Friday, March 31, 2017

ብሄራዊ ቁጭትን እንደ ህዝባዊ ድጋፍ የሚቆጥረው የህወሓት ቡድን በአባይ ግድብ @እንቅዩጳዝዩን 444

   


ብሄራዊ ቁጭትን እንደ ህዝባዊ ድጋፍ የሚቆጥረው የህወሓት ቡድን በአባይ ግድብ
@እንቅዩጳዝዩን 444
ይጠናቀቅበታል ከተባለበት 5 ዓመት አንድ አመት ጨምሮ ገና ከግማሽ በታች ያልተሰራው የአባይ ግድብ ለሆድ አደር ቱባ ባለስልጣናት ና መጠርቂያ የሌለው የአርቲስት ተብየከመንግስት ካድሬወች ከርስ ከፍ ከማድረግ ውጭ ከፍ ብሏል ሲሉት ግድቡ እራሱን ዝቅ እያደረገ እያየን ነው። በተለያየ መንገድ ሰራተኛው እስከ ተማሪው ፣ከነጋዴው እስከ ገበሬው ድረስ አዋጣ እየተባለ እየተገደደ ከደሞዙ በሚቆረጥበት ሁኔታ ተሰብስቧል የሚሉት ቢሊየን ብሮች በትክክለኛው ቦታ ሲወሉ አይስተዋሉም። ብሄራዊ ቁጭት ያንገበገበው የኢትዩጲያ ህዝብ ያዋጣው ገንዘብ የታል መለቱ አይቀርም። አፋን አውጥቶ እንዳይናገር የአምባገነኑ ወያኔ የበቀል በትር አፋን ብትለጉመውም ቅሉ በተለያየ ቦታና ጊዜ ቢያንስ ለራሱ አንድ ጥያቄን መጠየቁን አላቆመም።”ይጨረሳል የተባለው 5 ዓመት አለፈው ፤በየጊዜው በሰበብ አስባቡ የሚመነተፈው ብር የት ገባ ? ” እያለ ከቻለ ለጓደኛው ካልቻለ ለራሱ ሹክ ይለዋል። ይሄ ጉዳይ የራሱ የህወሓት ቡድን ሹመምንት ጥያቄ መሆኑ አልቀረም ፥የተበላ ነገር ይረሳልና። ይህችን ጥያቄ ለመጠየቅ የምትከፈትን አንደበት ለመዝጋት ያሰበ ይመስላል ከሰሞኑ የግድቡ አጠቃላይ ሃይል የማመንጨት አቅም ለ6 ዓመታት አካባቢ 6ሺ ኪሎ ዋት የነበረውን 450 ኪ.ዋት ጨምረው ሃይል የማመንጨት አቅሙ አድጓል 6450 ኪ.ዋት አድርገነዋል እያሉ ያሉት ።በተጨመረችው የቁጥር ጨዋታ ለመገንባት ደግሞ ያው ጊዜና ተጨማሪ የገንዘብ መጠን ያስፈልጋል በማለት ጨዋታውን የስልጣን ወንበር ጊዜ መግዣ ያደረጉት። መቼ ይሄ ብቻ?ህወሓት ብሄራዊ ህዝባዊ ና ሀገራዊ ቁጭትን ለህዝባዊ ድጋፍ ለመጠቀም ሌላም ነገር ይዞ መጥቷል።
ከሰሞኑ ወደ ግድቡ አካባቢ የሚሰማ አዲስ ፊልም እየተሰራ ይገኛል።ለጉልበት ስራ ወደ በረሃ የሚወርዱ ወገኖች በተዋናይነት ተመልምለዋል። የወረዳና የመንደር ተጠሪ ካድሬወች ለማስመሰያ ድግሱ ተፍ ተፍ እያሉ ነው ። ነገሩ እንዲህ ነው። የነፃነት ሃይሎችን ከህዝብ ለማራቅ ና የጥፋት ሃይል አድርጎ በህዝብ ላይ ለመሳል የሚደረግ ሙከራ ነው ። በጉልበት ስራ ላይ በአካባቢው የሚገኙና በየማጎሪያ ቤቱ ታስረው ከሚገኙ ወገኖችን መሳሪያ ታጥቀው ከግድቡ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ሲሉ ያዝኲቸው ብሎ በሚቆጣጠሩት ሚዲያ ለማቅረብ ያሰበ ነው። ለዚህም ከENN ፣ከፋና ፣ከዋልታ የቴሌቪዥን ጣቢያወች የተመረጡ ልማታዊ ጋዜጠኞች ተገኝተወል። በተለይ ዋልታ ቲቪ የስርጭት ጂማሮ በመጋቢት 24 መክፈቻ አብይ ጉዳይ ይሆናል ተብሎ እንደታሰበ ታውቋል። ከግልገል በለስ እስር ቤት ተመርጠው የተወሰዱ እንዳሉም ለማረጋገጥ ተችሏል። ከወደ ጉባ አዲስ ህዝብን ማታለያ መንገድና ህዝባዊ ድጋፍ ማግኛ መንገድ ይዞ ለመታየት የሚፍጨረጨረው የህወሓት ቡድን በነፃነት ሃይሎች በደፈጣ ውጊያና በእቅድ ዘመቻ አይቀጡ ቅጣት እየቀመሰ ይገኛል። በአካባቢው የሚገኙ የነፃነት ሃይሎች ግን “አባይን ግድብ የሚነካው እርሱ ጠላታችን ነው” ይላሉ። ጨምረውም የወያኔ አምባገነን ቡድን ህዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት የህዝቡን ብሄራዊ ቁጭት እየተጠቀመ በራሱ ሰወች በግድቡ ላይ ጥቃት ከፍቶ በነፃነት ሃይሎች እንደሚያሳብብ ከቀደመ ልምዱ እንረዳለን።ይሄን ማድረጉም አይቀርም ። በዚህም ነፃነት እንደውሃ የጠማው ህዝብ በንቃት እንዲከታተለው በአፅኖት ያሳስባሉ።



ቃላሚኖ አዳሪ ከፍተኛ ት/ቤት መቀሌ = የህወሃት የዘረኝነት ማስተማሪያ ተቋም!!!!

   
ቃላሚኖ አዳሪ ከፍተኛ ት/ቤት መቀሌ።
ከዛሪዎቹ ዘረኛ ህወሃቶች የባሱ ዘረኞች የሚፈለፈሉበት የህወሃት የዘረኝነት ማስተማሪያ ተቋም!!!!
በመቀሌው ቃላሚኖ አዳሪ ት/ቤት ከመላው ትግራይ ከ1-3 የወጡ ልዩ ተመሪዎች ተመርጠው በህወሃት ሙሉ ወጪ በልዩ አስተማሪ፣ሙሉ ኮምፒተራይዝድ የመማሪያ አቅርቦት ከ9-12 ደራጃ የሚማሩ ከ200በላይ ተማሪዎች መሰልጠኛ ቦታ ነው።

ተቃሙና የማስተማሪያው ካሪኩለም የተቀረጸው በራሱ በመለስ ዜናዊ ሲሆን ተማሪዎቹ በ3ዓመት ቆይታቸው የህወሃትን የበላይነትን ኢንዶክትሪኒሽን የሚሰለጥኑበት-የትግራይን ወርቃማ ሕዝብነት- የኢትዮጵያ ህልውና በዳግማዊ ምንሊክ አስገዳጅነት የተፈጠረች አገር መሆናን የሚሰለጥኑበት ጥንታዊው የአክሱም መንግስት የትግሬ መንግስት ሆኖ እራሱን የቻለ መሆኑን የሚማሩበት መርዘኛ ትምህርት ቤት ነው።

አንድ ኦራል ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን አሳፍሮ ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል።

   
አንድ ኦራል ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን አሳፍሮ ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ  በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል።
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት አንድ ኦራል ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን አሳፍሮ ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ ለምለም ተራራ ላይ ሲደርስ በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል። ምንጮች አሰቃቂ ሲሉ በጠሩት በዚህ አደጋ የአንድም ወታደር ህይወት ሊትርፍ አለመቻሉን ተናግረው፤ በከፍተኛ ሁኔታ የተቃጠሉና አካላቸው የተለያዩ ወታደሮች አስከሬን እየተለቀመ ተወስዷል። አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም። ወታደሮቹ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጋዮችን እንዲያድኑ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ነበር። ከዚሁ አካባቢ ዜና ሳንወጣ ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጋዮች በቋራ ወረዳ አስተዳደር ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተነሳ የእሳት አደጋ በአቅራቢያው የነበሩት ፍ/ቤት፣ የግብርና ጽ/ቤትና ሌሎችም መስሪያ ቤቶች ከወደሙ በሁዋላ ፣ አብዛኞቹ የወረዳው ባለስልጣናት ተይዘው ታስረዋል። ባለስልጣናቱ ከታጋዮች ጋር ግንኙነት ፈጥረው ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር ቢውልም ይህን የሚያሳይ መረጃ እስካሁን አልቀረበባቸውም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትንናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች የ3 ሚሊሺዎችን የጦር መሳሪያ ነጥቀው መውሰዳቸውን ተከትሎ፣ ታጋዮችን ለማደን የወጣ አንድ ሻምበል ጦር ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ ቀኑ 11 ሰአት አለመመለሱ ታውቋል። ወታደሮች በተያዘላቸው ሰአት አለመመለሳቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም፣ ወታደሮቹ ለምን እንዳልተመለሱ ኢሳት እስካሁን ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት አልቻለም። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጭልጋ ወረዳ ሻርዳ ቀበሌ፣ 17 አርሶአደሮች አንድ የነጻነት ታጋይን ካላስገባችሁ እርምጃ ይወሰድባችሁዋል በመባላቸው ጫካ ለመሰደድ ተገደዋል። ነፍሰጡሮች ሳይቀሩ ጫካ ለማደር መገደዳቸውን ታጋዩ ይናገራሉ።

ሙርሌዎች ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ሦስት ህጻናትን ይዘው ሄዱ



(ዘ-ሐበሻ) የሙርሌ ጎሳ አባላት ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ጋምቤላ በመግባት ጥቃት ፈጽመው በዚያውም ሦስት ህጻናትን ይዘው መሰወራቸው ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከስፍራው ባደረሱን መረጃ መሰረት ፒንዩዶ በተሰኘው የስደተኛ መጠለያ በመሄድ ነው እነዚሁ ሙርሌዎች ህጻናቱን ይዘው የሄዱት::
ከአስራምስት ቀን በፊት የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ባደረሱት ጥቃት 18 ሰዎች መግደላቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: እንዲሁም 22 ህጻናትን አፍነው መውሰዳቸው አይዘነጋም::
ከደቡብ ሱዳን ተነስተው የሚመጡት እነዚሁ የሙርሌ ታጣቂዎች በተመሳሳይ ባለፈው ፌብሩዋሪመጨረሻ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽመው 13 መግደላቸውን 20 ህጻናትን አፍነው መውሰዳቸውንም ይታወሳል::
መንግስት የለም ወይ?


 0  60  60

“ስለኦሮሞና ኦሮሞነት ማንሳት እንደወንጀል መታየት የለበትም” – የኦህዴድ ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ





