Monday, October 31, 2016

የዐማራ የጎበዝ አለቆች ሕብረት ተጋድሎ ወደ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያድግ ነው፤


የዐማራ የጎበዝ አለቆች ሕብረት ተጋድሎ ወደ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያድግ ነው፤
በተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች የወያኔ መንግሥት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉ በተበታተነ መልኩ በየአካባቢው ሲደረግ የነበረው ሕዝባዊ ተጋድሎ ድርጅታዊ መዋቅር የያዘ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊሆን ነው ብለዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ ሕብረት የመሠረቱት የሕዝባዊ ንቅናቄ ትግል በቅርብ ይፋ እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹ወሳኙ›› በመባል የሚታወቀው የጎበዝ አለቃ ‹‹ሕይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በአንድ ላይ መክረንበታል፡፡ በማንነታችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት የእኛን መስዋእትነት ይጠይቃል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ካሉ የጎበዝ አለቆች ጥምረት ጋር መክረንበታል›› ሲል ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. አረጋግጦልናል፡፡ ወሳኙ ያለበትን ቦታ ዕቅድም በድፍረት የተናገረ ቢሆንም ለጥንቃቄ ሲባል ቦታዎቹን ይፋ አለማድረግ መርጠናል፡፡ ‹‹ፈላሻው›› በመባል የሚታወቀው ሌላው የጎበዝ አለቃ ደግሞ ‹‹ወያኔ በዐማራው ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት ምንም ዓይነት መሻሻል አላሳየም፤ የማንነት ጥያቄ ያቀረቡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ኮሚቴዎችን ጥያቄያቸውን ከመፍታት ይልቅ እያሳደደ ማሳር ሥራየ ብሎ ይዞታል፡፡ የዐማራ ወጣት ለበለጠው ተጋድሎ መዘጋጀት አለበት፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣት እንደ አንድ መነሳት አለበት፡፡ ወጣቱ ዛሬ ወይም ነገ ለሚደረግ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ አለበት፡፡ ከሕዝባችን ላይ የተጣለውን ጭቆና ለመገርሰስ የእኛ መስዋትነት የግድ ብሏል›› ሲል አብራርቷል፡፡

የጎበዝ አለቆቹ በሰሜን ጎንደር የኮማድ ፖስት የሚባለው የወያኔ አገዛዝ የገበሬውን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ መፍጠሩንና በርካታ ወጣቶችን ማሰሩን አውስተዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሦእነሴ ጉንደወይን ከተማ የሁለት ወያኔዎች ንብረት የሆነ ዓለም ሆቴል የተባለን ለማቃጠል አስባችኋል በሚል ሳጅን ምናሉ የተባለ ቅጥረኛ የዐማራ ወጣችን ዛሬ ማሰሩን የጎበዝ አለቆቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ሳጅን ምናሉ እና ተመሳሳይ ወንጅል እየፈጸሙ ያሉ ቅጥረኞች ከዐማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአበባ እርሻ ባለንብረቶች ዐማራ የሆኑ የድርጅቱን ሠራቶች የሁለት ወር ደመወዝ ካለመክፈላቸውም በተጨማሪ ሠራተኞችን ያለ አግባብ ማንገላታታቸው በኋላ የእጃቸውን እንደሚያገኙም አሰጠንቅቀዋል፡፡ የአበባ እርሻ ጥበቃ ሠራተኞች በገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠ


በኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠ
ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ላሰቡ አሜሪካውያን ዜጎቿ ባለፈው ሳምንት ላወጣችው የጉዞ ማስጠንቀቂያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠውን ምላሽ ባለፈው ሰኞ ማቅረባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ማስጠንቀቂያው የወጣው የኢትዮጵያ ሁኔታ በተረጋጋበት ጊዜ መሆኑን ሲያመለክት በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለም ጠቅሷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ማክሰኞ በተለያዩ የዓለማችን ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ፣ የኢትዮጵያም ጉዳይ ተነስቶ ነበር። ማብራሪያውን የሰጡት፣ ቃል-አቀባዩ ጆን ከርቢ ናቸው። ዘገባውን አዲሱ አበበ ተከታትሎታል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡ 



ጆን ከርቢ /የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ/

ሕዝቦችን ያማከለ አንድነት ለትግሉ ስኬት – ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)


Image may contain: text
– ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ በጸረ – ኢትዮጵያ አቋም የሚዳክር በታታኝ ዘረኛ ቡድንና የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው። በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።
ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን። አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::
እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::
ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። 

በሊቦ ከምከም ወረዳ የተገደሉ የወያኔ ወታደሮች ብዛት ከ100 በላይ ሆኗል፤


በሊቦ ከምከም ወረዳ የተገደሉ የወያኔ ወታደሮች ብዛት ከ100 በላይ ሆኗል
በሊቦ ከምከም ወረዳ ሊቦ፣ ማርታዲዮስና አመኖ በሚባሉ ቀበሌዎች ያሉ ዐማሮችን ትጥቅ ለማስፈታትና በጎበዝ አለቆች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ኦፕሬሽኑን ሲመሩ የነበሩ የጎበዝ አለቆች አስታውቀዋል፡፡
በወረዳው አመኖ በሚባለው ቀበሌ አቶ አድነው መርሀግብር የተባለን የአካባቢ የጎበዝ አለቃ ለመየዝ ሙከራ ያደረገው የወያኔ ጦር ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል ተብሏል፡፡ አቶ አድነው በጀግንነት የከበቧቸውን ከዐሥር ያላነሱ ወታደሮች አብዛኛዎቹን ገድለው እንደተሰዉ ሰምተናል፡፡ በዚህ የተናደደው የወያኔ ጦር የአቶ አድነውን ሦስት ሙክቶች አርዶ መብላቱን የታወቀ ሲሆን በጎበዝ አለቆች እርብርብ አንድም ወታደር በሕይወት ሳይወጣ መቅረቱን ለማወቅ ችለናል፡፡
ሪፖርቱን እንዳቀረቡልን የጎበዝ አለቆች ከሆነ በአመኖ እና በሊቦ ቀበሌዎች ያልተነሱ የወያኔ ወታደሮች አስከሬን እስካሁን መኖሩን ነው፡፡ ከገበሬዎች በኩል ሁለት ሰዎች መሰዋታቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡ ተጨማሪ ሁለት ኦራል ጦር ወደ ሊቦ ቀበሌ መውጣቱንም አክለው ገልጸውልናል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በዓለፋና ጣቁሳ ወረዳዎች በተለይም በሻውራና የደልጊ ከተሞች ከ60 በላይ ወጣቶች ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. መታሰራቸው ታውቋል፡፡ የጎበዝ አለቆች በከተማ በመቀመጥ እጃቸውን አጣጥፈው ለወያኔ እስር የሚደረጉ ወጣቶች ወደ ማጥቃት እንቅስቃሴ መግባት እንዳለባቸው መክረዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል// 

የውጭ ሃገር ባንኮች በብድር ማቅረብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተገለጸ – ኢሳት


