ግርማ ሰይፉ ማሩ : ወዳጆቼ እንግዲህ ውይይቱ በተቀደው መስመር እየሄደ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ በአካሄዱ ላይ ከግምታችን ውጭ የሆነ ነገር የለም፡፡ ውይይቱ በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካካል ነው ሲባል ቆይቶ ኢህአዴግ ለበዓሉ ድምቀት በሚል የክልል ሀጋሮች ይግቡ፤ የሚል ሃሳብ ጫር ማድረጉን ሰምተናል፡፡ ለምን? ብለን ጠይቀን ማለፍ ይኖርብናል፡፡ የመድረኩ ፕሮፌሰር በየነ ቀደም ሲል አቅረበውት የነበረውን ሃሳብ (መሪ ተደራዳሪ መሆን አለብን የሚል ነው፡፡) አጥበቀው ለመሞገት ከሌሎቹም “ተቃዋሚ” ተብዬዎች ጋር እሰጥ አገባ ለመግጠም አልቦዘኑም፡፡ ከዚህ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፤ መድረኮች ሃሳቡን በመጀመሪያ ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ ከሌሎች አባላት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ያለማድረጋቸውን፤ እንደተለመደው ፕሮፌሰሩ አብዛኛውን ጊዚያቸውን በላቦራቶሪ ጥናት ላይ አሳልፈው ካቆሙበት ለመቀጠል ወደ ስብሰባ መምጣታቸውን የሚያሳብቅ ነው፡፡ በመድረክ ውስጥ ቢያንስ በጉልዕ የምናውቃቸው እነ ገብሩ አስራት ይህን ሃሳብ አምነውበት ከሆነ ፕሮፌሰሩን የላኳቸው፤ በግሌ ገብሩ አስራት ህወሓትን ረስቷል ብዬ መሳሳት ስለማልፈልግ፣ ፕሮፌሰሩን ባወጣው ያውጣው ብሎ ሊማግዳቸው ቆርጧል ብል ይቀለኛል፡፡ ከዚህ ውጭ መድረክ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ ሀሁ ገብቶት ፕሮፌሰሩን አይ የሚላቸው ስለማይኖር በቀጣዩ ዙር ስብሰባውን ረግጠው እንደሚወጡ ይጠበቃል፡፡
በእኔ እምነት ኢህአዴግ በሚያሳዝን ሁኔታ ውይይቱ በገለልተኛ አደራደሪ ይመራ የሚለውን የፈለገው አይመስልም፡፡ ምክንያቱም በውይይቱ ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን፤ በሰብሳቢ ወንበርነት መቀመጥ ብርቃቸው ስለሆነ ለዚህ ሲሉ ይህን እንደሚደግፉት ያውቃል፡፡ በድምፅ ብልጫ ከሆነ የኢህአዴግ ሃሳብ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ስብሰባውም አይረቤ መሆኑ ሰለሚረጋገጥ ይህን ጊዜ በቃኝ ማለት የጨዋ ስራ ይመስለኛል፡፡ የዚህ ስብሰባ ሌላው አስቸጋሪው ክፍል በስብሰባው የሚሳተፉት በዋነኝነት በኢህአዴግ እነ አቶ አስመላሽ፤ በተቃዋሚዎች ደግሞ እነ ፕሮፌሰር በየነ መሆናቸው ነው፡፡ በሁለቱም ወገን ሰጥቶ ለመቀበል ሳይሆን ለመቀማት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ እነዚህ ተደራዳሪዎች የባህሪ ለውጥ ባላመጡበት ሁኔታ የቀድሞ ጉዳይ እያሰላሰሉ ወደ አዲስ ውጤት መጓዝ አስቸጋሪ ነው፡፡ ኢህአዴግ የካቲት 30 በነበረው ስብሰባ ዘና ብሎ ተቃዋሚዎችን ሲያቧጭቅ ከዋለ በኋላ ከፈለጋችሁ በነጠላ (21 ችሁም) ፤ ከፈለጋችሁ ደግሞ በሃሳብ ተደራጅታችሁ በቡድን፤ ካልሆነ ደግሞ ሁላችሁም በአንድ ላይ ሆናችሁ ልገጥማችሁ ተዘጋጅቻለሁ ብሎ፤ በማላገጥ ውይይቱን አጠናቋል፡፡ አንድ ሆነው እንደማይቀርቡ ይታወቃል፡፡ በእኔ እምነት አሁን ባለው ተቃዋሚዎች ሶሰት ቡድን ከቻሉ በራሱ እጅግ መልካም ይሆናል፡፡ ለማነኛውም ውይይቱ መቀጠል የሚኖርበት ከሆነ ወሳኙ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ቆም ብለው ማሰብ ይኖርባቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ አሁን ከሚያሳየው ሁኔታ ቀርጠኛ እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡
ይህ ውይይት አንዳች ውጤት እንዲያመጣ ከታሰበ ከፍተኛ ሃላፊነት የሚሰጠው አደራዳሪ አካል እንዲቋቋም ማድረግ የግድ ነው፡፡ ይህን አካል ለማቋቋም ለኢህአዴግም ለተቃዋሚዎችም የጋራ የሆኑ ሰዎች በበቂ ሁኔታ ማግኘት አሰቸጋሪ ስለሆነ (እንደ አገር እዚህ ደረጃ መድረሳችን ያሳፍራል)፤ ከኢህአዴግ የሚመረጡ 2 ሰዎች፣ ከተቃዋሚ የሚመረጡ 2 ሰዎች እና አንድ በጋራ የሚመረጥ ሰብሳቢ መሰየም ያስፈልጋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የሚመርጧቸው ሰዎች የፖርቲ አባል ያልሆኑ፤ ይህች ሀገር የገባችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ የተረዱ እና ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉ፤ ሃሳቦችን ማመንጨት የሚችሉ ግለሰቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ አደራዳሪ አካል ሌሎች ተግባራትንም ለማከናወን ሃላፊነት የሚሰጠው ቢሆን ደግሞ ሁኔታውን የተሻለ ያደርገዋል፡፡ በዙር በሚደረግ የሰብሳቢነት ውይይት የፓርቲዎች ምክር ቤት የሚባለው ሲያደርግ እንደነበረው ቀልድ ለመቀለድ ብቻ የሚደረግ ነው፡፡

No comments:
Post a Comment