(አዲሱ አረጋ ቂጤሳ)
27ኛዉ የኦህዴድ ምስረታ በዓል በአዳማ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፓናል ዉይይት ተከብሯል፡፡ በፓናል ዉይይቱ ወቅት በተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ምላሽና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
በፓናሉ ማጠቃለያ ፕረዝዳንቱ የደረጉትን ንግግር የተወሰነ ክፍል ዋና መልዕክት ተርጉሜ አቅርቤላችኋለሁ፡፡ መልካም ንባብ!
———–
“በዚህ ሥራ ውስጥ እስካለን ድረስ የህዝብ ተልዕኮ እስካለን ማየት ያለብንን ነገር ያለምንም መሰልቸት ቢያመንም ደጋግመን መነጋገር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጥያቄ የጠየቃችሁ ሰዎች ባነሳችሁት ጥያቁ ላይ ልዩነት የለኝም፡፡ 27 አመታት ቆይታችን፤ በዚህ 27 ዓመታት ውስጥ መድረስ የነበረባችሁ ቦታ ደርሳችኋል ወይ ብላችሁ የጠየቃችሁ በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ለውጦችን ይህ ድርጅት እያየ በመሄድ ላይ ነው ወይ ብላችሁ በጠየቃችሁት ላይ በነዚህ 27 ዓመታት ደጋግመን እየተነጋገርን ያለነው ይህ ድርጅት ብዙ ለውጦችን አምጥቷል፡፡ ይህ አይካድም፤ አይደበቅም ተጨባጭ በመሆኑ፡፡ እንደ ዕውነት በትኩረት ካየን ደግሞ 27 ዓመታት ብዙ ጊዜ ነው፡ መንግስት ሆኖ ሀገር በማስተዳደር 27 ዓመት አይደለም በ7 ዓመት ፣ በ7 ወር ብዙ ነገር ስለሚሰራ ነው፡፡”
———–
“27 ዓታት ወደኋላ ተመልሰን ዛሬ የደረስንበትን ደረጃ ስናይ በእውነት ከወሰድነው ጊዜ ጋር ስናነፃፅር መስራት ያለብንን ሥራ በእውነት ሰርተናል ወይ ብለን ብናይ፣ አልሰራንም፡፡መስራት ያለብንን ሥራ ሰርተን ብንገኝ ኖሮ ህዝቡ ለምን ያኮርፋል? ለምን ይነሳብናል? ለምን ይቆጣል ማመስገን ሲገባው? ስላልሰራን ነው ይህ አያጠያይቅም፡፡ የቤት ሥራችንን ስላልሰራን ነው፡፡ 27 ዓመት ብዙ ጊዜ ነው፡፡ እያየን እዚህ ውስጥ ነው የተወለድነው፣ ልጅነትና የወጣትነት ጊዜያችንን ጨርሰን እያየን አረጀን፡፡ ብዙ ጊዜ ነው እርግጥ ነው የሰራናቸውን ሥራዎች እንደብቅ ማለት አይደለም፣ ለራሳችን እማኝ ከመሆን ይልቅ ህዝቡ እማኝ ይሁንልን፡፡ እኛ የምንሰራው ሥራ ለህዝብ ነው፡፡ እማኛችን ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ደግሞ እንኳን ብዙ ሥራ ሰርተን ይቅርና በሰራነው ጥቂት ሥራ እማኝ ሊሆነን ችግር የለበትም፡፡
እኛ እንደ አንድ ፖለቲካ ድርጅት 4 ሚሊየን አባላት እንዳሉት ድርጅት እንደ 40፣ 50 ሚሊየን ህዝብ እና ሰፊ ክልል እንደሚያስተዳድር ድርጅት ራሳችንን ስናይ ከትላንቱ ጋር አፈፃፀማችንን ነው ማየት ያለብን፡ ዛሬ ላይ ሆነን ከደርግ፣ ከኃ/ስላሴ ሥርዓት ጋር ራችንን ማወዳደር አለብን ወይ; በዚህ ራሳችንን የምንገመግም ከሆነ ግምገማው ትክክል አይደለም፡፡ ደርግ 17 ዓመት ነው ያስተዳደረው እኛ 27 ዓመት ነው ያስተዳደርነው፡፡ ከዚህ ጋር በምንም መመዘኛ ልናወዳድር አይገባም፡፡ ጊዜዉም የተለያየ ነው፡፡ ብዙ ነገር ተቀይሯል፡፡”
———–
“ዛሬ ከ27 ዓመት በኃላ በምንም መመዘኛ ደርግ ይህን አድርጓል ኃ/ስላሴ ይህን አድርጓል እኛ ይሄን አድርገንልሃል ብለን የምንነግድበት ሸቀጥ በእጃችን የለም፡፡ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ህዝብ እንደሚያስተዳድር ድርጅት፤ ራሳችንን የምናይ ከሆነ እንደ ምሣሌ የሚታዩ ሀገሮች በ30 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለምሳሌ የኤዥያ አገሮችን ብንወስድ ዛሬ በአለም ላይ በዕድገት የሰማይ ጥግ የደረሱ አገሮች ታሪካቸው የ20፣ የ30፣ የ40 ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ ሌላ ታሪክ የላቸውም፡፡ በዚያ ነው ራሳችንን መመዘን ያለብን እንጂ ወደቄየ ተመልሰን ሞቶ አፈር ከለበሰው ጋር ራሳችንን ዝቅ አድርገን ማወዳደር፣ በዚያ ራሳችንን ማሞኘት ይሆናል፡፡ ከዚህ ተነስተን ስናይ መስራት ያለብን፤ መድረስ ያለብ ደርሰናል ወይ ብላችሁ የጠየቃችሁ አልደረስንም፡፡ አልደረስንም ሣይሆን ትንሽ ነገር ነው የሰራነው ብዙ ነገር ይቀረናል ብለን ራሳችንን መመዘን አለብን፡፡ ብዙ ነገር ይቀረናል፡፡ ለምንድነው እዝያ መድረስ ያቃታን መሮጥ፣ መሄድ ሲገባን ለምን አዘገምን ብዙ ችግር ስላለብን ነው፡፡ ያንን በተሃድሶአችን ደጋግመን ስላየን አልደግመውም፡፡ እንናገራለን እንጂ የምንናገረው ነገር በሽታው ያለበት ሥፍራ የሚያክ አይደለም፣ በሽታው ያለበትን ሥፍራ የሚያድን አልነበረም፡፡”
———–
“እርግጥ ነው ንግግራችን ትልቅ ነው፡፡ ከይቅርታ ጋር ምላሳችንን አርዝመን ብዙ ተናግረናል፡፡ የምላሳችንን ያህል እጃችን ሊደርስ አልቻለም፡፡ የችግሩን ሥፍራ አላየንም አልነካንም፣ አልወጋንም፤ እንጂ እራሳችንን ማየት ቀርቶብን አይደለም፡፡ እርስ በርስ መገማገም ተጨካክነን እርምጃም መውሰድ ቀርቶብን አይደለም፤ መውጋት ያለብንን ሥፍራ አልወጋንም፡፡ ለዚያ ነው ዛሬ ስራችን ጎዶሎ የሆነው፡፡ መንገድ ላይ የቀረነው ብዙዎቻችን ነን፡፡ ትላንት ያሰብነው ለህዝብ ተቆርቋሪነት አጥተን ረስተን መንገድ ላይ ጥለን ያለፍን አውላላ ሜዳ ላይ የቆምን ብዙዎቻችን ነን፡፡
አንዳንዱ የራሱን ጌታ ፈጥሮ የሚሰግድለት አለ፡፡ ጌታ መፍጠር ለምን ይመጣል? ለምን አስፈለገ? ለምን ተፈለገ? ለሰላም? የድርጅታችን መስመር ይህን ስለሚል? ህዝቡ ይሄን ስለሚፈልግ? አይደለም፡፡ በእርግጥ የድርጅታችን ችግር ነበር ወይ? የድርጅታን ችግር ነበር እውነት ነው፡፡ አንድ የሚያመን ሥፍራ እዚህ ጋር ነበር መደባበቅ ስለሌለብን ነው፡፡ ለምንድን ነው ተመልሰን የምንባላው? አንድ ህዝብ ነው ያለን፣ አንድ ሀገር ነው ያለን፣ አንድ አላማ ነው ያለን፡፡ ይህ ከሆነ ለምን እንከፋፈላለን? ለምን እንባላለን? ለምን ደባና ሸር አንደኛችን በሌላኛችን ላይ እንፈፅማለን?”
———–
“የህዝባችን ችግር ሳይሆን የግል ጥቅም ችግር ስላለ ነው፡፡ ከህዝብና ከሀገር ጥቅም የግል ጥቅም ስላለ ነው፡፡ ሌላ አይደለም ሌላ ፍች የለውም ራስን ማስቀደም ስላለ ነው:: የራስ ጌታ ሲፈጥር ደግሞ በሄደበት ሁሉ ጉልበቱ ይብረከረካል፡፡ ወንበር ላይ መቀመጥ እንፈልጋለን ወንበር ላይ መቀመጥ ለስም መሆን የለበትም፡፡ በተቀመጥንበት ወንበር ላይ ወንበሩ የሚፈልገውን ሥራ መስራት ካልቻልን ወንበሩ የሚፈልገውን ውሳኔ መስጠት ካልቻልን ለስም ወንበር ላይ መቀመጥ ዋጋ የለውም፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነት ችግሮች ስላሉብን ነው ከ27 ዓመት በኋላም መድረስ የሚገባን ሥፍራ ሳንደርስ ታግለን ለታገልንለት ህዝብ ጋር የተቃቃርነው ለዚህ ነው፡፡ ለዚህ ነው የተጨካከነው ሌላ አይደለም፡፡
አሁንም ህዝቡ የመጨረሻ እድል ሰጥቶናል በእውነት ሁሉ ነገር ድኗል ሁሉ ነገር ምላሽ አግኝቷል ሁሉ ነገር አልቆለታል ብለን የምናስብ ከሆነ ሞኝነት ነው፡፡ ራሳችንን ማሞኘት የለብንም ሀገር ሰላም ነው አዎ ሀገር ሰላም ነው፡፡ ግን ሰላም አይደለም፡፡ አጭር ዕድል ነው የሰጠን እንጂ ህዝቡ ሰላም አይደለም፣ እድል ሰጥቶናል የመጨረሻ ዕድል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚሰሩ እንይ ብሎ እድል ሰጥቶናል፡፡ ይህን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በደንብ ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡”
———–
“እንደ ድርጅት፣እንደ መንግስት እያንዳንዳችን ከገባንበት ጓዳ ውስጥ አንገታችንን ይዞ አውጥቶ የፈለገውን ነገር ሊፈጽምብን እንደሚችል እንዲህ አይነት እርምጃ ሊወስድብን እንሚችል አይተናል፡፡በፊልም ሣይሆን በተጨባጭ ውስጥ ኖረን አይተናል ይሄ ቲያትር አይደለም፡፡ ጎበዝ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ ወዲያና ወዲህ የምናይ ሰዎች ካለን ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ የእኛ ጌታ ህዝባችን ነው፡፡ ለየክልላችን ህዝብ ነው፡፡ ሌላ ጌታ የለንም፡፡ ለሌላ ጌታ መስገድ የለብንም፡፡ ትልቅ ድርጅት አለን 4 ሚሊየን አባላት አሉን፡፡ አራት ሚሊየን ማለት በጣም ትልቅ ነው፡፡ በአለም ላይ አራት ሚሊዬን አባላት ያሉት ድርጅት ውስን ነው፡ እንደነ ቻይና ያሉት ካልሆነ በስተቀር ውስን ነው፡፡ በቁጥር አይደለም እንዲሁ በስም ብንናገር 50 ሚሊየን ህዝብ ነው እኮ ያለን፡፡ ይህን ይዘን ለምን እግራችን ብርክርክ እንደሚል ለምን እንደምንፈራ ለምን ወደ ጓዳ ተመልሰን አንገታችንን ደፍተን እንደምናጉረመርም አይገባኝም፡፡”
———–
“አሁን ያለን ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ደጋግመን ስንል እንደነበረው ማዳመጥ ያብን ማየት ያለብን ይሄንን ህዝብ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ ሌላ አራማራጭ የለውም፡፡ እንደ ሥራው ክብደትና ድካም እያንዳንዱ ተቀብሎ ይሞክር ብለን አስረክበን ብንወጣም ደስ ይለን ነበር፡ ዛሬ እንደዚህ አይነት ምርጫ አለን? እስቲ ይቅርብን ሌሎችም ይሞክሩት፡፡ ሰባት አመት ሣይሆን 27 ዓመት የለፋንበት ስለሆነ፡፡ አንዳዶችን እንዲያውም ሰውነታችን የዛለ በመሆኑ ፡፡ ሌላው እስኪ ይየው ብለን እንደዚህ መቀባበል ቢቻል እንላለን፡፡ በዚህ መልኩ የተዘጋጀ ነገር ቢኖር ደስ ባለን ነበር፡፡ እውን በዚህ ደረጃ ይህ አለ ወይ ብለን ብንጠይቅ የለም፡፡ ራሳችንን ማታለል የለብንም፡፡ እኛም ደግሞ መሆን ያለብንን ሳንሆን ቀርተን እየተዉረገረግን በመሄድ፣እንዲሁ አስመስለን በመጓዝ ብቻ ረጅም መንገድ መሄድ እንችላለን ወይ ብለን ብንጠይቅ አንችልም፡፡መስቀለኛ መንገድ ላይ ነዉ ያለነዉ፣ራሳችንን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ልናጠፋ ስለምንችል፡፡ ሀገርንም ልናፈርስ እንችላለን፡፡ ሀገር እንደ ድንገት ሲፈርስ ደግሞ አይተናል ሩቅ ሳንሄድ ከጎረቤት ሀገር፡፡ በዕቅድ የሚፈርስ ሀገር የለም፡፡ ስለዚህ ያለን ምርጫ ቆም ብለን አሁንም ደጋግመን ስንል እንደነበረው ጥርሣችንን ነክሰን ከዚህ ህዝብ ጋር ሆነን ለህዝቡ መሥራት ነው ሊያዋጣን የሚችለዉ፡፡ ”
———–
“ከዚህ በኋላ ትግሉ እጅግ መራር ነዉ፡፡ እኛ ታጋዮች ማወቅ ያለብን ምንድነዉ መራር የሚያደርገዉ የሚለዉ ነዉ፡፡ አንደኛ የተሰጠችን ጊዜ አጭር ናት፡፡ ሁለተኛ እኛ እንዳሻን ስንሠራ ዝም ብሎ ተኝቶ የሚያየንና የሚሰማን ህዝብ አይደለም ያለው፡፡ ህዝብ ማለት እኛ የምንቀመጥበት ዝምብሎ እንዲሁ ተሸክሞን የሚውልና የሚያድርንበር ሣይሆን ከሥር እሳት ያለው የሚፋጅ ወንበር ነው፡፡ እዚህ ወንበር ላይ ውለን ማደር የምንችለው ከሠራን ብቻ ነው፡፡ ካለበለዚያ በቁማችን ያቃጥለናል፡፡ ምንም አማራጭ የለንም፤ ስለሆነም ከእንግዲህ ወዲያ የምናደርገው ትግል መራርና ከባድ ነው ለዚያ ደግሞ ራስን አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ዝም ብለን መሥመር ውስጥ ገብተን ስለቆምንና ስለተጓዝን የሚያዋጣን አይመስለኝም፡፡ መራር ስለሆነ፡፡”
———–
“ሌላው ሊታይና መገንዘብ የሚያስፈለገው እዚህ ሀገር ላይ የፌደራሊዝምን ሥርዓት ከመሠረቱት ውስጥ እኛ ትልቅ ድርሻ አለን፡፡ አንዳንዴ የፌደራሊዝም ሥራዓቱ ይቅርና በሀገር ምስረታ ያለንን ድርሻ ዘንግተን የሠራናቸውን ሥራዎች የምንተውበት ጊዜ አለ፡፡ ይህቺ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንድትፈጠር ይሄ ህዝብ (ኦሮሞ) ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ይሄንን የፌደራል ሥረዓት በመፍጠር ረገድም ሚና አለውው፤ በፌደሬሽኑ ውስጥ የሚገባንን ለማግኘት መታገል ማለትም ይሄው ነው፡፡ሥርዓቱን መፍጠር ብቻም ሳይሆን የፈጠርነው ሥርጭት ለህዝባችን የሚጠቅም፣ የሚበጅ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይሄንን ስንል በዚህ ፌደራሊዝም ሥርዓት ውስጥ ምንም አይነት ችግር አይገጥመንም ሁሉንም ነገር ቤታችን ውስጥ ተቀምጠን ይመጣልናል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ስህተት ነው፡፡ የጥቅም ግጭቶች ይኖራሉ፡፡ ይህም በፌደሬሽን ውስጥ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ለጥቅማችን ታግለን ተከራክረን የዚህን ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅና ማስከበር አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይሄን ማለት ሌላ ነገር መሆን ማለት አይደለም፡፡
———–
አንዳንዶቻችን እየተሳሳትን ያለነዉ እንዲያዉም እያሽቆለቆልን ማንነታችንን እየዘነጋን መጥተን ዬት እንደደረስን ታውቃላችሁ? ስለ ኦሮሞና ኦሮሞነት ማንሳት እንደ ወንጀል መታየት ጀምሯል እኮ፡፡ እንደ ጥፋት እንደ አውሬ እንደ ሌላ ነገር መወሰድና መታየት ጀምሯል፡፡ እኛ ለዚህ አይደለም የታገልነው፡፡ ምንግዜም ቢሆን በየትኛውም መድረክ ላይ ፊትለፊት ወጥተን መናገር ተገቢ ነው፤ ይገባናል፡፡ እኛ ካልተናገርን ማን ይናገርልናል? እኛ የዚህ ህዝብ ተወካይ ነን ካልን እኛ ካልተናገርንለት ማነው የሚናገርለት? ትግል ይሄ ነው? አንዳንዴ ችግር ያልሆነ ነገር እንደችግር የተወሰደ ይመስለኛል፡፡ ደግ ሴት ከወንድሟ ታረግዛለች እንደሚባለው አይነት ነገር ለመፍጠር እየተጓዝን ያለ ይመስለኛል፡፡ We don’t have to be shy! ለዚህ ህዝብ መብት ቆመን መታገል አለብን ካልን መታገል መቻል አለብን፡፡
ደጋግመን ተናግረናል መታገል ምንድነው ትርጉሙ? የህዝቡን ኑሮ መለወጥ ነው፡፡ ሌላ ነገር የለውም፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር ወዘተ አለ፡፡ የግል ባለሀብቶቻችንን ዘንግተናቸዋል፡፡ መቼ ወደ እኛ መጥተው ያውቃሉ? መች አቅርበናቸዉ፣አደራጅተናቸዉ እናውቃለን? በክልላችን የኢኮኖሚና የልማት ሥራ ራሳቸዉንመ ጠቅመው ሀገራቸውንም እንዲጠቅሙ፣ እንዲለዉጡ አድርገን እናውቃለን? እንደዚህ አይነት ዕቅድስ አለን? ብዙ ነገር ግን እናወራለን፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ሠርተን በተጨባጭ ካለን መሬት ላይ የት አለ? ስለዚህ ባለሀብቶቻችንን የግል ጥቅማቸውን ብቻ ሣይን ሀገርንም መጥቀም አለብን በሚል ዕምነት ከዝህ በኋላ በልማት ሥራዎቻችን ውስጥ አሣትፉን መሥራት አለብን፡፡ ያ ሲሆን ነው ኢኮኖሚ የሚቀየረው፡፡
———–
እኛ በዕውቀታችን ሁሉ ነገር አሟልተን አይደለም ሀገር እየመራን ያለነው፡፡ በዕውቀት መታገዝ እና መረዳት አለብን፡፡ በአዲስ ሐሳብና በአዲስ ጥናት መደገፍ አለብን፡፡ በየጊዜዉ እየተቀያየረ በሚሄድ አለም ውስጥ እኛ ራሳችን መለወጥ የሚያቅተን ለምንድነው? ቶሎ ከዚያ ጋር ተላምደን እየተቀያየረ የሚሄደውን ሁኔታ ተረድተን መሥራት የሚያቅተን ለምንነው? በምሁራኖቻችን ስላልተደገፍን ነው፡፡ የእኛ ምሁራን፣ አዋቂዎችና ሐሳብ አፍላቂዎች ሊያግዙን ይገባል፡፡ ለእኛ ብለው ሳይሆን የዜግነት ግዴታ ስላለባቸው፡፡ ለዚያ ደግሞ እኛ በራችን ክፍት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ እነሱን ጋብዘን ድርሻቸውን ሊወጡ የሚችሉበትን መድረክ፣ ሊረዱንና አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉበትን አጋጣሚ መፍጠር መቻል አለብን፡፡ ይሁንና እነሱም ማዶ ተቀምጠው እኛን መውቀስ ብቻ ሳይሆን ማዶ ተቀምጠው ጉድለቶቻችንን ቆጥረው እኛን ማውገዝ ሳይሆን እኔስ ምን ሰራሁ ብለው ራሳቸውን ጠይቀው እኛን መደገፍና መርዳት አለባቸው፡፡
——
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ 27ኛ የምስረታ በዓልን በማስመልከት በተዘጋጀ የፓናል ዉይይት ያደረጉትን ንግግር እና ቀጣይ አቅጣጫዎች  በሶስት ክፍሎች  አቅረቤላችሁ ነበር፡፡ የንግግራቸዉ ክፍልየመጨረሻዉ ክፍል  እነሆ!
“እኛ በዕውቀታችን ሁሉ ነገር አሟልተን አይደለም ሀገር እየመራን ያለነው፡፡ በዕውቀት መታገዝ እና  መረዳት አለብን፡፡ በአዲስ ሐሳብና በአዲስ ጥናት መደገፍ አለብን፡፡ በየጊዜዉ እየተቀያየረ በሚሄድ አለም ውስጥ እኛ ራሳችን መለወጥ የሚያቅተን ለምንድነው? ቶሎ ከዚያ ጋር ተላምደን እየተቀያየረ የሚሄደውን ሁኔታ ተረድተን መሥራት የሚያቅተን ለምንነው? በምሁራኖቻችን ስላልተደገፍን ነው፡፡ የእኛ ምሁራን፣ አዋቂዎችና ሐሳብ አፍላቂዎች ሊያግዙን ይገባል፡፡ ለእኛ ብለው ሳይሆን የዜግነት ግዴታ ስላለባቸው፡፡ ለዚያ ደግሞ እኛ በራችን ክፍት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ እነሱን ጋብዘን ድርሻቸውን ሊወጡ የሚችሉበትን መድረክ፣ ሊረዱንና አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉበትን አጋጣሚ መፍጠር መቻል አለብን፡፡ ይሁንና እነሱም ማዶ ተቀምጠው እኛን መውቀስ ብቻ ሳይሆን ማዶ ተቀምጠው ጉድለቶቻችንን ቆጥረው እኛን ማውገዝ ሳይሆን እኔስ ምን ሰራሁ ብለው ራሳቸውን ጠይቀው እኛን መደገፍና መርዳት አለባቸው፡፡”
——
“የግል ባለሀባቶቻችንን ዘንግተናቸዋል፡፡ መቼ ወደ እኛ መጥተው ያውቃሉ? መች አቅርበናቸዉ፣አደራጅተናቸዉ  እናውቃለን? በክልላችን የኢኮኖሚና የልማት ሥራ ራሳቸዉንመ  ጠቅመው ሀገራቸውንም እንዲጠቅሙ፣  እንዲለዉጡ አድርገን  እናውቃለን? እንደዚህ አይነት ዕቅድስ አለን? ብዙ ነገር ግን እናወራለን፡፡  እንደዚህ አይነት ነገር ሠርተን በተጨባጭ ካለን መሬት ላይ የትአለ? ስለዚህ ባለሀብቶቻችንን የግል ጥቅማቸውን ብቻ ሣይን ሀገርንም መጥቀም አለብን በሚል ዕምነት ከዚህ በኋላ በልማት ሥራዎቻችን ውስጥ አሣትፉን መሥራት አለብን፡፡ ያ ሲሆን ነው ኢኮኖሚ  የሚቀየረው፡፡
——
“የመጨረሻዉን ዕድል ሰጥቶን እንየዉ ብሎ ከሁሉም በላይ ይህንን በአል በዚህ መልኩ ተቀምጠን እንድናከብር ትልቁ ባለ ድርሻና ይህንን ሰላም ለሰጠን ህዝባችን ያለኝን ክብርና ምስጋና በናንተ ፊት ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ ይህንን ሰላም ያጎናጸፈን መሳርያችን ወታደሮቻችን ወይም መዋቅራችን አይደለም:: ህዝባችን ነዉ ዕድሉን የሰጠን፡፡ ከሁሉም በላይ ይህንን ማወቅ ይገባናል፡፡ ለሰጠን እድል ደግሞ እውቅና ልንሰጠዉ ይገባናል፡፡ የሰጠን ዕድል ደግሞ የመጨረሻዉ ነዉ፡፡ የተለያየ ካርድ አይተናል፤ ቢሆንም ግን አሁንም የመጨረሻዉን ዕድል ሰጥቶናል፤ ይህ ትልቁ ዕድል ነዉ፡፡ በዚህ ዕድል ደግሞ አዉቀን መጠቀም የኛ ድርሻ ይሆናል፤ ቢሆንልንና ብዙ ነገር ብናወራ ጥሩ ነዉ፤ የሚድን ከሆነ አንዴ የወሰዱት መድሃኒት ነዉ የሚያድነዉ፤ ላለፉት ስድስት ወራት ብዙ ያወራን ስለሆነ በዚህ ሁኔታ ተደጋግፈን ተረዳድተን የምንሰራ ከሆነ እንለውጠዋለን የማይለወጥ  ነገር የለም፡፡ “
——
“እኛም ድርጅት የተባልነው ለለውጥ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም፤ መታገል ያስፈለገን ለለውጥ ነው፡፡ ከሰራን እንለውጣለን፤ ከተቀመጥን እንጠፋለን፤  ሀገር እናጠፋለን፤ አሁንም ህዝባችን ያለዉ ችግር ብዙ ነዉ፡፡ እዉነት ነዉ ያስመዘገብነዉ ዉጤት አለ፤ በህዝባችን ዉስጥ ብዙ ችግር አለ፤ ብዙ የሚያሳፍሩን ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ለዉጥ ያመጡልኛል ብሎ ነዉ በተስፋ የሚጠብቀን፤ ስለዚህ ቁመን እንስራ፡፡ ትናንት ቃል እንደ ተገባባነዉ ቃል መገባባትና መማማል በቂ አይደለም ሰርተን መታየት ነዉ ያለብን፡፡ ሰርተን ተጨባጭ ለዉጥ አምጥተን ነዉ ማሳየት ያለብን፡፡ ይሄ ከሆነ ህዝባችን ማክበር ብቻ አይደለም በትከሻዉ ይሸከመናል፡፡ በታሪካችን ውስጥ አይተነዋል እስቲ 27 ዓመታት ወደ ኋላ ተመልሳችሁ አስታውሱ በሶስትና አራት ዓመታት ውስጥ  ጥሩ ነገር ስንሰራ ሕዝባችን ምን ያህል እንዳከበረን እናውቃለን፡፡ ይህንንም በተግባር አይተናል፡፡ አጣጥመን የማናውቀው ነገር አይደለም ከመስመራችን ወጥተን ማንቀላፋት ስንጀምር ደግሞ ምን ይህል እንደሚቀጣን አይተናል፡፡ ከዚህ በላይ ትምህርትና ልምድ የሚሆነን ነገር የለም፤ ስለሆነም ኑሮአችሁን በአቋራጭ የመለወጥ ፍላጎት ያላችሁ  ሰዎች ካላችሁ ከአሁን ወዲያ ይህ ቦታ በዚህ የሚመረጥ ቦታ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ሁኔታው ለዚህ ምቹ አይደለም፡፡”
——
“ስለሆነም ይህንን በዓል ስናከብር የሕዝባችንን ችግር በማሰብ፤ ትናንት የነበርንበትን ጨለማና ችግር በማስታወስ ድክመታችንን በማስታወስና ከአሁን በኋላ የዚህን ሕዝብ ኑሮ እንዴት መለወጥ አንችላለን በማለት እያንዳንዳችን ምን መስራት እንዳለብን ትኩረት ሰተን ካየነው በዓላችን መልካም በዓልና በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ፈጣሪ ረድቶን ስኬታማ የሆነ ሥራ ሰርተን አንገታችንን ደፍተን በአዳራሽ ውስጥ ተሰብስበን ሳይሆን ከሕዝባችን ጋር ሜዳ ላይ ወጥተን ጨፍረን የምናከብረው ይሆናል፡፡ ስለሆነም በዚህ መልኩ እንስራ ከሰራን ደግሞ ለውጥ እናመጣለን፡፡ ለውጥ አስመዝግበን የምናውቅ ስለሆነ ይህንን በመስራት የዛሬውን ቀን በዚህ መልኩ በማስታወስ ሁላችንም ማለትም ሕዝባችንም በለሃብቶችም ምሁራንም የሀገር ሽማግሌዎችም አባገዳዎችም ተረዳድተን የህዝባችንን ኑሮ እንለውጥ እላለሁ ጥሪአችንን አክብራችሁ ጊዜአችሁን ሰጥታችሁን ስለተገኛችሁ አመሰግናለሁ፡፡

የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ጀግነት መዳፈር ማለት የመላው አፍሪካ፣ የመላው የጥቁር ሕዝብን ክብር እና ነጻነት መዳፈር ነው

     



 0  15  15
ከኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው
የጋርቤን፣ የሃሪየት ተብማንን፣ የማርቲን ሉተር ኪንግን፣ የማልከም ኤክሳን፣ የፍረድሪክ ዳግላስን፣ የማንዴላን፣ የኳሜ ኒኩርሟን፣ በአጤ ምኒልክ የጀግንነት ደም የተወጉትን የነፃነት መሪዎች እና ለአንድነት የታገሉትን እና  እየታገልን ያለንውን መዳፈር ነው።
ቁጥር አንድ
ማርች 29፤ 2017
አዩ እርሶ ሳያውቁት ከዚህ በታች ያለው ስዕል ሰለባ ነዎት።


ከዚህ ቀጥሎ ያለው ደግሞ በሚገባ እንደተቀመጠው ነጮች አደዋ ላይ ከተሸነፉ በኋላ የበርሊኑ ኮንፍራንስ በ1884 የታለመው አፍሪካን ለመቀራመት እንደተፈለገው በተግባር ባለመዋሉ አሜሪካንም ተባብራበት የነበረው እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቶ በጦርነት መሪነት እና ሕዝብን አስተባብሮ ባጭር ጊዜ ጦርነትን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ የታወቁት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ጣሊያንን ስላንበረከኩት ማለትም ባጋጣሚ የተገኘ ድል ሳይሆን በልምድ እና በቆራጥነት በመሆኑ ለሌላው ጥቁር በአለም ውስጥ በተለይም በባርነት ይኖር የነበረውን ሁሉ ብድግ በማድረጉ ከአፍሪካ፣ አሜሪካን፣ ከሃይቲ፣ ካሪቢያን እስከ አሜሪካ አውሮፓውያን አንድ ድምጽ የሌለው መሳርያ ነደፉ። ከዚህም ድምጽ ከሌለው መሳርያ ዋናው ጥቁሩን (አፍሪካውያንን) ለይቶ አንገት ለማስደፋት በባርነትም የተያዘውን ባጠቃልይ አፍሪካዊ ነግሮ በነሱ አነጋገር አላሸነፈንም ሚኒልክ ጥቁር አይደልም በሚል የፈረንጅ ስእል እየሳሉ ጭምር የአፍሪካዊ (የጥቁር) አንጎል ከጦጣ የማይበልጥ ነው ሳይንስ አረጋግጥዋል በሚል በትምህርት ደረጃ የሳይንስ አንዱ መእራፍ በማድረግ ነድፈው ወድያው ከአደዋ ጦርንት ድል ማግስት ጥቁርን ሕዝብ ሳይኮሎጂካልይ ድምጽ በሌለው መሳርያ እያነበበ እና እያየ እራሱን እንደ ጦጣ አንጎል ባለቤት እንዲያይ ዘመቻ አድርገው ኖረዋል። በዚህ ድምጽ በሌለው የሳይኮሎጂ መሳርያ አይምሮው ከጦጣ የተሻለ አንጎል የለህም በተባለው እንደ እርሶ የተመረዘው በተግባር ሲተሮገም በሂደት ከታየው ማንም ሳይመራው እራሱን በእራሱ ዝቅ በማድረግ የተነገረውን ይዞ የራሱ ወገኖች በጦርነት ቦታ ተገኝተው የመዘገቡትን አላምንም ጣሊያን የነገረኝን ብቻ ነው በሚል ያውም ፋሽስት ጣሊያን እርሶ እንደተናገሩት በኤስቢኤስ ያልጻፈውን ሃቁን ገለባብጠው በማቅረብ ጭምር ማለት ነው።
“When you control a man’s thinking you do not have to worry about his actions. You do not have to tell him not to stand here or go yonder. He will find his ‘proper place’ and will stay in it. You do not need to send him to the back door. He will go without being told. In fact, if there is no back door, he will cut one for his special benefit. His education makes it necessary.” Carter Godwin Woodson.
እያደረገ ታሪኩን ሲያንቋሽሽ እና ለወጣቱም ትውልድ የፈረንጅ የበላይነት እንዲቀበል ለማድርግ ሃሰት ያስተምራል ማልት ነው።
“When you control a man’s thinking you do not have to worry about his actions. You do not have to tell him not to stand here or go yonder. He will find his ‘proper place’ and will stay in it. You do not need to send him to the back door. He will go without being told. In fact, if there is no back door, he will cut one for his special benefit. His education makes it necessary.” Carter Godwin Woodson.

Professor Tekeste Negash,
History is a weapon man think about it. Stop thinking in a white man’s mind, but yours.
I suggest you to go outside the White man’s book and educate yourself with Dr. Woodson advise bay reading “The Mis-Education of the Negro” by Carter Godwin Woodson And “What They Never Told You in History Class, Vol.1: Indus Khamit-Kush .

በቁጥር ሁለት እንገናኛለን እንደገና።
ይሄ ግልባጭ ለሚደርሰው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነሆ።
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ከCarter Godwin Woodson ጋር የሚቀመጥ ነው።
ታሪክ ያውም በነቃ ዘመን በአንድ መስመር የሚሄድ ሳይሆን በብዙ አቅጣጫ ያለውን ሃቅ ማንበብ እና መርምሮ አጥንቶ ማወቅን ይጠይቃል። ነጮች ያስተማሩን በእየዩንቨስቲው የኖረ ሃሰት ታሪክ ነው። እነሱን የከፍ የሚያደርግ ሚመለከት ብቻ እንጂ የእኛን ታሪክ አይደለም ያቀረቡልን በእርግጥ ባሪያናችሁ እያሉ አስተምረዋል። በአሜሪካን የአለም ወይም ወርልድ ሂስትርይ ፕሮግራምን ስንመለከት 80 % ውሸት ነው። በሚቀጥለው ከእነመረጃው ምን ማለት እንደፈለኩኝ በራሴ የደረሰብኝን : ውሸት አልቀበልም በማ ክፍል ውስጥ አቀርባለሁ።
ባሪያን ነፃ ለማውጣት የሚደረገው ትግል ቀላል ነው። ከባዱ ባርያውን ባርያ መሆኑን ማሳመኑ ነው።
ከየሐረርወርቅ ጋሻው።

ከዚህ በታች ባለፈው የጻፍኩልዎ ሲሆን የፊደል ስህተቶች ስላገኘሁበት አርሜው እንደገና ከዚህ በታች አስቀምጬዋለሁ።
(http://ethiopatriots.com/pdf/Yedres-Le-Pro-Tekesete-20170320.pdf)
ይድረስ ለፕሮፈሰር ተከስተ ነጋሽ : የታሪክ አላዋቂነትዎን ያርሙት።
ከዳላስ ቴክሳስ።
ባለፈው በኤስቢኤስ በአውስትራልያው የአማርኛ የሬድዮ ስርጭት ላይ ፡ በእርሶ እና የኢትዮጵያን ታሪክ አዋቂ ይሁኑ አይሁኑ ሳይገልጹ እርሶ እና ባለቤትዎ ስማቸውን ጠቅሰው ያው ፎቶግራፋቸው እንደሚያሳየው የውጪ ሰው ናቸው ማለትም ነጭ ፡ ስለ ኢትዮጵያ ሴቶች ጻፍን ብለው ሲናገሩ ፡መጀመርያ ባለቤትዎን እንክዋን በሚገባ ቦታ አልሰጥዋቸውም መጽሃፉን አብረን ጻፍን ከማለት ሌላ ሴትን ማክበር ከቤት ይጀምራል። ዋናው መልክቴ ስለእርሶ ስለባለቤትዎ ሳይሆን ፡ መቼም ለሴቶች መብት ታጋይም በመሆኔ ጠቀስኳቸው እንጂ ጉዳዬ ጀግናዋ ንቁዋ እና ብቸኛዋን ንግስት እሌኒን ማለት ከአዳል እና ከአማራ የተወለዱትን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የተዛነፈ ያልተሟላ በደንብም የማያቁትን አስመልክቶ መሴ ማርሾን ዡል ከአጤ ላሊበላ ጀምሮ ስለ አጤ ዘረያቆብ፡ አጤ በእደ ማርያም ፡ አጤ እስክንድር ፡ አጤ አምደ ጽዮን ፡ አጤ ናኦድ ፡ አጤ አጤ ልብነ ድንግል ፡ አጤ ገላውዲዮስ ፡ አጤ ሚናንስ ፡ አጤ ሰርጸ ድንግል ፡አጤ ኢያሱ ቀዳማዊ ፡ ታሪክ ዜና እና መዋዕልን ያጠቃልላል። ከእነዚህ 16 መስሃፍት ውስጥ ስለ አጤ ዘረያቆብ ፡ አጤ በእደ ማርያም ፡ አጤ ናኦድ እና ልጃቸው አጤ ልብነድንገል መለስ ብለው ቢያነቡ ወይም ቢያጠኑ ትልቅ የታሪክ ችሎታዎን ያስተካክልሎዎታል ብዬ በሚገባ አምናለሁ። እንደሚታወቀው አንድ ሰው ስለ እራሱ ታሪክ ወይም ስለ አለም ታሪክ ለማወቅ የታሪክ ፒኤችዲ አያስፈልገውም። ያለውን የታሪክ መጸሃፍ ሁሉ ስራዬ ፡ ጉዳዬ ብሎ ማንበብ እና መመራመር እና ፈረንጅ የጻፈውን እራሱን ከፍ እያደረገ ፡ ጥቁርን ዝቅ እያደረገ አሜን ብሎ መቀበልም እንዳይሆን ፡ ጥናቃቄን የራስን ታሪክ በሚገባ አውቆ ቀድሞ በመጠንቀቅ ጭምር ማለት ነው።
ፕሮፌሰር ተከስተ እርሶ ስለ ንግስት እሌኒ የተናገሩት ፡ ይዘገንንናል የልጅን ሚስት ለአባት።
“ንግስት እሊኔ ከአዲያ እና ከንባታ ይወለዳሉ። የአጼ ዘርያቆብ ባለቤት ነበሩ የሚል ነው።
ከዚህ በታች ያለው በትክክሉ የንግስት እሌኒ ታሪክ ነው። ለዚህም ከላይ እንዳስቀመጥኩት የመሴ ፕርሾን ዡልን መጽሃፍ ያንብቡ። ከዚህ ውጪ በመሄድ ምንም አዲስ ታሪክ ሊፈጠር አይቻለም ሃቁ የኢትዮጵያን ታሪክ ምንያህል በሚገባ ያውቁታል ነው።
ፕሮፌሰር ተከስተ ፡
ንግስት እሌኔ አይደሉም ሐድያ እና ከምባታዋ ንግስት ጽዮን ሞገሳ ናቸው። ንግስት እሌኒ የአጼ ዘረያቆብ ባለቤት አይደሉም ታሪክ እንደሚያስራዳው በተለያየ መጸሃፍ ተጽፎ ይገኛል። ለርሶ የማዝልዎ የበድጋሚ የፐሴ ፕርሾ ዡልን መጽሃፍ ነው። የአጤ ዘረያቆብ ባለቤት ንግስት ጽዮን ሞገሳ ይባላሉ ብሄራቸውም ከንባታ እና ሕዲያ ነው።
ንግስት እሌኒ የአጤ በእደ ማርያም ባለቤት ናቸው። ማለት የአጤ ዘረያቆብ ልጅ ባለቤት።
ንግስት እሌኒ በእርግጥ ልጆች አልወለዱም ። ስላልወለዱ አጤ በእደ ማርያም ንግስት ሮማነ ወርቅንም አግብተው ወልደዋል ። ንግስት ሮማንወርቅ የአጤ እስክንድ በእደ ማርያም እናት መሆናቸው ነው።
በተጨማሪ ፓንክረስት ስለንግስት እሌኒ የጻፉትንም የቅርብ ጊዜን መጽሃፍ ያንቡ እና እራስዎን ያርሙ ።
በተረፈ ስለ አጤ ምኒልክ ትልቅ ውሸት ስላስቀመጡ ይሄም ከመጽሃፍዎ መታተም ጋር የተያያዘ አዲስ ዘመቻ ጣልያን ሊቀለብስ የማይችለውን ታሪክ መቀልበስ እራሱ ጽፎ ከተሰራጨው ጭምር በሚገባ በእየአሃጉር ተቀምጦ ስላለ በተለይ ፈረንሳይ ፡ እንግሊዝ ፡ ጀርመን ፡ ፓርቱጋል ፡ ስፔን ለኢትዮጵያ ብለው ሳይሆን ለራሳቸው ታሪክን በመበወዝ ስለማይቀበሉ የአጤ ምኒልክ የጥቁር ሕዝብ አኩሪ ታሪክ
ለዘለዓለም ይኖራል። የራስ መንገሻ ዮሐንሳን የሃይለስላሴ ጉግሳን ፡ የመለስ ዜናውን አሰቃቂ እፍረት ታሪክ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጬ ቡድንን አሳፋሪ እራስን የሸጡ የመጀመርያዎቹ ጥቁሮች ታሪክ ለመሸፈን ሲባል በአጤ ምኒልክ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በሃሰት ኤርትራን አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል ቦታ ስለሌለው እስከመጨረሻው ትምህርት የጎደለብዎትን እንዲያገኙ እናደርጋለን የኢትዮጵያ ልጆች ለከርስ መጸሃፍ ለማሳተሚያ የማንገዛ። ጣሊያን እራሱ የጻፈውን እና ያሳተመውን በጊዜው ማንበብ ይኖርቦዎታል አሁን በውዞ የሰጠዎትን ትተው ይሄውም በማስረጃ እነሆ እናም ከጣሊያኖች ጋር ይጠያየቁበት። ባለቤትዎ ነጭ ስለሆኑ አዩ ነጭ ያለዎትን ይዘው መላክ የጻፈው አድርገው የሚያዩ ከሆኑ ከነጮቹ ሳጥን ይውጡ እና የአለም ታሪክ ሜዳ ላይ ይቁሙ። በስሜት ፡ በጥላቻ ፡ በገንዘብ ማንኛንም ታሪክ የጥሩም ይሁን የመጥፎ ሆንዋል እና ተመዝግቦ የገኛል እና ማንም ሊሰርዘው አይችልም መክኒያቱም ቴክኒዎሎጂው የረቀቀ በመሆኑ።
እንደገባኝ በጣሊያን ስለሚያምኑ ያውም ትግሬዎችን ሊውጣቸው መንጋጋውስጥ አግብቶ ምኒልክ አንበሳው በፍጥነት በነቃው አይምሮአቸው ደርሰው ያስተፉትን ወገኖችዎን የረፈረፋቸውን አማራው እና ኦሮሞው ሰራዊት በብዛት ግንባሩን እየሰጠ ያዳናቸውን እየሰደቡ ጣሊያንን ያለው ነው ትክክል ሲሉ በስብሰባ ላይ ስለተሰሙ ይሄው ሃቁን ያግኙት ከዚህ ቀጥሎ ባለው መጽሃፍ እና ገጽ ።
“Memoire d’ Afrique Page 393” “Adua. E. Bellavia. P. 227”
“La Prima Guerra d’ Africa, R. Battagalia, PP, 793—800.”
“Douze ans en Abyssinia…PP.528-530; Adua. Belavitta P, 394”
“L’ Italia in Africa, Serie Storico, Vol I, Tome II, A Vitale ,PP. 122-123”
ከዚህ በላይ ለፕሮፌሰር ተከስተ የጻፍኩት ታሪካዊ ስህተታቸውን እንዲያርሙ
ስለ አጤ ምንይልክ በወያኔ እየተደረገ ያለውን የሃሰት ዘመቻ በሚገባ ስለደረስኩበት አጤ ምኒልክን እና ጀግንነታቸውን አስመልክቶ የጻፍኩት በኢትዮፓትሪኦትስ ድህረ ገጽ መውጣቱን ለማረጋገጥ ስገባ ስለ አደዋ ክብረበአል ለመሳተፍ የሄዱ እህት አጤ ምንይልክ ሲሰደቡ ሰምተው መምጣታቸውን የጻፉትን ስመለከት ምናይነት አጋጣሚ ነው ብዬ ባንድ ፊት ስገረም በሌላ በኩል የፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽም በኤስቢኤስ ሬድዮ ከጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ስለ ጻፉት መጸሃፍ በሚገባ የተቀነባበረ የእፍረት ታሪክ መደለዣ በማድረግ ስለ ሴቶች እያወሩ ነገር ግን ዋና አላማው አጤ ምንይልክን የመንገሻ ዮሐንስ የልዋጭ ልዋጭን አሳፋሪ ከጣልያን ጋር ያደረጉትን ውል መረብን መሸጥ ማደብዘዣ ዜሮ ዘዳጋር አንድ ሆኖ አገኘሁት። ባይሆን ኖሮ ዩኒፎርም ወይም አንድ የሆነ ምንም ያልተዛነፈ መልክት እንደ አንድ አክተር አጥንቶ እንደሚጫወተው ተከስተም በዚህ መልክ ስለ አጤ ምኒልክ ባልተናገሩ ነበር። ሰውዬ ባጭሩ ከጣሊያን ያገኙት ጉርሻ እንዳለ ግልጽ ነው ብሎም ከወያኔ። በመሆኑም ኤስቢኤስ ላይ የተናገሩትን በአደዋም በአል ስብሰባ ላይ የደገሙት የዘመቻው ዋና አፈ ቀላጤ ስለተደርጉ ብቻ ነው። ሃቁ በሙሉ ተከስተ የተነጋሩት አጤ ምኒክን አስመክቶ ውሸት ነው ። በበኩሌ ኢትዮጵያ ብዙ የታሪክ እናት ስለሆነች የአጤ ምኒይልክ ጀግንነት ሃቅ ባይሆን ኖሮ የታሪክም ድሆች ከሆኑ ብሄሮች ስላልተፈጠርኩኝ የታሪክ ባለቤቶች ከሁኑት ከኢትዮጵያ ብሄሮች እንጂ ያውም የጦር እና የስልጣኔ ባለቤቶቹ ምንም ስለ አጤ ምኒልክ ባላስተባበልኩኝ ነበር በዚህ መልክ ። እኔ የምናገረውም ፡ የምጽፈውም ማስረጃ አምጪ በባል ማስረጃ የማቀብበት እና ማስረጃም ገና ሳልጠየቅ በማቅረብ እታወቃለሁ ስለምጽፈው ሁሉ። ይሄም የአጤ ምኒልክ ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም።
ከኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
ዘብሄረ አንድ ኢትዮጵያ።
Email: yehar9@aol.com

