

(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ትናንት በዜና እወጃዋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ቆሼ ሰፈር የአፈር ክምር ተደርምሶ ሰዎች መሞታቸውን መዘግቧ አይዘነጋም:: በዚህም መሠረት ጉዳዩን የተከታተልነው ሲሆን በአደጋው የሞቱት ወገኖቻችን ቁጥር 15 መድረሱ ተሰምቷል::
በኮልፌ ቀራኒዮ በተለምዶ ቆሼ በሚባለው ሰፈር በ አፈር ናዳ እስካሁን 17 ቤቶች መፍረሳቸው ሲረጋገጥ ቤት ተደርምሶባቸው የሞቱና የቆሰሉት ቁጥር ከደርዘን አልፏል::
እየተደረገ ባለው ቁፋሮ የ15 ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አስከሬን ፍለጋው እንደተጠናከረ ነው:: ከተደረመሰው አፈር ስር ከ30 ሰዎች በላይ ሕይወት መትረፉም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::
የአካባቢው ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ መሰረትም የሕዝብ እርዳታ እጅጉን የሚያስፈልግበት ወቅት አሁን ነው::
ጉዳዩን ተከታትለን እንዘግባለን::
No comments:
Post a Comment