የውጭ ሃገር ባንኮች በብድር ማቅረብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተገለጸ – ኢሳት
ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማገዝ ወደ ሃገሪቱ የገቡ የውጭ ሃገር ባንኮች በብድር ማቅረብ ስራ ላይ መሰማራታቸውን ተገለጸ።
የደቡብ አፍሪካ፣ የቱርክ፣ የኬንያና፣ የአውሮፓ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማገዝ ይችሉ ዘንድ በቅርቡ በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ይታወሳል።
ስታንዳርድ የተሰኘ የደቡብ አፍሪካ ባንክ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እያካሄደ ያለውን ስራ ለመደገፍ የ100 ሚሊዮን ዶላር (ከ2 ቢሊዮን ብር) በላይ ብድር ማቅረቡን ይፋ እንዳደረገ አፍሪካ ቢዝነስ የተሰኘ መጽሄት ዘግቧል።
የአለም ባንክ በበኩሉ የሃገሪቱ አጠቃላይ የብድር መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረስ ከሃገሪቱ አጠቃላይ አመታዊ ምርት 55 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደያዘ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት አጋጥሞት ያለውን ይህንኑ የውጭ ብድር እዳ ለመቀነስ የፖሊሲ ማሻሻያ ዕርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወሳል።
ባለፈው አመት ብቻ ሃገሪቱ ወደ አራት ቢሊዮን የሚደርስ የብድር ስምምነትን የፈጸመች ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የብድር መጠንም ከ36 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን ለመረዳት ተችሏል።
የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ በባንክ ስራ እንዲሰማራ ፈቃድን ካገኘ በኋላ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለብድር ሲያቀርብ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አፍሪካ ቢዝነስ በዘገባ አስፍሯል።
ይሁንና ባንኩ ያቀረበው ብድር ምን ያህል ወለድ እንደሚከፈልበትና የመክፈያ ጊዜ መጠኑ ያልተገለጸ ሲሆን፣ ሌሎች የውጭ ሃገር ባንኮችም ለተለያዩ መንግስታዊ ፕሮጄክቶች ብድር እያቀረቡ መሆናቸው ታውቋል።
ይሁንና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ሃገሪቱ ከመጠን ያለፈ ዕዳ ውስጥ መግባቷ ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል አሳስበዋል።
መንግስት ለብድር የሚከፍለው የውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት የውጭ ምንዛሪ ክምችቱን ችግር ከማባባስ በተጨማሪ ለሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት አስተዋጽዖ ማድረጉን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፈው አመት ብቻ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር መውሰዱ ታውቋል።

የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣውጥቶ በኣፈናና በዘረፋ ላይ የተሰማራው የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የሚባለው መስሪያ ቤት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላቶችን በማፈ እና ሕዝብን በማስፈራራት በፍተሻ ስም ዘረፋ ላይ መሆኑን ሕዝቡ በምሬት ገለጸ።
በዚህም መሰረት ከሰማያዊ ፓርቲ የታፈኑት ወደ ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉ ሾን ከኣዋጁ በፊት መታፈናቸው ቢገለጽም ሰሚ ኣካል ባለመገኘቱ በእስር እየተንገላቱ እንደሆነ ታውቋል። ከትላንትና ጀምሮ በተጀመረው ኣፈና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ ሰሎሞን ስዩም ትናንት ምሽት በደህንነቶች ከመኖሪያ ታፍኖ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።እንዲሁም የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሃላፊ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የነበረው ወጣት ዳግማዊ ተሰማ በዛሬው እለት በድህንነት ሃይሎች ተይዞ ፮ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ኣፈናውን ኣጠናክሮ የቀጠለው ኮማንድ ፖስቱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን በክትትል ቀለበት ውስጥ ኣስገብቶ ለመያዝ መዘጋጀቱ ታውቋል። ከተመሰረተ ገና ኣንድ ሳምንት ሳይሞላ ከኣስራ ኣምስት ሺህ ዜጎች በላይ እስር ቤት እንደከተተ የሚነገርለት ኮማንድ ፖስቱ ስራው ማፈን\ማሰር ብቻ ሳይሆን ዘረፋም እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በሕዝቡ ላይ የገንዘብና የሞባይል የጌጣጌጥና የኤለክትሮኒክስ እቃዎችን በመዝረፍ ላይ እንደሚገኙ ሲታወቅ እነዚሁ የኮማንድ ፖስት ኣባላት በተሰጣቸው ስድ ስልጣን ነገ ሴቶችን ከመድፈር እንደማይመለሱ በመናገር ሕዝቡ ሮሮውን በማሰማት ላይ ይገኛል። #ምንሊክሳልሳዊ

ጀማሪ ዓቃቢያነ ሕግ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና በገቢዎች ባለሥልጣን ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ


‹‹ባለሥልጣኑ ያለ ሕጋዊ ውሳኔ በጅምላ የላከልንን የቅጥር ፎርም ማስተናገድ አንችልም›› ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌታቸው አምባዬ
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባወጣው የጀማሪ ዓቃቢያነ ሕግ የሥራ ቅጥር ተወዳድረውና የቅጥር ፎርም በመሙላት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ 54 ጀማሪ ዓቃቢያነ ሕግ፣ በቅርቡ የተቋቋመው ጠቅላይ

የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …


የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …
=========================================
* ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ ያማል 🙁
* መብት አስከባሪ ጠባቂ አልባ ዜጎች …
* ለስብዕና ቀናኢ እንሁን
ከቀናት በፊት እዚህ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የደረሰኝ መረጃ ምክንያት ሆኖ ውስጤን አሞኝ ሰንብቷል ። የሀገሬ ሰው ከለንደን የተሰማውን የኦነግ ቀባጣሪ ” ኢትዮጵያ ትፈራርስ ” ቱማታ ተከትሎ ሀገር ወዳዱ ወገን ከአድማስ አድማስ ታውኮ ከርሟል ። እኔም እንደቀረው ወገን በሆነው አዝኘ ” የኢትዮጵያ አትፈርስም ትፈርሳለች ” መረጃ ስመለከትና ስታዘብ ሰንብቻለሁ ። በኢትዮጵያ “አትፈርስም ትፈርሳለች ” መካከል መካከል ከንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ኃላፊዎች በኩል በአን ሀገር ወደድ ጥቆማ መሰረት ተጠርቸ ያየሁ፣ የሰማሁትና የተሰጠኝ መረጃ ሰቅጣጭ ነበር ።
በመንግስት እውቅና የኮንትራት ስራ ተብለው ከመጡት መካከል ያልታደሉት በውስጥ ደዌና በአዕምሮ ሁከት ተለክፈው ሲንገላቱ ህክምና በሚያገኙበት የህክምና ማዕከል ከ10 ያላነሱ በጠና ታመው ተኝተዋል ። ሶስት ያህሉ አስሰሚም አያዩም ፣ የቀሩት ከአልጋቸው መንቀሳቀስ አይችሉም ። የሀኪም ቤቱ ኃላፊዎች የመንግስታችሁ ተወካዮች ለህክምና የመጡ ዜጎቻቸውን ጉዳይ አይከታሉም የሚለውን ስሞታ በመረጃ ማስረጃ አቀረቡልኝ ። የተወሰኑትን በየአልጋቸው ሄጅ ስለመለከታቸው የተሰማኝን ሃዘን ብቻ ሳይሆን ባዶነት ነበር …ከቀናት በፊት በጠና ታሞ የጠየቅኩት ወንድም አልጋ በሌላ በሽተኛ ተይዟል ። ይህ ወንድም የት እንደሄደ ጠየቅኩ ፣ አሳዛኙ መርዶ ተነገረኝ 🙁 ወደ ማይቀረው አለም ማሸለቡን መረጃውን ከሚያቀብሉኝ አንዱ ሳውዲ ሀኪም ” እኒህ የምታያቸው እህቶች ዜጎቻችሁ ናቸው ፣ ከምንም በላይ ሰዎች ናቸው ፣ ቤተሰብ አላቸው ፣ ቤተሰቦቻቸው ይፈልጓቸዋልና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የመንግስታችሁ ተወካዮች ለምን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ እንዲንቀሳቀሱ አታደርጉም ? ” ብለው አፋጠጡኝ ። መልስ የለኝም 🙁
ጉብኝቴን ሳልከውን ሌላ መረጃ መዥረጥ አድርገው አወጡ ፣ በተለያየ ምክንያት ህይዎታቸው አልፎ በሬሳ ማስቀመጫ ለረዥም ጊዜ የተመጡ የዜጎቻችን ስም አጋሩኝ ። ውስጤ ታመመ 🙁 የማደርገው ባጣ ፣ ለመፍትሔው እጄ አጭር በመሆኑ አዝኘና አፍሬ ለመረጃው አመስግኘ የምችለውን እንደማደርግ ቃል ገብቸ ተለያየን!
በቀጥታ ያመራሁት ወደ ጅዳ ቆንስል መ/ቤት ነው ። የቆንስሉ ግቢ እንደቀድሞው በባለጉዳዮች አልተሞላም ። ቀዝቃዛ እንቅስቃሴውን እያስተዋልኩ ወደ ዲፕሎማቱ ቢሮ አመራሁ ። በቢሮው ኮሪደሮች አንዳንድ ባለ ባለጉዳዮች ፣ የቆንስሉ ቤተኞችና ሰራተኞች ይተላለፋሉ ። ከቤተኞች መካከል በቅርቡ አዲስ ቢሮ የተሰጣቸው የሴቶችን ሊቀ መንበር ተመለከትኳቸው ። ጉዳዬ በአልጋ ላይና በሬሳ ክፍል ውስጥ ስላሉት አብዛኛው እህቶች ጉዳይ ክትትል ማጣራት ቢሆንም በቀደመው የሻከረ ግንኙነት ባላንጣ ስላደረጉኝ እርሳቸውን መጠየቅ ከአንባጓሮ ባለፈ ፋይዳ እንደሌለው ስለተረዳሁ ልጠይቃቸው አልፈቅድኩም። እናም ወደ ሚመለከታቸው ዲፕሎማት ቢሮ አቀናሁ …
ዲፕሎማቱን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወንድም አገኘኋቸው ፣ ከሰላምታ በኋላ ውይይታችን ጀምርን ። በመጀመሪያ የጠየቅኳቸው በአሁኑ ሰአት በመጠለያው ከርማ ከወር በፊት ወደ ሀኪም ቤት እንድትገባ ስለተደረገው እህትና አሁን ያለችበትን ሁኔታ ማወቅ ስላለማወቃቸው ነበር ። ባለስልጣኑም ሆኑ ረዳታቸው በሆስፒታሉ ዘጠኝ ያህል ታማሚዎች በሆስፒታሉ ስለመኖራቸው መረጃ እንዳላቸው እምጅ የጠቀስኳት እህት ስለመኖሯ መረጃ የላቸውም ። ቀጥዬ ከሆስፒታሉ የተሰጠኝን መረጃ በተለይም ፖስፖርት ኮፒዋንና በቆንስሉ ለአሰሪዋ የተጻፈውን ደብዳቤ አሳየኋቸው ። መረጃው ትክክል መሆኑን ቢያረጋግጡኝም ዜጋዋ በሆስፒታሉ ስለመኖሯ በመዝገናቸው አለመስፈሩን አረጋገጥኩ ። ንዴቴ በፊቴ እየተነበበ ፣ ዝም አልኩ….
ከዚያ አከታትየ የጠየቅኳቸው ሞተው የቤተሰብ አድራሻና ማንነታቸው ባለመታወቁ አፈር መቅመስ ያልቻሉትዜጎች ጉዳይ ነበር ። ለዚህም ሲመልሱ ቤተሰብን ለማፈላለግ ማስታወቂያ እናወጣለን ቤተሰቦችን ማግኘት ከባድ ነው የሚል ምላሽ ሰጡኝ … ባለስልጣኑ ታመው የሚገቡትም ፣ የሚሞቱትም ሳውዲ ቤተሰብ አላቸው ብለው ያምናሉ ። እኔ ግን በዚህ አልስማማም ፣ ታመው ሲጨንቃቸው አምጥተው የጣሉ ሁሉ ቤተሰብ ላይሆኑ ስለሚችሉ ቢያንስ መርዶን ለቤተሰብ ለማርዳትና አፈር እንዲቀምሱ ለማድረግ አድራሻቸው ሀገር ቤት መፈለግ አለበት ባይ ነኝ ፣ ይህ ካልሆነ የፖስፖርት መምጣትን ከማየት ባለፈ ነዋሪው በማይጎበኘው በቆንስሉ ፊስ ቡክ ማስያወቂያ ለጥፎ ቤተሰብ ካላችሁ ሪፖርት አድርጉ ብሎ መናኛ ማስታወቂያ ማፈላለጉ ጠቀሜታው ብዙም እንደማይታየኝ አሳወቅኳቸው ። ደስተኛ አልሆኑም ፣ እኔ ግን ሀሳባቸው አልገባኝም !
በጫወታችን መካከል በጠና ታመው ካንቀላፉት መካከል ልክ የዛሬ ሁለት ሳምንት በአንበቱ ሀገር ቤት ስላሉ ቤተሰቦቹ ፣ ስለ ደጋፊ አልባ ልጆቹና ባለቤቱ አጫውቶኝ የነበረው ወጣት እስከ ወዲያኛው ማሸለቡን ስለተረዳሁት ወንድም መረጃ ጠየቅኩ ። ስለ ወጣቱ አትራፊ አጉዳይ ወጣት አባወራ መረጃው ያላቸው የጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች የዚህን ወንድም መርዶ ለቤተሰቦቹ አሳውቀው አፈር እንዲቀምስ የማድረጉን ሂደት አለመጀመራቸውን ግን ተረዳሁ 🙁
እኔ ሞቅ ባለ የያገባኛል ስሜት ፣ ባከስልጣኑ ” ለመፍትሔው ሁሉም ዜጋ መረባረብ አለበት ፣ መንግስት በጀት የለውም! ” በሚል ድፍን ምክንያት ውይይታችን ቀጠለ … እኛ እንደ ዜጋ መረጃ እናቀብላለን የሚቻለውን እናደርጋለን ፣ እናንተ ደግሞ አንድም እንደ ዜጋ ፣ ከፍ ሲል እንደ ከባድ የሀገር ኃላፊነት ፣ ከዚያም ወረድ ሲል ስለምትለፈሉበት ደመወዝ ስትሉ በማስተባበርና ለዜጎች መብት ልትቆሙ ይገባል ፣ ስል የሰጠኋቸው አስተያየት ዲፕሎማቱን ቱግ አደረጋቸው ! በውይይታን ብዙም አልቀጠለም ፣ ጥያቄ ለመጠየቅ ሳኮበኩም ያለወትሯቸው ያልተመቸኋቸው ዲፕሎማት ቆጣ ብለው ” አቶ ነቢዩ ጨረስን ይመስለኛል? ” አሉኝ … ጥቁት አተኩሬ አየኋቸውና መጨረሴን ገልጨላቸው እንደ ታመምኩ ቆዝሜ ከዚያ የሹሞች ቢሮ ወጣሁ … !
በሴቶች ስም ተመስርቶ ፖለቲካ የሚቆመርበትን የሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር ቢሮ በአሻጋሪ ፣ ሊቀ መንበሯን በኮሪደሪ ሲውረገረጉ አየኋቸውና ሀዘኔ ተጨማምሮ ከራሴ ጋር እያወጋሁ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ 🙁
በበሽታ ተቀስፈው ፣ ተስፋ ቆርጠው ጨንቆ ጨልሞባቸው አልጋ ላይ ተጋድመው ያየኋቸው ዜጎች ባይኔ ውልብ አሉ ፣ ሰው ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ እንዲሉ ማንነታቸው ሳይታወቅ ፣ ቤተሰብ መርዶ ሳይሰማ ወደ መቃብር ሊሸኙ የሚችሉትን ግፉአን እያሰብኩ በእኒህ የሆነው በእራሴ ቤተሰብ ቢሆንስ ? ብሎ የሚያስብ ጠፍቷል 🙁 ይህን ካየሁ ቀን ጀምሮ ለማትፈርሰው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች አልፈርስም ብሎ መጦመር ለእኔ የፊዝ ነበር !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 19 ቀን 2009 ዓም
Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.

የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። (ቆንጂት ስጦታው)


የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። (ቆንጂት ስጦታው)
የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ የሚሆነው፤ ነገሩ ያን ያህል ውስብስብ ጉዳይ ስለሆነ አይደለም። የዘኝነትን አባዜ በቀላሉ አሽቀንጥረን ለማስወገድ አልቻልንም አስገራሚ ነገር ነው። ጭራሽ፣ በዝምድና የሚገናኙ መሆን አለመሆናቸው የማይታወቁ ሰዎችን (የአንድ ብሔረሰብ ተወላጆችን) በጅምላ እንፈርጃለን። ይሄም አልበቃም። ጭራሽ፣ ከመቶ ዓመት በፊት፣ … ከአምስት መቶ ዓመት በፊት፣ ከሚሌኒዬም በፊት የነበረ ንጉስና አልጋ ወራሽ፣ ወይም ደጃዝማቾችና ፊታውራሪ፣ አልያም ሰባኪና ፀሃፊ፣ ሽፍታና ዘራፊ… እየጠቀስን፣ አሁን በሕይወት ያሉ ሰዎችን፣ የጥፋትና የበደል ወራሽ እንዲሆኑ በዘር እየፈርጅንና እያቧደንን፣ አገሩን ቀውጢ ስናደርግ ይታያችሁ? እብደቱ፣ በሽታውና ወረርሽኙ የዚህን ያህል ከፍቷል።
 
ኢትዮጵያ በብዙ አይነት የጥፋት ፈተናዎች ውስጥ፣ ህልውናዋን ሙሉ ለሙሉ ሳታጣ ያለፈች አገር ብትሆንም፣ የበርካታ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ዝንባሌን ስትታዘቡ፣ የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ከአመት አመት፣ የዘረኝነት ወረርሽኙ እየባሰበት፣ አገሪቱ ወደለየለት የጥፋት አዘቅት እንዳትሰምጥ አትሰጉም? በእርግጥ፣ አልፎ አልፎ፣ የዘረኝነት በሽታው፣ ለአፍታ ጋብ ሲልለት… እሳቱም ትንሽ ሲበርድለት እያየን፣ የእፎይታና የተስፋ ስሜት እናገኛለን። ግን፣ እፎይታው ብዙም አይቆይም።
 
እንደገና በሽታው ያገረሸበታል። ማገርሸት ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ እፎይታ በኋላ፣ ወረርሽኙ ባገረሸ ቁጥር፣ ከቀድሞው እጅጉን ብሶበት እናገኘዋለን። ተስፋ አስቆራጩና አስፈሪው ነገር ደግሞ ምን መሰላችሁ? የዘረኝነት ወረርሽኙን ለማስቆም የሚያስችል፣ አስተማማኝ መላ ምን እንደሆነ በግልፅ ጎልቶ አለመታየቱ ነው። ዙሪያው ሁሉ በጨለማ የተዋጠ ጉዞ ይመስላል። (ቆንጂት ስጦታው)

የኤርትራ አየር ኃይል አባላት የሚያበሩትን ጄት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ዜና ሃሰት መሆኑ ተረጋገጠ።


የኤርትራ አየር ኃይል አባላት የሚያበሩትን ጄት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ዜና ሃሰት መሆኑ ተረጋገጠ። konjit sitotaw
 
ሁለት የኤርትራ አየር ኃይል አባላት የሚያበሩትን ጄት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ በሚል አሶሲየትድ ፕሬስ ያወጣው እና ኑዮርክ ታይምስን ጨምሮ በትላልቅ የዜና አውታሮች የታተመው ዜና ሃሰት መሆኑ ተረጋገጠ። የዜና ወኪሉ ከስራ ተሰናብቷል።
 
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው አገልግሎት ሄኖክ ሰማግዜር ከ“ድህነነት ምንጮች” መረጃ አግኝቻለሁ ብሎ እንደዘገበትም ይታወሳል። ሆኖም የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እስካሁን የማስተካከያ ዜናም አልሰራም ፤ በተፈጠረውም ስህተት ይቅርታ የጠየቀ አይመስልም። በአሶሲየት ፕሬሱም በቪኦኤም የሃሰት ዘገባ ቅንብር የኢትዮጵያ መንግስት እጂ ያለበት ይመስላል።

ለስር ነቀል ለውጥ በሃገር ውስጥም በውጪም ተጠናክሮ ትግሉ ቀጥሏል።


ለስር ነቀል ለውጥ በሃገር ውስጥም በውጪም ተጠናክሮ ትግሉ ቀጥሏል።
– በኣማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡን የማስተባበር ሂደቶች በተሳካ መልኩ የቀጠለ ሲሆን በደቡብ ክልል እና በኣዲስ ኣበባ ጥሩ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ታውቋል፤ ሕዝቡ በራሱ ኣነሳሽነት ከኣብራኩ በወጡ ሃይሎች ለውጥ መፈለጉን በመተባበር እየገለጸ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።ኢትዮጵያ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋታል ሕዝቦች በእኩልነት በሃገራቸው ጠቃሚና ተጠቃሚ የሚሆኑበት መስመር መዘርጋት ያስፈልጋል የሚሉ ብዙሃን ሕዝቦች ኣደባባይ በመውጣት በኣራቱም የሃገሪቱ ማእዘናት ከመንግስት ጋር ከመጋፈጥ ኣልፈው በቤት ውስጥ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ማለት ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ሕዝብ ከስደት ይልቅ በሃገሩ ሰርቶና ተከብሮ መኖር ይፈልጋል የመንግስትን ኣመራር የያዘው ኣገዛዝ ኢትዮጵያውያንን የመኖር ሕለናቸውን ስለገፈፈ በየሰው ሃገር ለብሄራዊ ውርደት ተዳርገዋል። በዘር ላይ የተመረኮዘ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክፍፍል ኣንድን ዘር የበላይ እንዲሆን በማድረግ ሌሎችን የበይ ተመልካች ኣድርጎ ሃገርን ለድህነት ሕዝብን ለደሃ ደሃ ሰንሰለት ኣቀባብሎ ሰጥቷል።
በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል፥ በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ የእስር የግድያ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል፤ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል፥፥የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ
Image may contain: crowd, text, one or more people and outdoor

የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ፣የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል።


Image may contain: text
የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ፣የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል።