ትንቢታዊ መልእክት ከቆሼ – ያየያየ ይልማ



ከአውሮፓ ከተሞች ሁሉ ዝቅ ያለ ነው ደረጃዋ የተባለችውን፡  የአንዷን አውሮፓዊ ከተማ የቆሻሻ  አሰባሰብ ስርአቷን ፣ ቆሻሻ ስለሆነ ብቻ እንደው ባንድ ስም ቆሻሻ ተብሎ ወስዶ መጣል ሳይሆን፤ በሚገርም የቆሻሻ አይነትና ዝርዝር ብዛት እንዲወገድ ህብረተሰቡን ስለ እያንዳንዱ ቆሻሻ አወጋገድ የሚያስተባብሩበት መንገድንና ፣ እንዲሁም አጠቃላይ የቆሻሻ አወጋገድ ዘይቤያቸውንና አስተዳደራቸውን ፣ በእንግድነት ሰሞኑን ሄጄ እንደታዘብኩ፡ እጄን ባፌ ላይ ጭኜ የእውነት አገሬን አሰብኳት፤ በተለይ አዲስ አበባን፡፡
ከዚያም እንዴ እረ ለመሆኑ ኢትዮጵያን እንመራለን ብለው የሚደናገሩት ሰዎች በሙሉ ለቁጥር ለሚያታክት ጊዜ ያክል በምእራባዊያኑ አገራት ሲዘዋወሩ፡ የልምድ ልውውጥ ትብብር ሲፈራረሙ መኖራቸውን ብሰማም ፣ እንደው ለምን ይሆን ለህዝባቸው እንደው እንደዚህ አይነት በጎ ተሞክሮዎችን የማይኮርጁት እያልኩ እና በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ክልል መሪዎች መካከል በተነሳው ውዝግብ ምክንያት አዲስ አበባ ለሳምንታት እንዴት ገምታ እንደነበር አስታውሼ አዝኜ ሳላበቃ፣ ሳምንት እንኳ ሳይቆይ፣ የቆሼን እልቂትን መርዶ ሰማሁ እና አረፍኩት፡፡ በዚህ ክፉ መርዶ ዜና ምክንያት ነበር ታዲያ ሁለት ነገሮችን፡ ከዚህ እልቂት ጋር ስለተያያዙ ነገሮች በግሌ ማስተዋል የቻልኩት፡፡
አንደኛ
…የወያኔ አንደበት የሆኑት የተለያዩ ሰዎች ፣ በተለይ ወያኔን በተለያዩ ሚዲያዎች የክፋቱ ተወካዮች ሆነው የሚቀርቡት ሰዎች ስሜታዊ ሁለንተና፤ የአንድ እናት ልጅ የሆኑ እስኪመስል ድረስ፡ በሚያደናግር መንገድ አንድ መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡
ለዚህ ማሳያ እንዲሆን፣ ከአመታት በፊት ስሙን የማላስታውሰው  ፣ አንድ እጅግ አስገራሚ ስብእና ያለው የሸገር ኤፍኤም ራድዮ ጣቢያ ዜና አንባቢ-
(ልቅሶና ሲቃ በሚተናነቀው ድምፅ)
“…እድለ ቢስ ሆኜ ይህንን ክፉ መርዶ አንባቢ እንድሆን ተፈረደብኝ እንጂ ፣ ለእንጀራ ቢቻ ቢሆን ይህንን ዜና ፈቅጄ ከማንበብስ እንጀራው ጥንቅር ብሎ ቀርቶ ሞቴን እመርጥ ነበር፤”… በማለት ነበር ይህ ስሙን ባላስታውሰውም ልረሳው የማልችለው ጋዜጠኛ፡ የታላቁን ፣ የኢትየጵያ የሙዚቃ ንጉስ ፡ የጥላሁን ገሰሰን ሞት ለአዲስ አበባና ዙሪያዋ ነዋሪ ህዝብ ፣ ድንገተኛ የሞቱን መርዶ  የተናገረው፡፡
እንዲሁ ታዲያ ከአመታት በኋላ ፤ ሌላ ክፉ ዱብዳ ፣ ቅዳሜ መጋቢት 02 – 2009 የብዙዎችን እስትንፋስ እስከወዲያኛው፡ አመድ አለበሳቸው ፡፡ በዚህ ጊዜ፤ “ቆሼ ተደርምሶ ነዋሪዎችን ገደለ”፡ የሚል ዜና በኢቲቪ ተነበበ፡፡ የውድቀታቸው ዜና እንዲሁ ይጠርላቸው ብያለሁ፣ የሚስማማ ካለ አሜን ብሎ ይቀበል፡፡
ግን ዜናውን ያረቀቀው ሰው፣ እንደ ሸገሩ አንባቢ ቆሽት ቢኖረው ኖሮ፣  በቆሼዎቹ ምንዱባን ሞት ያለጥርጥር እርር ቅጥል ስለሚል ጥርሱን ነክሶ፡ እንዲህ ይል ይመስለኛል፤
በጉድፍ መጣያው ቆሼ፡ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት ተነባብሮ ተከምሮ የኖረ የቆሻሻ እና ክርፋት ተራራ፡ እንደ ጉድፍ ተቆጥረው ተገፍተው፡ ከቆሻሻው እየበሉ ከጎኑ በድህነት ይኖሩ ከነበሩ ጭርቁስ ጎረቤቶቹ ፣ ይልቅ እርሱ ቆሻሻው ጉልበት ኖሮት፣ ጉልበቱ ከድሃ ኢትዮጵያዊ ፈፅሞ ልቆ ፡ ከጀግና እኩል ከመቶ ሃያ በላይ የሰው ነብስ ግዳይ ውጦ ልካችንን አሳየን፡፡ ብሎ ተናግሮ ለሟቾች ዘመዶች ውለታ ይውልላቸው ነበር!! ግን አልሆነም፡፡ የኢቲቪ ጋዜጠኞች አይናቸው ኩል የተኳለ እስኪመስል ድረስ ፡ ወር ሙሉ ዜና ባነበቡ ቁጥር የሚያለቅሱት፡ ኢትየጵያ አይታ የማታውቀው ነብሰ በላ – መለስ፡ በፈጣሪ ፍርድ እንደ ማንኪያ ተቀንጥሶ መሄዱን መቀበል ያቃታቸው ጊዜ ነበር፡፡
ሁለተኛ
በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር ለአገር የሚበጅ ነገር  እንደሚመጣ ወያኔ ቢያውቅም ፣ እንዲህ አይነት መንገድን መከተል ቀድሞ የሚያጠፋው ወያኔን ስለሆነ፡ በእወቀት ላይ የሚመሰረት የአመራር ተሞክሮ ወያኔ ባቋቋማቸው የደደብነት ኢኒስቲዩቶች ውስጥ ገብተው እስካልተበረዙ ድረስ ጥቅም ላይ አይውሉም፡፡ 
ከታታላቆቹ አፍሪካዊ መሪዎች አናት ላይ የሚቀመጡት  አፄ ምንሊክ እና አፄ ኃይለስላሴ እጅግ በሚገርም ፈር ቀዳጅነታቸው እስከ ዛሬም ድረስ የምንጠቀምባቸውን ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችንና አገልግሎቶችን የሚከፈለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለው ለህዝባቸው ጥቅም ላይ አዋሉ፡፡ በዚህ ረገድ፣ ከባቡር ትራንስፓርት፣ ፖስታ፣ ቴሌኮሞዩኒኬሽን እስከ ዘመናዊ ትምህርትና ተሸከርካሪዎች እስከ የአየር እና የባህር ትራንስፖርት ድረስ የሚዘረጋ ፤ ከዘርፈ ብዙ የከተማ ልማት የስነ ህንፃን የማስፋፋት ትጋት እስከ ፈር ቀዳጅ ፖለቲካዊ አመራር ድረስ ጭምር በተሰሩ ስራዎች፣ አሁን ያሉ ኢትዮጵያዊያን የሚጠቀሙባቸው እና የሚኮሩባቸው ስራዎች፣ ከቀደምት መሪዎቻችን የወረስናቸው ህያው ውርሶቻችን ሆነው ዛሬ ድረስ አሉ፡፡
ወያኔ ለኢትዮጵያዊያን የሚበጅ ነገር ከተለያዩ የአለም ተሞክሮዎች ሳይመለከት ቀርቶ ሳይሆን፣ ከላይ እንደጠቀስኩት አይነት ባይፈጠሩም ሊቀዱ የሚገባቸው ተሞክሮዎችን ፤ በሚያስገርም ቁርጠኝነት እንደዚህ አይነት ከሌላ አለም ሊገኙ የሚችሉ እና  በእውቀት ላይ የሚመሰረት አመራር እና አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚጠይቁ በጎ ተሞክሮዎችን ማጥፋት ዋነኛ ተልእኮው ስለሆነ ነው እንጂ፤
ወያኔ አድርጎት ከኮረጀም የሚኮርጀው እንደፈለገ ቀዶ መስፋት የሚችላቸውን፣ ተሞክሮዎችን ብቻ ይሆናል፡፡ እነዚህም ታዲያ ከራሱ እጅግ ክፉ የአገዛዝ ስርአት ጋር ሊሄዱ የሚችሉ አይነት፤ ለምሳሌ በዘርኝነት ላይ የተመረኮዘው የፌደራል አገዛዝ እና በፀረ-ሽብር ስም መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት በሰሚ ሰሚ የሚያመክንበት አይነት ፖሊሲና ህጎቹ ብቻ ናቸው፡፡
ታዲያ እዚህ ጋር ወያኔ ያላወቀው ነገር ምን መሰላችሁ፣ ቆሼ የሚታየው ቆሻሻ፣ የሚታየው ሻጋታ ተከምሮ ያገዘፈው ተራራ ነበር፡ ስለዚህ መፍረሱ አይቀሬ ነበር! ምክንያቱም ውስጡ በስብሷል፡ እንኳን አምነው ተጠግተው ከክርፋት የሚገኝ ዳቦ ለሚቃርሙ መኖሪያነት ምቹ ሊሆን ይቅርና ለራሱም ቀን የሚጠብቅ፡ የተጣሉ የሸተቱ፡ የሻገቱ ብስባሾች የቆለሉት ክምር ነበርና ተደረመሰ! ይህ ግን ለወያኔ መፃኢ እጣ-ፈንታው ፡ ስሪቱን እና አወዳደቁን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አይቀሬ ሃቁ ነው፡፡ የቆሼው እልቂት፡ የላይ የውጪ ሻጋታና ክምር ድርምስ ነው ፤ የወያኔ አደረማመስ ግን ፡ አፅሙን የሚያንኮታኩት ታላቅ ነውጥ ነው!!!
… የሚናፍቀኝ የወያኔን ድንገተኛ የህልፈት መርዶ ፡ የዛ የታላቅ የሸገር ኤፍኤም ዜና አቅራቢ መንፈስ እና ኢትዮጵያዊ ቆሽት ባላቸው ሰዎች ሲነበብ ዜናው የሚደራጅባቸው ቃላቶች እና ድምፃቸው ነው፡፡ የዛ ሰው አርጎ ያገናኘን!!!

Thursday, March 30, 2017

ዜና ወልቃይት ….በወልቃይት የታሰሩ ወጣቶች ካልተፉ በአዲረመጥ ሌላ ተጋድሎ ሊጀመር ይችላል፤ – ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው



ሳተናው
By ሳተናውMarch 30, 2017 06:46 

ከአንድ ወር በፊት የአዲረመጥ ልጆች ለኳስ ጨዋታ ወደ ማይጋባ ሒደው ነበር፤ ሆኖም ሰፋሪዎች በትግራይ ፖሊሶች ታግዘው የአዲረመጥ ልጆችን ይደበድባሉ፡፡ ዛሬ ደግሞ ባለፈው የወልቃይት ልጆችን ሲያሰቃዩ የነበሩ ሰፋሪዎች ለስብሰባ ወደ አዲረመጥ መጡ፡፡
ለስብሰባ የመጡት ሰፋሪዎች ‹‹ዐማሮች ሊደበደቡን ነው›› የሚል ክስ በማሰማታቸው በሦስት መኪና የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ወልቃይት ጉዞ ጀምረዋል፡፡ ከዚህም በላይ በማይጋባ ከተደበደቡት ልጆች መካከል የተወሰኑትን ወጣቶች የታሰሩ ሲሆን ከታሰሩት ልጆች መካከል ፎቷቸው ከዚህ ሥር የተቀመጠው ሰሎሞን አታላይና አበራ አለነ ይገኙበታል፡፡ የታሰሩ ልጆች ካልተፈቱ ነገሮች ሊቀየሩ ይችላሉ ተብሏል፡፡ በአዲረመጥ ሌላ ሕዝባዊ ተጋድሎ ሊቀጣጠል ይችላል፡፡

“ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሁንም ጸረ ሰላም ሃይሎች ይንቀሳቀሳሉ” ብለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አራዘሙት | ዜና ትንታኔ

    

ከፋሲል የኔዓለም | የኢሳት ጋዜጠኛ
ዛሬ የኢህአዴግ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ 4 ወራት እንዲራዘም ወስኗል። አቶ ሲራጅ ለአዋጁ መራዘም እንደ ምክንያት ያቀረቡት “ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሁንም ጸረ ሰላም ሃይሎች ይንቀሳቀሳሉ” የሚል ነው። በመላ አገሪቱ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ህዝቡ አዋጁ እንዲራዘም መጠየቁና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም “አዋጁ ቢራዘም መልካም ነው” የሚል አስተያየት መስጠቱ ተገልጿል።

