አርመው በዋና ጠላታችን ላይ ማተኩር መቻል ነው።

No comments:

Post a Comment