ኢትዮጵያውያን ላለፉት መቶዎች ፣ሺዎች ኣመታቶች ተፋቅረው ተከባብረው ተጋብተው ተዋልደው ለዛሬ ኣድርሰውናል። ዛሬ ላይ ሃገር ቤት ከሚገኘው ለነጻነቱና ለመብቱ ከሚታገለው ሕዝብ ይልቅ በመከፋፈል በዘረኝነት እና በትምክህት እየጦዘ ያለው ዲያስፖራው ነው። ይህ ዲያስፖራው የፈጠረው ኣጉል የበታችነት ስሜት የወለደው የጎሳ ፖለቲካ ክፍተት በመፍጠሩ ሕዝብ ነጻነቱንና መብቱን እንዳያስከብር እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ለወያኔ የእፎይታ ጊዜ ሆኗል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማሰብ የማይችሉ የኣጼዎቹ ስርዓት ናፋቂዎችም ሌላው ቤንዚሎች ናቸው።በዲያስፖራው ኣከባቢ የሚነዙ ጡዘቶች በሃገር ቤት ባለው ትግል ላይ ምናምን ይቸልሱበታል የሚለውን ፍራቻ ሰብረን ማለፍ በጣም ቀላል ነው። አንድነት – ፍቅር – ትእግስት – መከባበር – መደማመጥ – መተራረም
ደጋግመን የምንጮዀ ነገር ቢኖር በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተጨቆኑ ሕዝቦች ለውጥ ይፈልጋሉ፤ ለለውጥ የሚደረገው ትግል ፈር ያዘ እንበርታ በተባለበት በዚህ የሕዝብ ድል በሚበሰርበት ኣዲስ ምእራፍ ተከፍቶ የእኩልነት ኢትዮጵያ በምትመሰረትበት ወቅት እኩይ ኣንደበታቸውን ይዘር ሴራቸውን የሚያቀረሹ ጥቂቶች ሰፊውን ሚዲያ ተቆጣጥለው ለሕዝቦች ዳግም ባርነት ልብ ሰባሪ ፖለቲካ በመቀሸር ላይ መገኘታቸው የለመለመን ተስፋ ኣቀጭጮ የወያኔን ስልጣን ከማጥበቅ ኣይለይም።
በማግለል በፍረጃ እና በኣልሳካም ባይነት የሚናውዘው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖለቲካ በወያኔ ሃይሎች እጅ ሆኖ ሕዝብን እያመሰ ይገኛል፤ ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ሕዝባዊ ማኒፌስቶ የያዘ ኣጀንዳ ሲኖር ብቻ ነው። ሕዝባዊ ኣጀንዳ ባለለበት ብዙ ፖለቲከኞች እየተጋቡ ተፋተዋል ፖለቲካውን የቅፈላና የጭብጨባ ኣድርገውታል።እንዲሁም ከፖለቲካ የተገለሉ በሃገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ ስማቸው የሚጠፋ ኣካላት ከወያኔ ጋር በመተባበር የሚያሴሩት ተንኮል ትግሉ ወደ ኋላ እንዲጎተት ሲያደርገው ሕዝብ በፍራቻ እንዲርድ የፖለቲካ ውዥንብር እንዲፈጠር መንገድ ከፍቷል።
ለዚህ መፍትሄው ሁሉም ከትንሽ እስከ ትልቅ በሃገር ጉዳይ ስለሚያገባው በጋራ የተሳተፈበት ትልቅ ስራ በመስራት ትግሉን ወደ ድል ማሸጋገር ሲቻል ዋናው እና ሊተኮርበት የሚገባው ለውጥ ፈላጊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ እናወጣሃለን ያሉ ሁሉ በጋራ ሊቆሙ ይገባል። በመከፋፈል በማግለል በማዋሰድ በመሳደብ በማንቋሸሽ ማንም ምንም የሚያተርፈው ሃቅ የለም። ሕዝቡን ተባብረን ተረባርበን ልንደግፍ ይገባል። የነጻ ኣውጪ ነን የሚሉ የለውጥ ሃዋርያ ነን የሚሉ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ በመካከላቸው ያለው ግብግብ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ስራ ታላቅ ኣስታውጾ ያደርጋል። የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ቆሞ የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል። #ምንሊክሳልሳዊ

ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ


የተበታተነውን ትግል ለማሰባሰብ የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ \አህመን\ የሚባል ደርጅት አገር ቤት ተቋቋመ::የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)የጎበዝ አለቆች ያሉበት፣ የተለያዩ በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱት ለማሰባሰብ ፣ የአማራ ተጋድሎን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ የተቋቋመ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደር ደርጅት እንደሆነ ነው መግለጫው የሚጠቁመው።
ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ
ባለፉት ሥርዓቶች እንደብቸኛ ተጠቃሚ እየተደረገ የፈጠራና የውንጀላ ታሪክ ተሰጥቶን በጭቆና ስር የሚማቅቀው ወግናችን የአማራ ህዝብ መደራጀት የግድ የሆነበት ደረጃ ላይ የተደረሰው በአማራ ልሂቃን ጉትጎታ ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ከግፉ መብዛት፡ ከጭቆናው አሰቃቂነት የተነሣ በራሱ በአማራ ህዝብ የተፈጠረ ነው።
አብዛኞቹ የአማራ ልሂቃን ዛሬም ድረስ ወገናቸው “በመደራጀት ለራሴ ቀድሜ በመቆም ነው፡ ለኢትዮጵያ ልበጅ የምችል” ቢላቸውም ቅሉ አሁንም በአንድነት ስር ካሉ ሃይሎች ጋር በመሆን ዛው የህልም ሩጫ ውስጥ መዳከር ላይ ናቸው። ያውም ምንም አይነት የወሳኝነት ሚና በሌላቸው ድርጅቶች ውስጥ በመታቀፍ ጊዜያቸውንና ሃብታቸውን ይሰዋሉ።
ይህ አካሄድ የአማራን ህዝብ ሊጠቅም አይደለም፡ እንደውም ለጥቃት ያጋለጠ ከመሆኑ በላይ እነዚህ ሃይሎች የአማራን ህዝብ ትግልና ተጋድሎ በስሙ መጥራት፡ የሚደርስበትን በደል በይፋ መናገር ሁሉ የሚያሳፍራቸው መሆናቸው ደግሞ ጉዳዮ የበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።
በርካታ ወጣት የአዲሱ ትውልድ ልሂቃን ግን በሀቀኛ መረጃዎች የተደገፉ ጥፋቶችን በማሳየት ይህንን የአማራን የተጋድሎ ንቅናቄ ፈር ለማስያዝና ወደላቀ ድል ለማድረስ በየአቅጣጫው በመደራጀትና በማንቃት ላይ ናቸው። ከዚህ ደረጃ ትግሉን ያደረሰው ህዝባዊ ንቅናቄው እንጂ የቱም ድርጅት አለመሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንዳንድ የስም አንድነት ድርጅቶች የአማራን ተጋድሎ በስሙ ለመጥራት የሚያፍሩ ሆነው፡ በተጨማሪም በተረት ዓለም እንደሚኖር ምንዱብ ትግሉንና ድሉን በመድረኮቻቸው ሁሉ የራሳቸው በማድረግ ገቢ ማግኛ አድርገውታል፡ ይህም ድርብ ግፍ ነው። የሚደርስበትን ሰቆቃ በፀጥታ ከማለፍ ባሻገር የሚያደርገውን ተጋድሎ ባልዋሉበት ውለው መንጠቅ፡ ድርብ ግፍ ነው።
አሁን የሌሎችን በኛ የሚደረግ በደል የምናወራበትና የምናለቃቅስበት ጊዜ አይደለም። ዛሬ አማራ በጓዳው ያስለቅሱት የነበሩትን ሰቆቃዎች ሁሉ ባደባባይ ለመጋፈጥ ቆርጦና ጨክኖ የወጣበት ሰዓት ላይ ነን። የኛ ድርሻ መሰባሰብ፡ ዘመናዊ ስልትና ዕጣ ፈንታን መቀየስ፡ እንደአንድ ቤተሰብ መምከርና አንድ ልብ፡ አንድ ሃሳብ መሆን፡ ድሉን ከወንድምልቻችንና እህቶቻችን እኩል ለማጣጣም እንድንበቃ መቀናጀት፡ መደራጀት፡ በንድነት ትልቅና ማንም የማይቋቋመው ህጋዊ የአማራው ተወካይ ሆነን መገኘት ነው።
አማራ የሌለበት ትግል ሁሉ ፍሬ ክርስኪ መሆኑን ሌሎች ከኛ በላይ ይረዱታልና፡ የኛ መደራጀት የኢትዮጵያ ወሳኝ ዕጣ መሆኑን ተገንዝበን እስከጀነርነው ድረስ በጽናትና በሆደ ሰፊነት፡ በአማራ ባህል በሽምግልናና ዕርቅ ዳኝነት እየተስማማን፡ በጎበዝ አለቆች የሚመራውን በጠንካራ ባህላችን የተፈጠረውን ትግል፡ በዘመናዊ የፖለቲካ የትግል ስልት ደግፈን ፈጣን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ና ጠላቶቻችን የሚያዋርድ አንድነትና አደረጃጀት ለመፍጠር እንነሳ።
የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)

የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ


የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ  በመጪው ሳምንት ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀርባል
ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ የ22 ታራሚዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆንየወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቃጠሎውን በተመለከተ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀርባል ተብሏል፡፡
አደጋው የደረሰ ሰሞን በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን የተመለከቱት የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፤ የእሳቱን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጣርቶ የምርመራ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አባዲ፤ ምርመራውና ማጣራቱ ተጠናቆ ሪፖርቱ መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚቀርብ ገልፀዋል፡፡
በማረሚያ ቤቱ ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በወቅቱ 2 ታራሚዎች በጥይት፣ ቀሪዎቹ በቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሌላ በጎንደርና ደብረ ታቦር ወህኒ ቤቶችም በደረሰው የቃጠሎ አደጋ የታራሚዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም፡፡

በቀይ ሽብር ዘመን የኢሕአፓ የመረጃ ሰው ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ኣረፉ።


በቀይ ሽብር ዘመን የኢሕአፓ የመረጃ ሰው ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ  ኣረፉ። የወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ኣጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሞንጉስ ከ አባታቸው ከኣቶ ስዩም ሰሙንጉስ ተጫኔ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ኣቦነሽ በቀለ በኣዲስ ኣበባ ተረት ሰፈር በሃምሌ 23 ቀን 1949 ኣመተ ምህረት ተወለዱ፤ ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሲቢስቴ ነጋሲ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሽመልስ ሃብቴ ትምህርት ቤት ኣጠናቀዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ፒያሳ ከሚገኘው የኣተሻገመ የጽሕፈት ስራ ትምህርት ቤት የጽሕፈት ስራዎች ስልጠና በመውሰድ በሰርተፍኬት የተመረቁ ሲሆን እንዲሁም በኣዲስ ኣበባ የንግድ ስራ ኮሌጅ በጸሃፊነት ሙያ የሚሰጠውን ትምህርት በመከታተር በዲፕሎማ ተመርቀዋል በተጨማሪም በፍት ህ ሚኒስቴር ስር የተለያዩ የሕግ ትምህርቶችን በመከታተል እስከለተ ሞታቸው ድረስ በሕግ የማማከር እና በሕግ ኣገልግሎት ስራ ላይ ተሰማርተው ከ30 ኣመት በላይ ቆይተዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ በትግል ስማቸው በለጥሻቸው አምሐ በቀይ ሽብር ዘመን በተንቀሳቀሱበት ሁሉ የደርግ ገዳዮችን ኮቴ በመከተል ለኢሕኣፓ የመረጃ ስራ ሲሰሩ እንደነበር እና የበርካታ የሕዋስ ኣባላትን ሕይወት እንዳተረፉ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል ። ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ለተቸገሩ የነጻ የሕግ ኣገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በማህበራዊ መስክ ሕዝብን በነጻ በማገልገል ኖረዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሞንጉስ በደረሰባቸው ድንገተኛ ሕመም ያረፉ ሲሆን የቀብር ስነስርዓታቸው ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው የቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ባለትዳርና የኣምስት ልጆች እናት ነበሩ። ፈጣሪ ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን።

ወያኔ\ኢሕአዴግ ዛሬም ይቀልዳል። የኢሕአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የኢሕአዴግ መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡


ወያኔ ዛሬም ይቀልዳል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
Reporter : የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስፈጸም ሒደት በኮማንድ ፖስቱና በሌሎች የሕግ አስፈጻሚ አካላት ሊከሰት የሚችል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከታተልና ዕርምጃ ለማስወሰድ የተቋቋመው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ከአስፈጻሚው አካል የሚሞከር ተፅዕኖም አያሠጋኝም አለ፡፡
በማጣራት ሥራ ወቅት በኮማንድ ፖስት አማካይነት የማስፈጸም ሥራውን ከሚያከናውነው የመንግሥት አካል፣ መርማሪ ቦርዱ ነፃነትና ገለልተኝነት ላይ ተፅዕኖ  ሊያሳድር የሚችል ሥጋት ሊኖር አይችልም በማለት የቦርዱ አባላት ገልጸዋል፡፡
ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. የቦርዱን በይፋ ሥራ መጀመር ለማብሰር የቦርዱ ዋና ሰብሳቢና አባላት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ አዳራሽ  የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዕለቱም የቦርዱ አባላት በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሱ ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶችን ዋቢ በማድረግ፣ ቦርዱ ሊተገብራቸው የተዘጋጀበትን የትግበራ ዕቅድ በመዘርዘርም አስረድተዋል፡፡
በዕቅድ ትግበራው ወቅት በክትትልና በቁጥጥር ሥራዎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝና ከመብት ጥሰቶች ጋር ሊኖሩ የሚችሉ ክስተቶችን በግልጽ ለይቶ በማውጣት፣ ተጠሪ ለሆኑለት ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋ ገልጸዋል፡፡ ከምክር ቤቱ በተጨማሪ መርማሪ ቦርዱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠሪ መሆኑን ያስረዱት ሰብሳቢው፣ በኮማንድ ፖስቱ በኩል ሊከሰት የሚችል ኢሰብአዊ አያያዝን አጋልጦ የእርምት ዕርምጃ ማስወሰድ በሕገ መንግሥቱ ለቦርዱ የተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
ከቦርዱ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ ከአዋጁ ድንጋጌዎች መተላለፍ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦችን ዝርዝር፣ ማንነትና የታሰሩባቸውን ሥፍራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የሚለው ይገኝበታል፡፡
ሙሉ በሙሉ በኢሕአዴግና በአጋር ፓርቲዎች ከተወከለው ምክር ቤትም ሆነ ከፍትሕ ተቋማት የተሾሙ አባላት የተዋቀረው መርማሪ ቦርድ፣ በሥራ አስፈጻሚው በኩል ሊታይ የሚችል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን መርምሮ ለማጋለጥ ምን ያህል ገለልተኛና ተዓማኒነት ሊኖረው እንደሚችል፣ ነፃና ግልጽ የሆነ ሪፖርት ለማቅረብም ከአስፈጻሚው አካል ተፅዕኖ ሊያጋጥመው ይችል እንደሆነ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡
ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ቅድሚያውን የወሰዱት የቦርዱ ሰብሳቢ፣ ‹‹ቦርዱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አባላቱም ከምክር ቤቱ የተውጣጡ ናቸው፡፡ እነዚህ አባላት ቀድሞውንም የምክር ቤት አባል ያደረጋቸው የፓርቲው አባላትነታቸው መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ለፓርቲያቸው ፖሊሲና ስትራቴጂ ተገዥ ቢሆኑም፣ በአፈጻጸም ላይ በሚታዩ ችግሮች ልዩነት ለማሳየት አይከለክላቸውም፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
‹‹በአፈጻጸም በምናደርገው እንቅስቃሴ ተፅዕኖ ሊመጣ አይቻልም፡፡ ሥራችንን በነፃነት እንደምንሠራ ሊታወቅ ይገባል፤›› ሲሉም አቶ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የምክር ቤት ወኪል በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ ገነት ታደሰ በበኩላቸው፣ ‹‹የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ የቦርዱ አባላት የኢሕአዴግ አባል ስለሆንን ብቻ ለመንግሥት ጥብቅና አንቆምም፤›› በማለት ቦርዱ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ የገለልተኝነት ጥያቄ ሊነሳ እንደማይችል ጠቁመዋል፡፡
ከፍትሕ ዘርፍ ተወክለው የተሾሙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛው አቶ ክፍለጽዮን ማሞ በበኩላቸው፣ ‹‹ሥራችንን የምናከናውነው ኢሕአዴግን እያሰብን ሳይሆን ሕገ መንግሥቱን እያሰብን ነው፤›› በማለት በቦርዱ ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ እንደማያስነሳና በተፅዕኖ ሥር ሊወድቅ እንደማይችልም ገልጸዋል፡፡
ዋና መሥሪያ ቤቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከፍቶ ሥራ መጀመሩን ይፋ ያደረገው መርማሪ ቦርዱ፣ በቅርቡም ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በተለያዩ የክልል ከተሞች እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከኮማንድ ፖስቱ አፈጻጸም እንቅስቃሴ ጋር ተያይዘው እንደሚከፈቱ ያስታወቁት የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ፣ በሁሉም ሥፍራዎች የኮሚቴ አባላቱን በማሰማራት ቦርዱ የክትትልና የቁጥጥር ተግባር እንደሚያከናውን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በተለይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የሚገኙ ሪፖርቶችን ለምክር ቤቱ በማቅረብ፣ ዕርምት ያስፈልጋቸዋል ባላቸው ጉዳዮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በማቅረብ ዕርምጃ የማስወሰድ ሥራ እንደሚኖርም ገልጸዋል፡፡
ኅብረተሰቡም ከመብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ጥቆማ ካለው ቦርዱ በሩ ክፍት መሆኑንም አሳውቋል፡፡ ለማንኛውም የጥቆማ አገልግሎት ኅብረተሰቡ በስልክ ቁጥር 0111-544641 እና በፋክስ ቁጥር 0111-545926 መጠቀም እንደሚችልም ገልጿል፡፡