ህወሃታውያን በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ “ ጸረ-ሰላም ሃይሎችን” በቁጥጥር ስር ማዋል ይችሉ እንደሆን እናያለን። ግን የገረመኝ የአርበኞች ግንቦት7 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን ለይቶ ውሳኔ ማሰለፉን በሰማሁ በሰዓታት ውስጥ አዋጁ ለ4 ወራት የመራዘሙን ዜና መስማቴ ነው። ያጋጣሚ ነገር ይሆን ወይስ …?
ለማንኛውም ህወሃት/ኢህአዴግ አካሄድኩ የሚለውን የዳሰሳ ጥናት በተመለከተ ኢሳት የካቲት 14 ቀን 2009 ዓም ባወጣው ዜና እንዲህ ብሎ ነበር- “ በተለያዩ የጎንደር ቀበሌዎች በተካሄዱ የህዝብ ስብሰባዎች፣ የአገዛዙ ካድሬዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት በኩል የህዝቡ አስተያየት ምንድነው በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ህዝቡ ግን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በጽሁፍ ፣ “ እናንተን አንቀበላችሁም፣ አናውቃችሁም፣ ከህዝብ ውጭ ሆናችሁዋል” የሚል መልስ በብዛት መስጠቱ ካድሬዎችን አስደንግጧል። አንዳንድ ሰዎች “ አዋጁን ስታውጁ እኛን አላማከራችሁንም፣ ሁሌም በራሳችሁ ከላይ ወስናችሁ ከጨረሳችሁ በሁዋላ ነው እኛን የምትጠይቁን፣ እኛ ደግሞ ኮማንድ ፖስት ተነሳ አልተነሳ ከግድያና አፈና አትታቀቡም፣ ብትፈልጉ አንሱት ባትፈልጉ ተውት፣ ጥቅሙን መጨረሻ ላይ ታገኛላችሁ” የሚሉ አስተያየቶችም በብዛት ተሰጥተዋል።”
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቡድን አዋጁ እንዳይነሳ አስተያየት መስጠቱን በተመለከተም ኢሳት በጥር 30 ዘገባው ላይ እንዲህ ብሎ ነበር – “በአማራ ክልል የሚታየውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም ከፌደራል የተላከው የኮማንድ ፖስቱ አጣሪ ቡድን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳ ህዝቡ በቀጥታ በመንግስት ላይ ከእስካሁኑ የከፋ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። ኮማንድ ፖስቱ “ የክልሉን ህዝብ ገትቶ የያዘው መሳሪያ ነው” ያለ ሲሆን፣ አዋጁ ቢነሳ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ አመፁን ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠናል” ብሎአል፡፡ለአንድ ወር ያክል በጎንደር፣ በባህርዳር እና በአዊ ዞን የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ የህዝቡን ሁኔታ ማጥናቱን የሚገልጸው የፌደራል ኮማንድ ፖስት ቡድን፣ በአማራ ክልል የተካሄደው ተሃድሶ የይምሰል እና ስር ያልስደደ ነው ሲል አጣጥሎታል።”
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተራዘመው በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎችን ለመደምሰስ አይመስለኝም። ይህ እንደማይሆን እነሱም ያውቁታል፤ ባለፉት 6 ወራት ታጋዮቹ ራሳቸውን በማጠናከር በኩል ብዙ ስራዎችን ሰርተዋል፤ “ሳይቃጠል በቅጠል” የሚባልበት ጊዜ አልፏል። አዋጁን ለማራዘም የተገደዱት በተለይ በ2 ምክንያቶች መሆኑን አምናለሁ። ጥልቅ ተሃድሶ ብለው ባዘጋጁዋቸው መድረኮች ላይ የህዝቡ ቁጣ በቀላሉ እንደማይበርድ አረጋግጠዋል። በመድረኮች ላይ የተሰጡት አስተያየቶች ፍርሃት ለቆባቸዋል። አንድም ሰው እነሱን የሚደግፍ አስተያየት አለመስጠቱ ግራ አጋብቷቸዋል። በእኔ እምነት ህወሃታውያናንን እያስፈራቸው ያለው በድንበር አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በበለጠ የመሃል አገሩ ህዝብ ቁጣ ነው። ሰሞኑን በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ ፣ “መሃሉ ዳግም ከተነሳ ከእንግዲህ በመሳሪያ አናቆመውም” የሚል አስተያየት በከፍተኛ ባለስልጣን ተነግሯል። በጎንደር አንድ የመኮንኖች ስብሰባ ላይም እንዲሁ መኮንኖች ” ፖለቲካዊ መፍትሄ ካልተገኘ በስተቀር የህዝቡ ተቃውሞ በጉልበት የሚቆም አይሆንም” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ወታደሩ ሰልችቷል።
ሌላው ምክንያት ደግሞ በድርጅቶች ውስጥ ያለው መከፋፈል እየጨመረ መሄዱ ነው። በተለይ ኢህአዴግን ከመሰረቱት 4 ድርጅቶች ውስጥ የሁለቱ ህልውና አዳጋ ላይ ወድቋል። በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በማንኛውም ጊዜ “ውስጣዊ ፍንዳታ” ሊከሰት ይችላል። አዋጁ በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ እነዚህን ድርጅቶች ከውስጣዊ ፍንዳታ ይታደጋቸው አይታደጋቸው የምናየው ይሆናል።
ለማንኛውም ግን አዋጁ፣ በአንድም ይሁን በሌላ፣ አገዛዙን ዋጋ እያስከፈለው ነው። የገጽታ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የአመኔታ ወዘተ።

የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው በቅርቡ በባለቤታቸው ላይ የደረሰውን አስገራሚና አሳዛኝ ሁኔታ ገለፁ


By ሳተናውMarch 30, 2017 06:05



“….. ኃይሌ የግል ህይወቱን በሚመለከት ደግ ነው፣ ጥሩ የቤተሰብ ሰው ነው፣ ቤተሰቡን የሚያከብር፤ ከዛም ውጪ ልጆቹንምየሚንከባከብ፤ ከዛም አልፎ ደግሞ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ …. በኢትዮጵያዊነቱ በመርዳርት የሚያምን ሰው ነው።
                                                                ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው 121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ዳላስ ውስጥ ሲከበር ከተናገሩትየተወሰደ
121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ባሳለፍነው ሳምንት በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያ ጉዳዮች የውይይት መድረክ ፎረም አዘጋጅቶ ፕ/ርኃይሌ ላሬቦን በክብር እንግድነት ከተጋበዙት አንዱ መሆናቸው የሚታወስ ነው። በእለቱ ከባሌቤታቸው ጋር እንዲመጡ የተጋበዙት የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው በስፍራው ተገኝተው ዝግጅቱን ያዘጋጀው ፎረም በማመስገን በኢትዮጵያ ጉዳዮች በተለያየ ወቅት የግልአስተያየታቸውና ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በሚያበረክቱት ባለቤታቸው ከሚደርሰው ዛቻና ማስፈራሪያ በተጨማሪ በመላው ቤተሰቡ የሚደርሰው ጫናለታዳሚው አስረድተዋል። ይህ ተግባር ቀድማም የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በኢሳትና በሌሎች ኢትዮጵያ ነክ በሆኑ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት አስተያየትያልተደሰቱ ግለሰቦችና ቡድኖች በተደራጀ መልኩ በመላው ቤተሰብ ጫዋነት የጎደለው ድርጊት በመፈፀም ከፍተኛ ጫና ሲፈጥሩባቸው እንደነበርገልፀዋል። በዚህ ሁሉ አስከፊ ወቅት ከባለቤታቸውና ከመላው ቤተሰብ ጎን መቆም አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩትን አመስግነዋል።

ያልተሸፋፈነው የፕሬዝዳንቱ አስገራሚ ንግግር


received_1877523075852220

” ለስም ወንበር ላይ መቀመጥ ዋጋ የለውም ! ”
“ዛሬ ከ27 ዓመት በኃላ በምንም መመዘኛ ደርግ ይህን አድርጓል ኃ/ስላሴ ይህን አድርጓል እኛ ይሄን አድርገንልሃል ብለን የምንነግድበት ሸቀጥ በእጃችን የለም፡፡ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ህዝብ እንደሚያስተዳድር ድርጅት፤ ራሳችንን የምናይ ከሆነ እንደምሣሌ የሚታዩ ሀገሮች በ30 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለምሳሌ የኤዥያ አገሮችን ብንወስድ ዛሬ በአለም ላይ በዕድገት የሰማይ ጥግ የደረሱ አገሮች ታሪካቸው የ20፣ የ30፣ የ40 ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ ሌላ ታሪክ የላቸውም፡፡ በዚህ ነው ራሳችንን መመዘን ያለብን እንጂ ወደኋላ ተመልሰን ሞቶ አፈር ከለበሰው ጋር ራሳችንን ዝቅ አድርገን ማወዳደር፣ በዚያ ራሳችንን ማሞኘት ይሆናል ፡፡ ከዚህ ተነስተን ስናይ መስራት ያለብን፤ መድረስ ያለብን ደረጃ ደርሰናል ወይ ብላችሁ ለጠየቃችሁ… አልደረስንም፡፡ አልደረስንም ሣይሆን ትንሽ ነገር ነው የሰራነው ብዙ ነገር ይቀረናል ብለን ራሳችንን መመዘን አለብን፡፡ ብዙ ነገር ይቀረናል፡፡ ለምንድነው እዝያ መድረስ ያቃታን መሮጥ፣ መሄድ ሲገባን ለምን አዘገምን ብዙ ችግር ስላለብን ነው፡፡ ያንን በተሃድሶአችን ደጋግመን ስላየን አልደግመውም፡፡ እንናገራለን እንጂ የምንናገረው ነገር በሽታው ያለበት ሥፍራ የሚያክ አይደለም፣ በሽታው ያለበትን ሥፍራ የሚያድን አልነበረም፡፡”
“እርግጥ ነው ንግግራችን ትልቅ ነው፡፡ ከይቅርታ ጋር ምላሳችንን አርዝመን ብዙ ተናግረናል፡፡ የምላሳችንን ያህል እጃችን ሊደርስ አልቻለም፡፡ የችግሩን ሥፍራ አላየንም አልነካንም፣ አልወጋንም፤ እንጂ እራሳችንን ማየት ቀርቶብን አይደለም፡፡ እርስ በርስ መገማገም ተጨካክነን እርምጃም መውሰድ ቀርቶብን አይደለም፤ መውጋት ያለብንን ሥፍራ ግን አልወጋንም፡፡ ለዚያ ነው ዛሬ ስራችን ጎዶሎ የሆነው፡፡
መንገድ ላይ የቀረነው ብዙዎቻችን ነን፡፡ ትላንት ያሰብነው ለህዝብ ተቆርቋሪነት አጥተን ረስተን መንገድ ላይ ጥለን ያለፍን አውላላ ሜዳ ላይ የቆምን ብዙዎቻችን ነን፡፡
አንዳንዱ የራሱን ጌታ ፈጥሮ የሚሰግድለት አለ፡፡ ጌታ መፍጠር ለምን ይመጣል? ለምን አስፈለገ? ለምን ተፈለገ?…. ለሰላም ? የድርጅታችን መስመር ይህን ስለሚል? ህዝቡ ይሄን ስለሚፈልግ ???……. አይደለም፡፡ በእርግጥ የድርጅታችን ችግር ነበር ወይ ? አዎን የድርጅታችን ችግር ነበር እውነት ነው፡፡ አንድ የሚያመን ሥፍራ እዚህ ጋር ነበር መደባበቅ ስለሌለብን ነው፡፡ ለምንድን ነው ተመልሰን እርስ በርስ የምንባላው? አንድ ህዝብ ነው ያለን፣ አንድ ሀገር ነው ያለን፣ አንድ አላማ ነው ያለን፡፡ ይህ ከሆነ ለምን እንከፋፈላለን? ለምን እንባላለን? ለምን ደባና ሸር አንደኛችን በሌላኛችን ላይ እንፈፅማለን?”
ምክንያቱ ግልጽ ነው “የህዝባችን ችግር ሳይሆን የግል ጥቅምን የማስቀደም ችግር ስላለ ነው፡፡ ከህዝብና ከሀገር ጥቅም የግል ጥቅምን ማስቀደም ስላለ ነው፡፡ ሌላ አይደለም ! ሌላ ፍች የለውም ! ራስን ማስቀደም ስላለ ነው:: የራስ ጌታ ሲፈጥር ደግሞ በሄደበት ሁሉ ጉልበቱ ይብረከረካል፡፡ ወንበር ላይ መቀመጥ እንፈልጋለን ወንበር ላይ መቀመጥ ለስም መሆን የለበትም፡፡ በተቀመጥንበት ወንበር ላይ ወንበሩ የሚፈልገውን ሥራ መስራት ካልቻልን ወንበሩ የሚፈልገውን ውሳኔ መስጠት ካልቻልን ለስም ወንበር ላይ መቀመጥ ዋጋ የለውም፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነት ችግሮች ስላሉብን ነው ከ27 ዓመት በኋላም መድረስ የሚገባን ሥፍራ ሳንደርስ ታግለን ከታገልንለት ህዝብ ጋር የተቃቃርነው ለዚህ ነው፡፡ ለዚህ ነው የተጨካከነው ሌላ አይደለም አሁንም ህዝቡ የመጨረሻ እድል ሰጥቶናል በእውነት ሁሉ ነገር ድኗል ሁሉ ነገር ምላሽ አግኝቷል ሁሉ ነገር አልቆለታል ብለን የምናስብ ከሆነ ሞኝነት ነው፡፡
ራሳችንን ማሞኘት የለብንም ሀገር ሰላም ነው አዎ ሀገር ሰላም ነው፡፡ ግን ሰላም አይደለም፡፡ አጭር ዕድል ነው የሰጠን እንጂ ህዝቡ ሰላም አይደለም፣ እድል ሰጥቶናል የመጨረሻ ዕድል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚሰሩ እንይ ብሎ እድል ሰጥቶናል፡፡ ይህን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በደንብ ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡”
“እንደ ድርጅት፣እንደ መንግስት እያንዳንዳችን ከገባንበት ጓዳ ውስጥ አንገታችንን ይዞ አውጥቶ የፈለገውን ነገር ሊፈጽምብን እንደሚችል እንዲህ አይነት እርምጃ ሊወስድብን እንሚችል አይተናል፡፡በፊልም ሣይሆን በተጨባጭ ውስጥ ኖረን አይተናል ይሄ ቲያትር አይደለም፡፡ ጎበዝ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡
ወዲያና ወዲህ የምናይ ሰዎች ካለን ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ የእኛ ጌታ ህዝባችን ነው፡፡ ለየክልላችን ህዝብ ነው፡፡ ሌላ ጌታ የለንም፡፡ ለሌላ ጌታ መስገድ የለብንም፡፡ ትልቅ ድርጅት አለን 4 ሚሊየን አባላት አሉን፡፡ አራት ሚሊየን ማለት በጣም ትልቅ ነው፡፡ በአለም ላይ አራት ሚሊዬን አባላት ያሉት ድርጅት ውስን ነው፡ እንደነ ቻይና ያሉት ካልሆነ በስተቀር ውስን ነው፡፡ በቁጥር አይደለም እንዲሁ በስም ብንናገር 50 ሚሊየን ህዝብ ነው እኮ ያለን፡፡ ይህን ይዘን ለምን እግራችን ብርክርክ እንደሚል ለምን እንደምንፈራ ለምን ወደ ጓዳ ተመልሰን አንገታችንን ደፍተን እንደምናጉረመርም አይገባኝም፡፡”
“አሁን ያለን ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ደጋግመን ስንል እንደነበረው ማዳመጥ ያለብን ማየት ያለብን ይሄንን ህዝብ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ ሌላ አራማራጭ የለውም፡፡ እንደ ሥራው ክብደትና ድካም እያንዳንዱ ተቀብሎ ይሞክር ብለን አስረክበን ብንወጣም ደስ ይለን ነበር፡ ዛሬ እንደዚህ አይነት ምርጫ አለን? እስቲ ይቅርብን ሌሎችም ይሞክሩት፡፡ ሰባት አመት ሣይሆን 27 ዓመት የለፋንበት ስለሆነ፡፡ አንዳዶችን እንዲያውም ሰውነታችን የዛለ በመሆኑ ፡፡ ሌላው እስኪ ይየው ብለን እንደዚህ መቀባበል ቢቻል እንላለን፡፡ በዚህ መልኩ የተዘጋጀ ነገር ቢኖር ደስ ባለን ነበር፡፡ እውን በዚህ ደረጃ ይህ አለ ወይ ብለን ብንጠይቅ የለም፡፡ ራሳችንን ማታለል የለብንም፡፡ እኛም ደግሞ መሆን ያለብንን ሳንሆን ቀርተን እየተዉረገረግን በመሄድ፣እንዲሁ አስመስለን በመጓዝ ብቻ ረጅም መንገድ መሄድ እንችላለን ወይ ብለን ብንጠይቅ አንችልም፡፡መስቀለኛ መንገድ ላይ ነዉ ያለነዉ፣ራሳችንን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ልናጠፋ ስለምንችል፡፡ ሀገርንም ልናፈርስ እንችላለን፡፡ ሀገር እንደ ድንገት ሲፈርስ ደግሞ አይተናል ሩቅ ሳንሄድ ከጎረቤት ሀገር፡፡ በዕቅድ የሚፈርስ ሀገር የለም፡፡ ስለዚህ ያለን ምርጫ ቆም ብለን አሁንም ደጋግመን ስንል እንደነበረው ጥርሣችንን ነክሰን ከዚህ ህዝብ ጋር ሆነን ለህዝቡ መሥራት ነው ሊያዋጣን የሚችለዉ፡፡
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ 27ኛ የምስረታ በዓልን በማስመልከት በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

ያልተሸፋፈነው የፕሬዝዳንቱ አስገራሚ ንግግር


received_1877523075852220

” ለስም ወንበር ላይ መቀመጥ ዋጋ የለውም ! ”
“ዛሬ ከ27 ዓመት በኃላ በምንም መመዘኛ ደርግ ይህን አድርጓል ኃ/ስላሴ ይህን አድርጓል እኛ ይሄን አድርገንልሃል ብለን የምንነግድበት ሸቀጥ በእጃችን የለም፡፡ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ህዝብ እንደሚያስተዳድር ድርጅት፤ ራሳችንን የምናይ ከሆነ እንደምሣሌ የሚታዩ ሀገሮች በ30 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለምሳሌ የኤዥያ አገሮችን ብንወስድ ዛሬ በአለም ላይ በዕድገት የሰማይ ጥግ የደረሱ አገሮች ታሪካቸው የ20፣ የ30፣ የ40 ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ ሌላ ታሪክ የላቸውም፡፡ በዚህ ነው ራሳችንን መመዘን ያለብን እንጂ ወደኋላ ተመልሰን ሞቶ አፈር ከለበሰው ጋር ራሳችንን ዝቅ አድርገን ማወዳደር፣ በዚያ ራሳችንን ማሞኘት ይሆናል ፡፡ ከዚህ ተነስተን ስናይ መስራት ያለብን፤ መድረስ ያለብን ደረጃ ደርሰናል ወይ ብላችሁ ለጠየቃችሁ… አልደረስንም፡፡ አልደረስንም ሣይሆን ትንሽ ነገር ነው የሰራነው ብዙ ነገር ይቀረናል ብለን ራሳችንን መመዘን አለብን፡፡ ብዙ ነገር ይቀረናል፡፡ ለምንድነው እዝያ መድረስ ያቃታን መሮጥ፣ መሄድ ሲገባን ለምን አዘገምን ብዙ ችግር ስላለብን ነው፡፡ ያንን በተሃድሶአችን ደጋግመን ስላየን አልደግመውም፡፡ እንናገራለን እንጂ የምንናገረው ነገር በሽታው ያለበት ሥፍራ የሚያክ አይደለም፣ በሽታው ያለበትን ሥፍራ የሚያድን አልነበረም፡፡”
“እርግጥ ነው ንግግራችን ትልቅ ነው፡፡ ከይቅርታ ጋር ምላሳችንን አርዝመን ብዙ ተናግረናል፡፡ የምላሳችንን ያህል እጃችን ሊደርስ አልቻለም፡፡ የችግሩን ሥፍራ አላየንም አልነካንም፣ አልወጋንም፤ እንጂ እራሳችንን ማየት ቀርቶብን አይደለም፡፡ እርስ በርስ መገማገም ተጨካክነን እርምጃም መውሰድ ቀርቶብን አይደለም፤ መውጋት ያለብንን ሥፍራ ግን አልወጋንም፡፡ ለዚያ ነው ዛሬ ስራችን ጎዶሎ የሆነው፡፡
መንገድ ላይ የቀረነው ብዙዎቻችን ነን፡፡ ትላንት ያሰብነው ለህዝብ ተቆርቋሪነት አጥተን ረስተን መንገድ ላይ ጥለን ያለፍን አውላላ ሜዳ ላይ የቆምን ብዙዎቻችን ነን፡፡
አንዳንዱ የራሱን ጌታ ፈጥሮ የሚሰግድለት አለ፡፡ ጌታ መፍጠር ለምን ይመጣል? ለምን አስፈለገ? ለምን ተፈለገ?…. ለሰላም ? የድርጅታችን መስመር ይህን ስለሚል? ህዝቡ ይሄን ስለሚፈልግ ???……. አይደለም፡፡ በእርግጥ የድርጅታችን ችግር ነበር ወይ ? አዎን የድርጅታችን ችግር ነበር እውነት ነው፡፡ አንድ የሚያመን ሥፍራ እዚህ ጋር ነበር መደባበቅ ስለሌለብን ነው፡፡ ለምንድን ነው ተመልሰን እርስ በርስ የምንባላው? አንድ ህዝብ ነው ያለን፣ አንድ ሀገር ነው ያለን፣ አንድ አላማ ነው ያለን፡፡ ይህ ከሆነ ለምን እንከፋፈላለን? ለምን እንባላለን? ለምን ደባና ሸር አንደኛችን በሌላኛችን ላይ እንፈፅማለን?”
ምክንያቱ ግልጽ ነው “የህዝባችን ችግር ሳይሆን የግል ጥቅምን የማስቀደም ችግር ስላለ ነው፡፡ ከህዝብና ከሀገር ጥቅም የግል ጥቅምን ማስቀደም ስላለ ነው፡፡ ሌላ አይደለም ! ሌላ ፍች የለውም ! ራስን ማስቀደም ስላለ ነው:: የራስ ጌታ ሲፈጥር ደግሞ በሄደበት ሁሉ ጉልበቱ ይብረከረካል፡፡ ወንበር ላይ መቀመጥ እንፈልጋለን ወንበር ላይ መቀመጥ ለስም መሆን የለበትም፡፡ በተቀመጥንበት ወንበር ላይ ወንበሩ የሚፈልገውን ሥራ መስራት ካልቻልን ወንበሩ የሚፈልገውን ውሳኔ መስጠት ካልቻልን ለስም ወንበር ላይ መቀመጥ ዋጋ የለውም፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓይነት ችግሮች ስላሉብን ነው ከ27 ዓመት በኋላም መድረስ የሚገባን ሥፍራ ሳንደርስ ታግለን ከታገልንለት ህዝብ ጋር የተቃቃርነው ለዚህ ነው፡፡ ለዚህ ነው የተጨካከነው ሌላ አይደለም አሁንም ህዝቡ የመጨረሻ እድል ሰጥቶናል በእውነት ሁሉ ነገር ድኗል ሁሉ ነገር ምላሽ አግኝቷል ሁሉ ነገር አልቆለታል ብለን የምናስብ ከሆነ ሞኝነት ነው፡፡
ራሳችንን ማሞኘት የለብንም ሀገር ሰላም ነው አዎ ሀገር ሰላም ነው፡፡ ግን ሰላም አይደለም፡፡ አጭር ዕድል ነው የሰጠን እንጂ ህዝቡ ሰላም አይደለም፣ እድል ሰጥቶናል የመጨረሻ ዕድል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚሰሩ እንይ ብሎ እድል ሰጥቶናል፡፡ ይህን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በደንብ ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡”
“እንደ ድርጅት፣እንደ መንግስት እያንዳንዳችን ከገባንበት ጓዳ ውስጥ አንገታችንን ይዞ አውጥቶ የፈለገውን ነገር ሊፈጽምብን እንደሚችል እንዲህ አይነት እርምጃ ሊወስድብን እንሚችል አይተናል፡፡በፊልም ሣይሆን በተጨባጭ ውስጥ ኖረን አይተናል ይሄ ቲያትር አይደለም፡፡ ጎበዝ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡
ወዲያና ወዲህ የምናይ ሰዎች ካለን ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ የእኛ ጌታ ህዝባችን ነው፡፡ ለየክልላችን ህዝብ ነው፡፡ ሌላ ጌታ የለንም፡፡ ለሌላ ጌታ መስገድ የለብንም፡፡ ትልቅ ድርጅት አለን 4 ሚሊየን አባላት አሉን፡፡ አራት ሚሊየን ማለት በጣም ትልቅ ነው፡፡ በአለም ላይ አራት ሚሊዬን አባላት ያሉት ድርጅት ውስን ነው፡ እንደነ ቻይና ያሉት ካልሆነ በስተቀር ውስን ነው፡፡ በቁጥር አይደለም እንዲሁ በስም ብንናገር 50 ሚሊየን ህዝብ ነው እኮ ያለን፡፡ ይህን ይዘን ለምን እግራችን ብርክርክ እንደሚል ለምን እንደምንፈራ ለምን ወደ ጓዳ ተመልሰን አንገታችንን ደፍተን እንደምናጉረመርም አይገባኝም፡፡”
“አሁን ያለን ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ደጋግመን ስንል እንደነበረው ማዳመጥ ያለብን ማየት ያለብን ይሄንን ህዝብ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ ሌላ አራማራጭ የለውም፡፡ እንደ ሥራው ክብደትና ድካም እያንዳንዱ ተቀብሎ ይሞክር ብለን አስረክበን ብንወጣም ደስ ይለን ነበር፡ ዛሬ እንደዚህ አይነት ምርጫ አለን? እስቲ ይቅርብን ሌሎችም ይሞክሩት፡፡ ሰባት አመት ሣይሆን 27 ዓመት የለፋንበት ስለሆነ፡፡ አንዳዶችን እንዲያውም ሰውነታችን የዛለ በመሆኑ ፡፡ ሌላው እስኪ ይየው ብለን እንደዚህ መቀባበል ቢቻል እንላለን፡፡ በዚህ መልኩ የተዘጋጀ ነገር ቢኖር ደስ ባለን ነበር፡፡ እውን በዚህ ደረጃ ይህ አለ ወይ ብለን ብንጠይቅ የለም፡፡ ራሳችንን ማታለል የለብንም፡፡ እኛም ደግሞ መሆን ያለብንን ሳንሆን ቀርተን እየተዉረገረግን በመሄድ፣እንዲሁ አስመስለን በመጓዝ ብቻ ረጅም መንገድ መሄድ እንችላለን ወይ ብለን ብንጠይቅ አንችልም፡፡መስቀለኛ መንገድ ላይ ነዉ ያለነዉ፣ራሳችንን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ልናጠፋ ስለምንችል፡፡ ሀገርንም ልናፈርስ እንችላለን፡፡ ሀገር እንደ ድንገት ሲፈርስ ደግሞ አይተናል ሩቅ ሳንሄድ ከጎረቤት ሀገር፡፡ በዕቅድ የሚፈርስ ሀገር የለም፡፡ ስለዚህ ያለን ምርጫ ቆም ብለን አሁንም ደጋግመን ስንል እንደነበረው ጥርሣችንን ነክሰን ከዚህ ህዝብ ጋር ሆነን ለህዝቡ መሥራት ነው ሊያዋጣን የሚችለዉ፡፡
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ 27ኛ የምስረታ በዓልን በማስመልከት በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

የኢትዮጵያዊነት ድምጽ ያስተጋባል #ግርማ_ካሳ




ቴዲ አፍሮን አላውቀዉም ነበር። ከአስራ አራት አመት ስደት በኋላ ወደ አገሬ ተመለስኩ። በ1997 ዓ.ም። መኪናም አልተከራየሁም፤ ታክሲ እየያዝኩ ነበር አዲስ አበባ ዉስጥ የምመላለሰው። ያስተስርያል የሚለው ዘፈን ሚኒባስ ዉስጥ ሲዘፈን ሰማሁ። ከአይኔ እምባ መፍሰሰ ጀመረ። “ይሄ ማን ነው ?” ብዬ ከጎኔ ያለችዋን አንዲት እህት ስጠይቃት “ቴዲ ነዋ” አለችኝ፣ ቴዲ አፍሮን ባለማወቄ በመገረም ቢጤ። ያኔ ከቴዲ አፍሮ ጋር ተዋወቅን።
ክዚያ በኋላ ጥቁር ሰው፣ ሃሌሉያ አበባየሁ(ለአለም) ..ብዙ ጣእመ ዜማዎቹን አደመጥኩኝ። በቀለኞች የሆኑት ሕወሃቶች አስራ ሰባት መርፌ በማለቱ በቂም በቀል፣ ባላጠፋው ጥፋት ለሁለት አመት ወህኒ አወረዱት። እርሱ ግን አልተቀየመም። የአሳሪዎቹና አሰቃዮቹ አለቃ መለስ ዜናዊ ሲሞት፣ የአሰቃዮቹን ስሜት ላለመጉዳት ሲል የሰርግ ቀኑን አራዘመ። መለስ ዜናዊ በመሞቱ፣ ከእጮኛው ጋር ለቅሶ በመድረስ ሃዘኑን ገለጠ። ክፋትን በደግ መመለስ ይሉታል ይሄ ነው።
እነርሱ ግን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት ፣ ስልጣኔ የማይገባቸው ትንሾች በመሆናቸው አሁንም ውስጣቸው በቀል አለ። ሕወሃቶች ከአክራሪ ኦነጎች ጋር በመሆን ኮንሰርት እንዳያዘጋጅ ሆነ ማድረግ የሚፈለገውን እንዳያደርግ መዶለታቸውን አላቆሙም። እርሱ ግን ቀዳዳ አልከፈተላቸውም። የነርሱን ጥላቻ በፍቅር እየመከተ አሁንም የፍቅርን፣ የአንድነትን የኢትዮጵያዊነትን መልእክት ለማስተላለፍ ተዘጋጅቷል።
በቴዲ አፍሮ ዙሪያ ኤርሚያስ ቶኩማ (Ermias Tokuma) ከጦመረው የተወሰነዉን እንደሚከተለው አስቀምጫለሁ። ኤርሚያ ካለው በተጨማሪ አንድ መጥቀስ የምፈለገው ቴዲ አፍሮ ለልጆቹ መልካም አባት፣ ለባሌበቱም መልካም ባል ነው። ለቤተሰቡ ያልሆነ ለአገር ሊሆን አይችልምና።
==============================
ብዙዎቻችን ቴዲ አፍሮን ከሙዚቃ ሥራውና ከሐገር ወዳድነቱ ባሻገር እምብዛም የግል ሕይወቱን እና ምን አይነት ሰው እንደሆነ አናውቀውም እርሱም ቢሆን ስለራሱ ማውራት ስለማይወድ እና ይህንን ፈፀምኩኝ ብሎ ስለማያወራ የቴዲን ማንነት በግልጽ ልናውቀው አልቻልንም ሆኖም ቴዲ አፍሮ እንደዚህም አይነት ሌላ ገፅታ አለው።
★ ሐምሌ 30,1998 ዓመተ ምሕረት በድሬዳዋ ደርሶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ለወገን ደራሽነቱን አሳየን።
★ ጥቅምት 1,2002 Elshaday relief and development ባዘጋጀውና ከ50 ሺህ በላይ በተገኘበት የአዲስ አበባ ስታዲየሙ ኮንሰርት ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስቦ ለእርዳታ ድርጅቱ ያስረከበ ሲሆን በእለቱ ለአበበች ጎበና ሕፃናት ማሳደጊያ 100 ሺህ ብር ለይልማ ገ/አብ የወርቅ ብእር ሸልሟል።
★ ጥቅምት 23,2002 በህመም ላይ ትገኝ ለነበረችው ማንአልሞሽ ዲቦ መታከሚያ ይሆን ዘንድ 20 ሺህ ብር አበረከተ
★ ጥቅምት 17,2004 የወጣት አስመሮም ሃይለስላሴን ነፍስ ለማዳን ለሶማሊያ ሽማግሌዎች 700 ሺህ ብር ከፈሎ የወገኑን ህይወት አተረፈ።
★ ጥቅምት 17,2004 ለኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበር የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎ ለማህበሩ ያለውን አጋርነት አሳየ። ማህበሩም የምስጋና ምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።
★ የአራት ኪሎ ወጣቶች ከአልባሌ ሥፍራ ይርቁ ዘንድ በአባቱ ስም ተቋቁሞ ለነበረው የእግር ኳስ ቡድን ለአራት አመታት በየአመቱ ግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
★ በራሱ አነሳሽነት ለአበበ መለሰ ኮንሰርት በማዘጋጀት የአርቲስቱን ህይወት ከህልፈት ታደገ።
★ ጥቅምት 2005 ቀድሞ ይማርበት ለነበረው ቤቲልሄም ት/ቤት የኮምፒውተር እና የሙዚቃ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።
★በተለያየ ግዜያት በተዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ እንደዚሁም እዛው ድረስ በመሄድ ለወይዘሮ አበበች ጎበና እፃናት ማሳደግያ ከመቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ እርዳታ።
★ ባለቤቱ አምለሰት ባስመረቀችው አረንጋዴ መሬት ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃት ላይ በእንጨት ለቀማ ይተዳደሩ ለነበሩ እናት የ 20ሺብር ቼክ ሰታቸዋል።
★ እንደዚሁም ለተለያዩ ድምፃዊያን ግጥም እና ዜማ በነፃ የሰጣቸውም አሉ::
ይህ ነው የቴዲ አፍሮ ሌላው ገፅታ ይህ ህዝቡ የሚያውቀው ነው ቴዲና ድጋፍ ያደረገላቸው ብቻ የሚያውቁት ብዙ አለ። ቴዲ ከመልካምነቱ በተጨማሪ ጥሩ የፍቅር መምህርም ነው

በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም



በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም።
ዘለቄታነቱ ሳይረጋገጥ የተጨበጨበለት የኢኮኖሚ አብዮት ግቡን ለመምታቱ ምንም ማረጋገጫ የለም።በትግራይ በሕወሓት መሪነት የብረታ ብረት ፋብሪካ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ፋብሪካ፣ የሰፋፊ እርሻ ልማት ሥራዎችና ሌሎች ሲገነቡ ስራ ላይ ሲውሉ ነባር ፋብሪካዎች ሲከስሩ የሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በኦሮሚያና በኣማራ ሲያራግፉ ጥሬ እቃዎችን ሲበዘብዙ የኢኮኖሚ አብዮት አለመባሉ አሁን ላይ ለተከሰተው መደለያ ዘላቂነቱ ታማኝነት የለውም።
ባለፉት ሐያ አምስት አመታት የኢንዱስትሪና ኢኮኖሚ አብዮት ለኦሮሚያና አማራ ክልል ለምን አልታሰቡም ? የሕዝብን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረው የኢንዱስትሪና ኢኮኖሚ አብዮት ቀጣይነቱ ምን ድረስ ነው ? ባለፉት አመታቶች ሕወሓት ከፍተኛ ሐብቶችን ከኦሮሚያና አማራ ክልሎች ሲያሸሽ ኖሮ የውጪ ባለሐብቶችንና ራሱ የቀፈቀፋቸውን የወጥ ብሄር ሰዎችን ሰብስቦ ከፍተኛ ብዝበዛ ሲያካሂድ ኖሮ ድንገት ሕዝቡ ቢነሳ የፈጠረው አዲስ የኢኮኖሚ አብዮት ዜማ አነጋጋሪ ሆኗል።
በሃገሪቱ ብዙሃን ወደ ድህነት የተወረወሩበት ጥቂቶች በዘር ኔትወርክ የከበሩበት የሕዝብ ሓብትና ንብረት አሁንም ገና ከፓርቲ የንግድ ድርጅቶችና ከባለስልጣናቱ እጅ ያልወጣበት ደረጃ ላይ ሆኖ ስለ ኢኮኖሚ አብዮት ማሰብ ራስን ከለውጥ መስመር ላይ ማውጣት ነው።ስልጣን ላለማጣት የሕዝብ ተቃውሞ ለማዳከም የታቀደ ሴራ መሆኡ ሕወሓት በራሱ የፈጠረው ታክቲክ ነው። የኦሮሚያና የኣማራ የኢኮኖሚ አብዮት ጡዘት ተከትሎ ጥያቄ ያነሱት የሕወሓት የሚዲያ ድረገጾች እነትግራይ ኦንላየን የመሳሰሉት አስመሳይ ሚላሳቸውን ሲያሾሉ ቢነሱም የሌሎችን ክልሎች አድገት እንደማይፈልጉ ማሳየታቸው በራሱ የሕወሓትን ተንኮል ያጋለጠ ጉዳይ ነው።
አሁንም ቢሆን በቂ የሆነ ዝግጅት ያልተደረገበት ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ታስቦ የማያውቅ ለደባ የተወጠነ የኢኮኖሚ አብዮት ዘላቂነት የሌለው ባዶ ጩኽትና ኪሳራ ሲሆን በተዘዋዋሪ ለፖለቲካ ዱላ የሚውሉ መንደርደሪያዎችን የሚያመቻች የኢኮኖሚ ጅራፍ ነው። ሕዝቡ እንዳይታለል በንቃት ተከታትለን የሕወሓትን የማጭበርበሪያ ስልቶች ማክሸፍ ይጠበቅብናል። በተጭበረበረ ፖለቲካ የኢኮኖሚ አብዮት ሊገነባ አይችልም። #ምንሊክሳልሳዊ