Sunday, October 30, 2016

የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …


የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …
=========================================
* ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ ያማል 🙁
* መብት አስከባሪ ጠባቂ አልባ ዜጎች …
* ለስብዕና ቀናኢ እንሁን
ከቀናት በፊት እዚህ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የደረሰኝ መረጃ ምክንያት ሆኖ ውስጤን አሞኝ ሰንብቷል ። የሀገሬ ሰው ከለንደን የተሰማውን የኦነግ ቀባጣሪ ” ኢትዮጵያ ትፈራርስ ” ቱማታ ተከትሎ ሀገር ወዳዱ ወገን ከአድማስ አድማስ ታውኮ ከርሟል ። እኔም እንደቀረው ወገን በሆነው አዝኘ ” የኢትዮጵያ አትፈርስም ትፈርሳለች ” መረጃ ስመለከትና ስታዘብ ሰንብቻለሁ ። በኢትዮጵያ “አትፈርስም ትፈርሳለች ” መካከል መካከል ከንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ኃላፊዎች በኩል በአን ሀገር ወደድ ጥቆማ መሰረት ተጠርቸ ያየሁ፣ የሰማሁትና የተሰጠኝ መረጃ ሰቅጣጭ ነበር ።
በመንግስት እውቅና የኮንትራት ስራ ተብለው ከመጡት መካከል ያልታደሉት በውስጥ ደዌና በአዕምሮ ሁከት ተለክፈው ሲንገላቱ ህክምና በሚያገኙበት የህክምና ማዕከል ከ10 ያላነሱ በጠና ታመው ተኝተዋል ። ሶስት ያህሉ አስሰሚም አያዩም ፣ የቀሩት ከአልጋቸው መንቀሳቀስ አይችሉም ። የሀኪም ቤቱ ኃላፊዎች የመንግስታችሁ ተወካዮች ለህክምና የመጡ ዜጎቻቸውን ጉዳይ አይከታሉም የሚለውን ስሞታ በመረጃ ማስረጃ አቀረቡልኝ ። የተወሰኑትን በየአልጋቸው ሄጅ ስለመለከታቸው የተሰማኝን ሃዘን ብቻ ሳይሆን ባዶነት ነበር …ከቀናት በፊት በጠና ታሞ የጠየቅኩት ወንድም አልጋ በሌላ በሽተኛ ተይዟል ። ይህ ወንድም የት እንደሄደ ጠየቅኩ ፣ አሳዛኙ መርዶ ተነገረኝ 🙁 ወደ ማይቀረው አለም ማሸለቡን መረጃውን ከሚያቀብሉኝ አንዱ ሳውዲ ሀኪም ” እኒህ የምታያቸው እህቶች ዜጎቻችሁ ናቸው ፣ ከምንም በላይ ሰዎች ናቸው ፣ ቤተሰብ አላቸው ፣ ቤተሰቦቻቸው ይፈልጓቸዋልና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የመንግስታችሁ ተወካዮች ለምን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ እንዲንቀሳቀሱ አታደርጉም ? ” ብለው አፋጠጡኝ ። መልስ የለኝም 🙁
ጉብኝቴን ሳልከውን ሌላ መረጃ መዥረጥ አድርገው አወጡ ፣ በተለያየ ምክንያት ህይዎታቸው አልፎ በሬሳ ማስቀመጫ ለረዥም ጊዜ የተመጡ የዜጎቻችን ስም አጋሩኝ ። ውስጤ ታመመ 🙁 የማደርገው ባጣ ፣ ለመፍትሔው እጄ አጭር በመሆኑ አዝኘና አፍሬ ለመረጃው አመስግኘ የምችለውን እንደማደርግ ቃል ገብቸ ተለያየን!
በቀጥታ ያመራሁት ወደ ጅዳ ቆንስል መ/ቤት ነው ። የቆንስሉ ግቢ እንደቀድሞው በባለጉዳዮች አልተሞላም ። ቀዝቃዛ እንቅስቃሴውን እያስተዋልኩ ወደ ዲፕሎማቱ ቢሮ አመራሁ ። በቢሮው ኮሪደሮች አንዳንድ ባለ ባለጉዳዮች ፣ የቆንስሉ ቤተኞችና ሰራተኞች ይተላለፋሉ ። ከቤተኞች መካከል በቅርቡ አዲስ ቢሮ የተሰጣቸው የሴቶችን ሊቀ መንበር ተመለከትኳቸው ። ጉዳዬ በአልጋ ላይና በሬሳ ክፍል ውስጥ ስላሉት አብዛኛው እህቶች ጉዳይ ክትትል ማጣራት ቢሆንም በቀደመው የሻከረ ግንኙነት ባላንጣ ስላደረጉኝ እርሳቸውን መጠየቅ ከአንባጓሮ ባለፈ ፋይዳ እንደሌለው ስለተረዳሁ ልጠይቃቸው አልፈቅድኩም። እናም ወደ ሚመለከታቸው ዲፕሎማት ቢሮ አቀናሁ …
ዲፕሎማቱን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወንድም አገኘኋቸው ፣ ከሰላምታ በኋላ ውይይታችን ጀምርን ። በመጀመሪያ የጠየቅኳቸው በአሁኑ ሰአት በመጠለያው ከርማ ከወር በፊት ወደ ሀኪም ቤት እንድትገባ ስለተደረገው እህትና አሁን ያለችበትን ሁኔታ ማወቅ ስላለማወቃቸው ነበር ። ባለስልጣኑም ሆኑ ረዳታቸው በሆስፒታሉ ዘጠኝ ያህል ታማሚዎች በሆስፒታሉ ስለመኖራቸው መረጃ እንዳላቸው እምጅ የጠቀስኳት እህት ስለመኖሯ መረጃ የላቸውም ። ቀጥዬ ከሆስፒታሉ የተሰጠኝን መረጃ በተለይም ፖስፖርት ኮፒዋንና በቆንስሉ ለአሰሪዋ የተጻፈውን ደብዳቤ አሳየኋቸው ። መረጃው ትክክል መሆኑን ቢያረጋግጡኝም ዜጋዋ በሆስፒታሉ ስለመኖሯ በመዝገናቸው አለመስፈሩን አረጋገጥኩ ። ንዴቴ በፊቴ እየተነበበ ፣ ዝም አልኩ….
ከዚያ አከታትየ የጠየቅኳቸው ሞተው የቤተሰብ አድራሻና ማንነታቸው ባለመታወቁ አፈር መቅመስ ያልቻሉትዜጎች ጉዳይ ነበር ። ለዚህም ሲመልሱ ቤተሰብን ለማፈላለግ ማስታወቂያ እናወጣለን ቤተሰቦችን ማግኘት ከባድ ነው የሚል ምላሽ ሰጡኝ … ባለስልጣኑ ታመው የሚገቡትም ፣ የሚሞቱትም ሳውዲ ቤተሰብ አላቸው ብለው ያምናሉ ። እኔ ግን በዚህ አልስማማም ፣ ታመው ሲጨንቃቸው አምጥተው የጣሉ ሁሉ ቤተሰብ ላይሆኑ ስለሚችሉ ቢያንስ መርዶን ለቤተሰብ ለማርዳትና አፈር እንዲቀምሱ ለማድረግ አድራሻቸው ሀገር ቤት መፈለግ አለበት ባይ ነኝ ፣ ይህ ካልሆነ የፖስፖርት መምጣትን ከማየት ባለፈ ነዋሪው በማይጎበኘው በቆንስሉ ፊስ ቡክ ማስያወቂያ ለጥፎ ቤተሰብ ካላችሁ ሪፖርት አድርጉ ብሎ መናኛ ማስታወቂያ ማፈላለጉ ጠቀሜታው ብዙም እንደማይታየኝ አሳወቅኳቸው ። ደስተኛ አልሆኑም ፣ እኔ ግን ሀሳባቸው አልገባኝም !
በጫወታችን መካከል በጠና ታመው ካንቀላፉት መካከል ልክ የዛሬ ሁለት ሳምንት በአንበቱ ሀገር ቤት ስላሉ ቤተሰቦቹ ፣ ስለ ደጋፊ አልባ ልጆቹና ባለቤቱ አጫውቶኝ የነበረው ወጣት እስከ ወዲያኛው ማሸለቡን ስለተረዳሁት ወንድም መረጃ ጠየቅኩ ። ስለ ወጣቱ አትራፊ አጉዳይ ወጣት አባወራ መረጃው ያላቸው የጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች የዚህን ወንድም መርዶ ለቤተሰቦቹ አሳውቀው አፈር እንዲቀምስ የማድረጉን ሂደት አለመጀመራቸውን ግን ተረዳሁ 🙁
እኔ ሞቅ ባለ የያገባኛል ስሜት ፣ ባከስልጣኑ ” ለመፍትሔው ሁሉም ዜጋ መረባረብ አለበት ፣ መንግስት በጀት የለውም! ” በሚል ድፍን ምክንያት ውይይታችን ቀጠለ … እኛ እንደ ዜጋ መረጃ እናቀብላለን የሚቻለውን እናደርጋለን ፣ እናንተ ደግሞ አንድም እንደ ዜጋ ፣ ከፍ ሲል እንደ ከባድ የሀገር ኃላፊነት ፣ ከዚያም ወረድ ሲል ስለምትለፈሉበት ደመወዝ ስትሉ በማስተባበርና ለዜጎች መብት ልትቆሙ ይገባል ፣ ስል የሰጠኋቸው አስተያየት ዲፕሎማቱን ቱግ አደረጋቸው ! በውይይታን ብዙም አልቀጠለም ፣ ጥያቄ ለመጠየቅ ሳኮበኩም ያለወትሯቸው ያልተመቸኋቸው ዲፕሎማት ቆጣ ብለው ” አቶ ነቢዩ ጨረስን ይመስለኛል? ” አሉኝ … ጥቁት አተኩሬ አየኋቸውና መጨረሴን ገልጨላቸው እንደ ታመምኩ ቆዝሜ ከዚያ የሹሞች ቢሮ ወጣሁ … !
በሴቶች ስም ተመስርቶ ፖለቲካ የሚቆመርበትን የሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር ቢሮ በአሻጋሪ ፣ ሊቀ መንበሯን በኮሪደሪ ሲውረገረጉ አየኋቸውና ሀዘኔ ተጨማምሮ ከራሴ ጋር እያወጋሁ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ 🙁
በበሽታ ተቀስፈው ፣ ተስፋ ቆርጠው ጨንቆ ጨልሞባቸው አልጋ ላይ ተጋድመው ያየኋቸው ዜጎች ባይኔ ውልብ አሉ ፣ ሰው ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ እንዲሉ ማንነታቸው ሳይታወቅ ፣ ቤተሰብ መርዶ ሳይሰማ ወደ መቃብር ሊሸኙ የሚችሉትን ግፉአን እያሰብኩ በእኒህ የሆነው በእራሴ ቤተሰብ ቢሆንስ ? ብሎ የሚያስብ ጠፍቷል 🙁 ይህን ካየሁ ቀን ጀምሮ ለማትፈርሰው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች አልፈርስም ብሎ መጦመር ለእኔ የፊዝ ነበር !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 19 ቀን 2009 ዓም
Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.

በአማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ወያኔ መርዛም ፕሮፓጋንዳውን እየረጨ ነው።


በአማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ወያኔ መርዛም ፕሮፓጋንዳውን እየረጨ ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በኣማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የሕወሓት ኣገዛዝ በውማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር በመሃል ሰርጎ ገብቶ ኣማራውን ለመፍጀት የሚያስችለውን እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት ያዩ የኣይን እማኞች ገልጸዋል።
የሕወሓት ካድሬዎች ኮሌኔል ደመቀ የአማራን ጦር እየመራ የቅማንትን ህዝብ ሊያስጨፈጭፍ የነበረ ጠላት እንደነበር ለቅማንቶች እየነገሩ ሃሰተኛ መርዝ በመርጨት ኣርሶ ኣደሩን እያታለሉ እደሚገኙ በቦታው ደርሰው መርዘኛ ፕሮፓጋንዳው የሰሙ ተናግረዋል።እማኞቹ እንዳሉት ተመሳሳይ ስራዎችንም በጎንደር ዙሪያ ባሉ የቅማንት ማህበረሰብ በብዛት ባሉባቸው ቀበሌወች እንዲሁም በቆላማ ስፍራወች ጭምር አርሶ አደሩን ታርጌት አድርገው ቅስቀሳቸውን አጧጡፈውታል። የሕዝቦች ኣንድነት የሚያስበረግገው ወያኔ የሚረጨውን ክፉና ከፋፋይ ኣደገኛ መርዝ ለማክሸፍ እያንዳንዱ የኣከባቢው ተወላጅ የበኩሉን ሚና መጫወት ኣለበት ሲሉ እማኞቹ ተናግረዋል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ተአምር ወይስ ቅዠት ? ኢትዮጵያ የድህነትና የረሃብ ማምረቻ


ተአምር ወይስ ቅዠት ? ኢትዮጵያ የድህነትና የረሃብ ማምረቻ
ለወራቶች የዘለቀው የሕዝብ ንቅናቄ እና ተቃውሞ ኢትዮጵያን የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ከቷታል። ኦክላንድ ኢንስትቲዩት ባወጣው ኣዲስ ሪፖርት መሰረት የኣፍሪካ አንበሳ የተባለችው ኢትዮጵያ ኣፈ ታሪክ መሆኑን ኣረጋግጧል። በኢትዮጵያ ረሃብና ድህነት ማምረት ተኣምር ወይም ቅዠት እንደሆነ ባለስልጣናቱ በልማት ስም ያወጡት እቅድ ኢትዮጵያን ለድህነት ለምግብ ዋስትና ማጣት ዜጎችን ለጥቃትና ለመገለል ኣሳልፎ የሰጠ መሆኑን በግልጽ ባለስልጣናቱን ኣጋልጧል።ምንሊክ ሳልሳዊ ዝርዝሩን ከሊንኩ ያገኙታል