Wednesday, March 29, 2017

አላሙዲ የመንግስትን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ አልከፈሉም | “መንግስት ገንዘቡን አልቀበል አለኝ” ሜድሮክ

   





ዛሬ በኢትዮጵያ ታትሞ የወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያስነበበው ዜና እጅግ የሚያስገርም ሆኖ አግኝተነዋል:: መንግሥት በሽያጭ ካዘዋወራቸው የልማት ድርጅቶች ውስጥ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ እንዳልተከፈለው የመንግሥት የልማት ደርጅቶች ሚኒስቴር ማስታወቁን የሚዘግበው አዲስ ዘመን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ባለዕዳ የሆነው ሚድሮክ ኢትዮጵያ «አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብሩን ልክፈል ብልም መንግሥት ገንዘቡን ሊረከበኝ አልቻለም» ሲል ገልጿል ሲል አስነብቧል:: ዘገባውን እንደወረደ ያንብቡትና በዚህች ሃገር ውስጥ የሚሰራውን ውንብድና ታዝበው አስተያየትዎን ይስጡበት::
የአዲስ ዘመን ዘገባ እንደወረደ:-
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቲ እንዳስታወቁት፤ ድርጅቶች ከመንግሥት ወደ ግል ሲዛወሩ ከመሸጫ ዋጋቸው ውስጥ 35 በመቶ በመክፈል ቀሪውን ክፍያ በአምስት ዓመት ውስጥ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን እስከአሁን ድረስ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዕዳቸውን ያልከፈሉ ድርጅቶች አሉ። ጠቅላላ እዳቸውም ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ይደርሳል።
በዘንድሮ የግማሽ ዓመት ላይ በተደረገው ግምገማ ዕዳቸውን ካልከፈሉ ድርጅቶች መካከል ሚድሮክ ኢትዮጵያ ሁለት ቢሊዮን ብር ባለመክፈል ከፍተኛው ባለዕዳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሌሎችም ድርጅቶችም ቢሆኑ በውሉ መሠረት ዕዳቸውን ባለመክፈላቸው ወለዱና ቅጣቱ በየቀኑ እየጨመረባቸው ነው ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻም፤ ዕዳ ያለባቸውን ድርጅቶች በአካል በመጥራት ተቋማቸው አነጋግሯቸዋል። በዚህም ድርጅቶቹ ከምርትና ምርታማነት እንዲሁም ከውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ችግር እንዳለባቸው መገንዘብ ተችሏል። ይሄንኑ ችግራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባትም ድርጅቶቹ የተከለሰ ዕቅድ እንዲያቀርቡ በማድረግ ዕዳቸውን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲከፍሉ ድርድር እየተደረገ ይገኛል።
መንግሥት በውሉ መሠረት በህግ አግባብ ድርጅቶቹን ወርሶ በመሸጥ ዕዳውን መውሰድ ቢችልም፤ በድርጅቶቹ የሚሠሩ ሠራተኞችን ስለሚበትንና በሂደቱም አገር ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ስለሚያጓድል የድርጅቶቹ ዕዳ መክፈያ ጊዜ ቢያልፍም በድርድር እንዲከፍሉ ለማድረግ ወደ ድርድር መግባቱን እንደመረጡ ነው ዶክተር ግርማ ያስታወቁት። በድርድሩ መሠረት ዕዳቸውን፣ ወለዱንና ቅጣቱን በማይከፍሉ ድርጅቶች ላይ ግን መንግሥት በህግ አግባብ እንዲከፍሉ ያደርጋልም ነው ያሉት።
በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮንንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ፤ በበኩላቸው ከመንግሥት ወደ ግል የተዛወሩ 29 ድርጅቶች ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ያልከፈሉት ዕዳ አለባቸው ብለዋል።
እንደ አቶ ወንዳፍራሽ ገለጻም፤ ከእዳው ውስጥም ሁለት ቢሊዮን ብሩ በሚድሮክ ኢትዮጵያ በተያዙ ስድስት ድርጅቶች ላይ ያለ ነው። አንድ ቢሊዮን ብር የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ የሌሎች 23 ድርጅቶች ዕዳ ሲሆን፤ በተደረገው ድርድር መሠረት ዕዳቸውን ለሚከፍሉ ድርጅቶች የባለቤትነት ማረጋጋጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል።
ሚድሮክ አለበት የተባለውን ዕዳ አስመልክቶ ምላሽ የሰጡን የሚድሮክ እህት ኩባንያ የሆነው የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ስትራቴጅና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንትና ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ፤ «ድርጅቶቹ ስንረከባቸው የምርታማነት ችግር ነበረባቸው። ምርታማነታቸውን ሳንጨምርና አቅማችንን ሳናጠናክር ወደ ክፍያ ብንገባ የበለጠ ስለምንዳከም የገንዘብ ክፍያው ሊዘገይ ችሏል። የክፍያው መዘግየት ድርጅቱን ቢጎዳውም መንግሥት ግን ተጨማሪ ገንዘብ በወለድና በዕዳ እያገኘ ነው» ብለዋል።
ሚድሮክ በላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪና የቡና ማዘጋጃ ስም ያለበትን አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ዕዳውን ሙሉ በሙሉ ለመክፈል ከመስከርም 2009 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጁ ቢሆንም፤ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ገንዘቡን ሊቀበልና የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሟልቶ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ የጠቆሙት አቶ ይበልጣል፤ በዚህ ምክንያት በድርጅቱ ላይ በየቀኑ ተጨማሪ ገንዘብ እየወለደባቸው መሆኑን ነው ያስታወቁት።
የሌሎቹን ድርጅቶች ዕዳም እስከ ሰኔ 2009 ዓ.ም ድረስ ለመክፈል የጊዜ ሰሌዳ ማውጣታቸውንና ዝግጁ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ይበልጣል፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ለዚህ ዝግጁ ሊሆንና ችግሮቹን አስተካክሎ ማስረከብ እንዳለባት አሳስበዋል።
አጎናፍር ገዛኸኝ

በአሜሪካ ኒውጀርሲ የአራት ወር ነብሰጡር የነበረችው ኢትዮጵያዊት ህይወቷ አልፎ ተገኘ


(አድማስ ራድዮ) ሜሮን ለማ የተባለች የ35 ዓመት ወጣትና የነርሲንግ ምሩቅ ባለፈው እሁድ ማርች 19 ቀን ፣ በምትኖርበት ኒውጀርሲ በሚገኝ አፓርመንት ውስጥ ህይወቷ አልፎ መገኘቱ ተነገረ። አሟሟቷን ፖሊስ እያጣራ ቢሆንም፣ ቤተሰብ በሰው ሳትገደል አልቀረችም የሚል ግምት እንዳለው ይነገራል።
ሜሮን የነርሲንግ ተማሪ እንደነበረችና ብቻቸውን እንዳሳደጓት የሚናገሩት የሜሮን እናት ከኒውጀርሲው ስቶከን ዩኒቨርሲቲ በህዝብ ጤና አጠባበቅ መመረቋንና ከዚያም በነርሲንግ ሙያ ፈቃድ አግኝታ መስራት መጀመሯን ገልጸዋል። አያይዘውም እሁድ አመሻሽ ላይ ፖሊስ ቤታቸውን አንኳክቶ ሜሮን ልጃቸው መሆኗን ካረጋገጠ በኋላ አፓርትመንቷ ውስጥ ሞታ እንደተገኘች እንደነገራቸው እናት ይገልጻሉ። ሜሮን የአራት ወር እርጉዝ እንደነበረች የቅርብ ቤተሰቦች ለአድማስ ሬዲዮ ገልጸዋል።
ፖሊስ እሁድ አስክሬኗን ሲያገኝ ህይወቷ ካለፈ ሁለት ቀን ሞልቶ ነበር። በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስክሬኗን ወደ አገር ቤት ለመላክና የአሟሟቷን ሚስጥር ለማወቅ ፖሊስ የሚያደርገውን ክትትል ለማገዝ የጎ ፈንድ ሚ አካውንት መክፈታቸውን ለአድማስ ሬዲዮ ገልጸዋል። የፍትሃት ጸሎት በመጪው ቅዳሜ ፣ በቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን Memorial service at St. Emmanuel Ethiopian Orthodox Church , 6825 Green way avenue, Philadelphia, Pennsylvania 19142 , starting 9:30am እንደሚደረግም ታውቋል።

የታምፐሬ ዩኝቨርሲቲ ኃይለማርያም ደሳለኝን የክብር ዲግሪ እንደማይሰጥ አስታወቀ፤

    


የታምፐሬ ዩኝቨርሲቲ ኃይለማርያም ደሳለኝን የክብር ዲግሪ እንደማይሰጥ አስታወቀ፤ Muluken Tesfaw
በፈረንጆች አቆጣጠር መስከረም 20 ቀን 2016 በፊንላንድ የሚገኘው የታምፐሬ ቴክኖሎጂ ዪንቨርሲቲ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሚሰጥ ካስታወቀበት ቀን ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን ሲገልጡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ሳምንት ዩንቨርሲቲው ‹‹ለኃይለ ማርያም ደሳለኝ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አንሰጥም›› በማለት አስታውቋል፡፡
የፊንላንድ ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት የስዊድንኛ ቋንቋ የዝግጅት ክፍል ለዩንቨርሲቲው ዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ ‹‹አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በታምፐሬ ዩንቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አይሰጣቸውም›› ሲል ዘግቧል፡፡ የዜና አውታሩ ከዩንቨርሲቲው ተሰጠኝ ያለው መልስ ጠቅላይ ሚንስተር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሽልማት በሚደረግበት ጊዜ መገኘት ስለማይችሉ ነው የሚል መልስ ቢሰጥም የዝግጅት ክፍሉ የራሱን ትንታኔ ሰጥቷል፡፡
የካሊፎርኒያ ስቴት ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም (አልማርያም)ና ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን ዋቢ አድርጎ ‹‹በሽዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችና ኦሮሞዎች እየተገደሉ፣ አገሪቱ በወታደራዊ አገዛዝ ሥር ሆና ከ30 ሺ በላይ ሰዎች በየቦታው ታስረው እየተሰቃዩ ያለበትን አገዛዝ ኃላፊ መሸለም ለአፍሪካውያን ስድብ ነው፤ የፊንላንድ መንግሥትም ለአፍሪካውያን ሰብአዊ መብት ጥሰት በይፋ ድጋፍ እንደሚያደርግ ያሳያል›› በማለት ሰፋ ያለ ሐተታ አስፍሯል፡፡
የዜና አውታሩን የስዊድንኛ ቋንቋ ዘገባ በጎግል ወደ እንግሊዝኛ መልሳችሁ ለማንበብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

የግፍ ዘመናችን ለምን ረዘመ፤ ስለማንነጋገር፤ – ግ. ተ. አበጋዝ



By ሳተናውMarch 29, 2017 06:45



ኢትዮጵያን በባርነት በመግዛት ላይ የሚገኘው የወያኔ መንግስት ላለፉት 26 አመታት ኢትዮጵያን ትልቅ ሀገር ከማለት ይልቅ እንደ ትልቅ እስር ቤት፤ ትልቅ የዘር መጥፋት የሚካሄድባት ሀገር ብሎ መጥራት በሚቀልበት ደረጃ አውርዶ እየገዛት ይገኛል፡፡ በእነዚህ 26 አመታት ውስጥ በአንድ ሀገር ዜጋ ላይ መድረስ የማይገባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፤ ፖለቲካዊ መብት ረገጣዎች፤ መሀበራዊ መብት ጭቆናዎች እና ገድያዎች በኢትዮጵያ ላይ ተፈራርቀውባታል፡፡
በማንኝውም ቦታና ግዜ በየትም አለም የተከሰቱ አምባግነን መሪዎች ከአንድ መሃጸን ውስጥ እንደተፈጠረ ፍጹም መንትዮሸ በድርጊታቸው ይመሳሰላሉ፡፡ አዲስ የተፈጠሩትም አምባገነኖች ታሪክ ሆነው ካለፉት ጨካኞች ብዙ ጭካኔና ግፍን ቀስመውና ልቀው ግፍን ያለገደብ በህዝብ ላይ የፍጽማሉ፡፡ ይህን የግፍና የጭካኔ ዘመን አንጋፋው የፖለቲካ ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ክፉ ቀን ብለው ይጠሩታል፡፡
ፕ/ር መስፍንወልደማሪያም በ 2002 ባሳተሙት አገቱኒ በሚለው መጽሃፋቸው ላይ ክፉ ቀን ብለው በሰየሙት አርእስት ስር ክፉ ቀን ጥሩ ነው የወደቀውን ለድል የጣለውን ለውድቀት ያዘጋጃል፡፡ በመግደል የሚተማመነውን ግዚያዊ ድል ለሞት ይዳርገዋል በሞት ይሸነፋል ተገድሎ የሚያሸንፍ ህዝብ ድሉ የዘላለም ነው፡፡ ክፉ ቀን ጥሩ ነው ክፋት በጎነትን አሸንፎ እንደማይዘልቅ ያሳያል፤ ህግ ቀልቡ ሲገፈፍ ዳኝነት ሚዛን ሲያጣ ጉልበት ሁሉን ደምጦ ሲወጣ የሰውነት ባህሪ ክፉው በጎው ነጥሮ ሲወጣ ያሳያል፡፡ ክፉ ቀን ጥሩ ነው፤ የህዝብን ጥሪ አንድናዳምጥ፤ ከራስ በላይ ንፋስ በሚል እምነት ላይ የቆመውን የግል ኑሮን ማንቆ እንድንበጥስ፤ እንድንተሳሰብ፤ የእድገት ጉዞ እንቅፋቶችን እንድናስወግድ ያሳስብናል፤ ሲሉ የሁሉን ህብረተሰብ ክፍል በሚቆነጥጥ አገላለጽ አስፍረውታል፡፡
ይህንን ክፉ ዘምን ያመጣብንን የህውሀት/ኢህአዴግ ስርአት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል የሁላችንም ሃላፊነት ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮቸ አብላጫውን ድርሻ ይውስዳሉ፡፡ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሃገር ሆና ባታቅም ባለፉተ 26 አመታት ውስጥ ህውሃት በታሪክ አይታ ይማታውቀውን ግፍ እና መከራ በህዝቦችዋ ላይ በመፈጸም አምባገነን መንግስት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህን የግፍ ስርአት ለማስወግድ ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተነጋገሩና እየተደራደሩ ካልሰሩ ብዙ መጉዋዝ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ በሀገራችን ፖለቲካ እንደ እድል ሆኖ ጻድቃን የሚያንሱ ሀጢያተኞች የሚበዙባት ይመስለኛል፡፡
ህውሀት/ኢህአዴግ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ሀገሪቱን ወደ እስርና የስቃይ ማእከልነት ቀይሯታል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎት፤ ባልፉት ጥቂት አመታት ፍጹም ሰብኣዊ ባህሪ በሌለው መልክ፤ ነጻነት ፍትህና አኩልነት ፈልጎ፤ በመላው ሀገሪቱ ለተቃውሞ በወጡ ሰላማዊ ህዝብ ላይ፤ ፍጹም ርህራሄ በሌለው መልክ በታጠቁ የህውሀት ወታደሮች ሲገድል ሲያሰቃይ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍል እየለቀመ፤ ወደተለያዩ እስርቤቶችና ወታደራዊካ ምፖች በማጉዋጉዋዝ ለእስርና ለስቃይ ዳርጉዋቸዋል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎት ምንም የህሊና እና የህግ ዳኝነት ሳያግደው፤ በመዳፋቸው የወደቀውን ህዝብ ጨፍልቆ ለመያዝ ስጋት በገጠማቸው ግዜ፤ በመክላከያ ኢታማዦር ሹም ጅነራል ሳሞራ ዮኑስ (ይህን ሰው በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስማርና በመከላከያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስሰራ አውቀዋልው፤ ፍጹም ዘረኛና ከሱ ዘር ውጪ የሆኑትን የመከላከያ አባል በፍጹም የማያምን አና የሚዘልፍ ነው) እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ የሚመራ የአስቸኩዋይ ግዜ አዋጅ (ኮማንድፖስት) አቁዋቁመው፤ ህዝብን በከፍተኛ ጭንቀት ቀስፎ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አዛውንቶችን እስርቤት አጉርዋል፡፡ ይህ የአስቸኩዋይ ግዜ አዋጅ በከፍትኛ የህውሀት ወታደራዊ አመራሮች እየተመራ በኢትዮጵ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ከተሞችና ገጠሮች፤ የደቡብና የመሀል አዲስአበባን ጨምሮ ህዝብን የማሰር ይመግደልና የማሰቃየት ሀላፊነት የተሰጠው ነው፡፡
በአሁኑ ሰአት መያዣ መጨበጫ ያጣወ የህውሀት/ኢህአዲግ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ ስለተነሳበት የሚያስራቸውና የሚገላቸው ንጹሀን ቁጥር በውል ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን ይህ የወያኔ ድርጊት የሚያሳየው ድርጅቱ ተስፋ መቁረጡን ነው ለዚህ ሁሉ ግፍ ከፋይ አለው አስክፋዩ ህዝብም ራሱን እያዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህም ነው ከላይ የፕ/ር መስፍን ወልደማሪያምን ክፉ ቀን ጥሩ ነው ብለው በመጽሀፋቸው ያስቀመጡትን የጠቀስኩት፡፡ እውነት ግን ለምን የዚህ ግፍ ዘመን በኢትዮጵያ ላይ ረዘመ፤ እንደ ፕ/ር መስፍን ሀሳብ ከሆነ ክፉቀን ወይም አሁን የኢትዮጵየ ህዝብ ላይ እየደረስ ያለው ስቃይ ነገ ላይ የሚመጣው ብሩህ ቀን ጠንካራ መሰረት ይጥላል ባይ ብሆንም፤ የስቃይ መብዛቱና መርዘሙ ያሳስበኛል፡፡ የዚህ ግፍ ዘመን ማጠር የሚያስደስተኝም ቢሆንም ለምን እንደረዘም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘወትር ለውጥን እየተመኘ የተቀመጠ ህዝብ ነው፡፡ ታዲያ ለውጥ ያሻ ህዝብ ለምን የፍላጎቱን አላገኘም፤ ለምን የግፍ ዘመን ረዘመበት፤ እንደረዳት ፕ/ር መራራ ጉዲና ሀሳብ በበርካታ ቁርሾዎች የታጨቀውን የሀገራች የተቃዋሚ ፖለቲካ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ አድርጎ ከፈላጊው ህዝብ ጋር ለማገናኘት የመነጋገር የመወያየት ባህል ሊፈጠር እንደሚገባው ያሳስባሉ እኔም የዚህ ሀሳብ ዋንኛ ተጋሪ ነኝ፡፡ የግፍ ዘመኑም መርዘም ቀዳሚ ምክንያት የመነጋገር የመወያየት እና የመደማመጥ እጥረት ነው ብዬም ለመመለስ እደፍራልው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከኔ በላዬ ላሳር የሚለውን አስተሳሰብ ጥሎ ከአንድ ሁለት እንደሚሻል አምኖ በጋራ መስራትና፤ ያንተ ሆድ ስለሞላ ሌላው አልራበውም አለማለት፤ እና የችግሩ መፍትሄ ባትሆን እንኩዋን፤ እንቅፋት አለመሆን የምንመኘውን ነጻነት ሊያጎናጽፈን ይችላል፡፡
ግ. ተ. አበጋዝ፤ መጋቢት፤ 2009፤ ሳስካቱን፤ ካናዳ

ወያኔ ጠላቴ ነዉ ያለዉ አማራን እንጅ ኢትዮጵያን አይደለም::አንተ ከዬት አምጥተህ ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያም ጠላት ነዉ እያልክ የምትጽፈዉ?


ሸንቁጥ አየለ
——-
ጥያቄ:-
ወያኔ ኢትዮጵያ ጠላቴ ናት ብሎ አልተነሳም::ኢትዮጵያ ጠላቴ ነች ሲልም አልተደመጠም:: የተነሳዉ አማራ ጠላቴ ብሎ ነዉ::አንተ ግን ወያኔ ኢትዮጵያን ጠላቴ እንዳለ አድርገህ ትጽፋለህ እሳ ? ይሄን ከዬት አምጥተህዉ ነዉ? የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይመጣልኛል:: በተለይም በመደብ ትግል የሚያምኑ በመደብ ትግል ይወድማሉ ከሚለዉ የሰሞኑ ጽሁፌ ጋር ተያይዞ ይሄ ጥያቄ ደጋግሞ እየመጣ ነዉና መልስ ይፈልጋል:: እናም ወደ ጥልቁ ገብተን እዉነታዉን እየቀዳን እንነጋገር::ላይ ላዩን ሳይሆን::ጭብጡን ይዘን እናዉጋ::
የወያኔ ሙሉዉ መርህና ፍልስፍና ባጭሩ በሚከተሉት አምስት ነጥቦች ሊጠቀለል ይችላል:-
1. ክህደት አንድ እና የጠላትነት ምሰሶዉ:-
ወያኔ ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ/የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ/ ብሎ ሲነሳ የመጀመሪያዉ በጠላትነት የተፈረጀዉ ኢትዮጵያን ነዉ::ዋናዉ ግብ ከኢትዮጵያ ነጻ መዉጣት ነዉ::የዚህ ነጻነት ዋና አስፈላጊነትም ኢትዮጵያ በጠላትነት ትግራይን ይዛዋለች የሚል ታሳቢ ነዉ::በራሳቸዉም ሰነድ “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቆና እና ባርነት ነጻ ካልወጣ” ህልዉናዉ አይረጋገጥም ሲሉ አዉጀዉ በሰነድ ጽፈዉ ነዉ የተነሱት::ወያኔዎች ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ በግልጽ አቋማቸዉን ያስቀመጡት ኢትዮጵያ የምትባል የመቶ አመት ታሪክ ያላት እና በወራሪዉ ምኒሊክ የተፈጠረች ሀገር የትግራይን ህዝብ ታሪክ ነጥቃ እና ክብሩን አዋርዳ ባርነት ዉስጥ አስቀምጣዋለች ብለዉ ያትታሉ::የብስራት አማረን የህዉሃት ገድል እና የራሱን የወያኔን ማኒፌስቶ ማንበብ በቂ ነዉ::በነሱ ትረካም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚባል የለም::ኢትዮጵያ የምትባል ወራሪ ሀገርም የለችም:: ወራሪዉ ሚኒልክ ጠፍጥፎ የሰራዉ ነገር ነዉ እንጅ:: እናም ኢትዮጵያ የሚለዉ ስም መደምሰስ ያለበት ነዉ:: ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ከዚህ በላይ ጠላትነት ምን አለ?ከጥንት ጀምሮ በመጽሀፍ ቅዱስ ሳይቀር የሚታወቀዉን ሀገር ክዶ ከመነሳት የከፋ ሀሰት እና ጠላትነት ከወዴት አለ?
2. አማራ የገዥ መደብ – የትግራይ ህዝብ ጠላት
ወያኔ ሁለተኛዉን የትርክት ምሰሶዉን ያቆመዉ በአማራ ህዝብ ላይ ነዉ::በወያኔ ትንታኔ አማራ የሚባለዉ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህልዉና የበለጠ ተጠቃሚ በመሆኑ የሌለችዉን ኢትዮጵያ እንዳለች በማስመሰል ይተርካል::ስለዚህም የትግራይ ህዝብ አማራን ሊዋጋዉ እና አማራ የሰራትን ኢትዮጵያ ሊያፈራርስ ይገባዋል::ወያኔ አሁንም ዋና ማጠንጠኛዉ አማራን ማንበርከክ: አማራን ማጥፋት እና አማራን ማሸነፍ ብሎም ኢትዮጵያ ከምትባል የጭንቆና ቀንበር ነጻ መዉጣት የሚል ታሳቢ ነዉ::
በወያኔ ትረካ መሰረትም የአማራ እና የኢትዮጵያ ትስሥር በብስራት አማራ (የህዉሃት ገድል መጽሀፍ ) እንደሚከተልዉ ቀርቧል::” አማራ ባሪያ ህዝብ ነዉ::ይሄ ባሪያ ህዝብ ከሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ባሪያ ህዝቦች ጋር ( ማለትም ከኦሮሞዎች: ከሲዳማዎች: ከጉራጌዎች እና ከሌሎችም) እየተቀላቀለ እና እየተቀየጠ ኢትዮጵያ የምትባል የዉሸት ሀገር ፈጥሯል::ይሄ አማራ የሚባል ህዝብ በምንም መልኩ የሰለሞን ነገስታት ዘር አለኝ የሚለዉ ሀሰት ነዉ::ምክንያቱም አማራ ባሪያ ነዉ እየተቀየጠ እና እየተቀላቀለ ያለዉም ከባሪያዎች ጋር ነዉ::” ብስራት አማረ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዴት እንደሚጠላዉ እና የህዉሃት የፖለቲካ ፍልስፍና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን እንደሚመስል ለማወቅ የፈለገ ሰዉ የብስራት አማረን መጽሀፍ ያንንብብ:: በብስራት አማረ መጽሀፍ ዉስጥ አማራ የበለጠ የተሰደበ እና የተረገመ ሆኖ ቢገኝም ዋናዉ ግብ እና አላማ ግን አማራዉ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በዉህደት የፈጠራት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርን የለችም : መጥፋት አለባት: ባሪያዎች ተሰባስበዉ ሀገር ሊመሰርቱ አይገባም የሚል ታሳቢ ነዉ::
አንዳንዱ ደንቆሮ ህዉሃት ስለ ብሄር እኩልነት ስታስጨፍረዉ እዉነቷ እየመሰለዉ አብሮ ይዘላል:: አንዱን ብሄረሰብ በሌላዉ ላይ ስታስነሳ እዉነት እየመሰለዉ በወንድሙ ላይ ሰይፍ ይመዛል:: የህዉሃት ፍልስፍና ግን በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የጠላትነት ስነልቦና ነዉ::ሌላዉ ቀርቶ እንደ ዋለልኝ አይነት የአማራ ልጆች አማራን በህዉሃት ፍልስፍና (ከአባታቸዉ ከሻቢያ እንደተማሩት) የኢትዮጵያ ጠላት ነዉ : የብሄር ብሄረሰብ መብት የተረገጠዉ በአማራ ህዝብ ነዉ በሚል የፈጠራ ታሪክ ሲከሱት የነበረዉ የጠላትን የተራቀቀ ሚስጥርን ካለመረዳት ነበር::
የኢትዮጵያዉያንን ማህበረሰብ እና ብሄረሰቦችን እኩልነት የዲሞክራሲ እና ሰበአዊነት መብት ለማወጅ ኢትዮጵያ መዉደም የለባትም::ህዉሃት : ሻቢያ እና ከነሱ የተማሩት እነ ዋለልኝ ግን የተቀኙት ኢትዮጵያን በመደምሰስ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥ ወራሪዋን ኢትዮጵያን ማፍረስ በሚል ቅኝት ነበር:: ይሄ ሁሉ የተንኮል ትርክትም ሻቢያ እና ወያኔ የሚያልሙትን ነጻነት ለመቀናጀት እንዲያስችላቸዉ የተጎነጎነ ሲሆን እነዋለልኝ የሚባሉት መናጆዎች ደግሞ በገልቱነት የተጎነጩት መርዛማ አስተምሮት ነበር::
በዚህ ሂደትም ዉስጥ የበለጠ ይሄን እዉነት ይጋፈጥብኛል: ይቃወመኛል ብላ ያሰበችዉ አማራ ላይ ወያኔ የዘር ማጥፋት በራሷ እና በሌሎች ብሄሮች እንዲክከናወን ሰፊ የቤት ስራ ሰርታለች:: አማራዉን በአንድ በኩል ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ጨፍልቃ ባሪያ ነዉ: ከባሪያ ጋር ይጋባል: በዉህደትም ኢትዮጵያ የምትባል የሀሰት ሀገር መስርቷል እያለች የምትወቅሰዉ ወያኔ በሌላ በኩል ደግሞ አማራዉን በሌሎች ብሄሮች ለማስጠላት ሰፊ የቤት ስራ ሰርታለች::እየሰራችም ነዉ::ወያኔ ግቧን በአንድ አቅጣጫ አታከናዉንም::በብዙ መልክ እና መስክ እንጅ::
3. ወያኔን ከተቃወምክ ከየትኛዉም ብሄር ብትሆን ያዉ የወያኔ ጠላት ነህ
እዚህ ጋ የኦሮሞ ማህበረሰብን ጉዳይ እንደ ማሳያ ማንሳቱ ተገቢ ነዉ:: ሶማሌን እና የጋንቤላን ማህበረሰብም እንደ ማጣቀሻ ማቅረቡ ጥሩ ነዉ::ወያኔዎች ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻ ብቻ ሳይሆን አንግበዉ የመጡት የተሳሳተ ሀሳብንም አንግበዉ ነዉ የመጡት::ለምሳሌ አማራን በቀንደኛ ጠላትነት ፈርጀዉ የዘር ማጥፋት እንዳወጁበት ሁሉ የኦሮሞን ማህበረሰብ እያታለሉ እንዳሰኛቸዉ የሚያቄሉት እና የሚገዙት መስሏቸዉ ነበር::ከወያኔዎች ይልቅ ፕሮፌሰር ሌቪይ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ የስነልቦና አንድነት በደንብ ያዉቃል::ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪይ ታላቋ ኢትዮጵያ የብዙሃን ሀገር በሚለዉ መጽሀፉ እንደተረከዉ ኦሮሞዎች እና አማራዎች ስልጣንን: ጦርነትን: ባህል እና ታሪክን በተመለከተ አንድ አይነት ስነልቦናዊ ይዘት አላቸዉ::ባህላቸዉም አንድ ነዉ ሲል ያትታትል:: ሲቀጥልም ሁለቱም ወገኖች ጥሩ ጦረኞች ናቸዉ ሢል ያብራራል::ዶናልድ ሌቪይ እንደሚተርከዉም ኦሮሞዎችም ሆኖ አማራዎች ሰላማዊ እና ሌሎችን አክብረዉ መኖር የሚችሉ ታላቅ ህዝቦች ናቸዉ:: ከነኳቸዉ እና ካጠቋቸዉ ግን ለክብራቸዉ የሚዋደቁ ጦረኞች ናቸዉ::
ወያኔ ግን ይሄን እዉነታ ክዳ የኦሮሞ ህዝብን እንዳሰኛት እንደምትጫወትበት በማሰብ እና እንዳሰኛት ለማሞኘት ብዙ ጥራለች::ሆኖም እዉነታዉ ወዲያዉ ነዉ የተገለጠዉ::ኦነጎች ያነገቡት ኢትዮጵያን የማዉደም ፍልስፍና ሸዉራራ ቢሆንም ወያኔን መቃወም እና ወያኔን ቁም ስቅሏን ማሳዬት የጀመሩት ወያኔ ገና ስልጣኗን በአግባቡ ማደላደል ሳትጀምር ነበር::ከዚያ ብኋላ ላለፉት ሀያ አምስት አመታታ ሙሉ የኦሮሞ ተቃዉሞ በወያኔ ላይ እንደነደደባት ነዉ::ኦሮሞዎች በሰላማዊ ትግልም ሆነ በጦርነት: በልዩ ልዩ ፓርቲም በመደራጀት ወይም ከራሷ ከወያኔ መዋቅር ዉስጥ ተሰግስገዉ በመግባትም ቢሆን ወያኔ እንዳሰበችዉ የማንም መጫወቻ እንዳልሆኑ አስመስክረዋል:: ወያኔም በመጨረሻ ይሄ እዉነታ ሲገለጥላት የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ ማሰር: መግደል እና ማፈናቀል ይዛለች:: የወያኔ የበቀል በትር በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከተመዘዘ ብኋላ በአንድ ቀን እንኳን ከሽህ በላይ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላትን በመግደል (ያዉም የሀይማኖት ክብረ በአል ላይ) ጠላትነቷን አስመስክራለች:: ወያኔ አሁን በምስራቅ ኢትዮጵያ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ላይ የማፈናቀል እና የማሰቃዬት ስራዋን ተያይዛዋለች::
በተመሳሳይ ወያኔን የሶማሌ ማህበረሰብ ሲቃወማት የተወሰደበት የጅምላ የዘር ማጥፋት እርምጃ አሰቃቂ ነበር:: አሁን ወያኔ አንዱን የሶማሌ ጎሳ መርጣ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ደም እያቃባችዉ ነዉ::በዚህም ወያኔ ጥንድ ትርፍ ታተርፋለች::በአንድ ሰይፍ ኦሮሞና ሶማሌ እንዲጫረስ ስታደርግ በሌላ ሰይፍ ደግሞ ወያኔ ገላጋይ ሆና ስልጣኗን አደላድላ ኢትዮጵያን መበዝበሯን ትቀጥላለች:: የወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላትነት በዚህ አይበቃም::የጋምቤላን ማህበረሰብ ሆን ብላ እሁለት ከፍላ አኝዋኮች ላይ ይሄ ነዉ የማይባል የዘር ማጥፋት እርምጃ ወስዳባቸዋለች::ይሄ ሁሉ እጅግ ብዙ መራራ እዉነት እያለ ይሄን ሁሉ የህዝብ ጠላትነት መካድ አይቻልም::ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና ብሄረሰብ ጠላት ናት::
4. ኢትዮጵያ :- የወያኔ ጋለሞታ
አንዳንድ ሰዉ ዝም ብሎ ላይላዩን እንዳዬ እድሜዉን ይገፋዋል::አሁን ወያኔ ኢትዮጵያን ወራ ይዛ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር የምትመራ የሚመስለዉ ሰዉ አለ:: ወይም ይሄ ሁሉ ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ላይ የሚወርደዉ መከራ በኢትዮጵያ የሚፈጸምበት የሚመስለዉ ሰዉም አለ:: እዉነታዉ ግን እንደሱ አይደለም::ኢትዮጵያን ወያኔ እንደ ጋለሞታ ነዉ የማረከቻት::በወያኔ ልብ ዉስጥ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር የለም::ኢትዮጵያ የምትባል ጋለሞታ እና በጊዚያዊነት የተማረከች የጠላት ሚስት ግን አለች:: ወያኔ ኢትዮጵያን ሀያ አምስት አመት በቅኝ ሲገዛት አሁንም የትግራይ ነጻ አዉጭ ሆኖ ነዉ::አሁንም በልቡ ወያኔ የሚያልመዉ ከዚህች ከጋለሞታ ኢትዮጵያ ትግራይን ነጻ ማዉጣት ነዉ::ወያኔ ለዚህም ነዉ የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ የሚለዉን ስሙን የማይለዉጠዉ::የወያኔ ግቡ ኢትዮጵያ አይደለም::ኢትዮጵያ የጠላት ሚስት ናት::ምናልባት የተገደለዉ የኢትዮጵያ ባል መቃብሩን ፈነቃቅሎ የተነሳ እንደሆነ ወይም ምናልባትም የተገደለዉ የኢትዮጵያ ባል ልጆች ወልዶ ከሆነ እና ኢትዮጵያ የሚል መዝሙር ከተነሳ ወያኔ ኢትዮጵያን አዉድሞ ትግራይን ነጻ አዉጥቶ ይሄዳል::ከዚህ የከፋ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላት በምድር ላይ የለም::ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነዉ::በገሃድም የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ያወጀ ሀይል ነዉ::
5. አሁን የተነሱት እና እናታቸዉ የተማረከችባቸዉ የኢትዮጵያ ልጆች ምን እያሉ ነዉ?
ወያኔ በጠላትነት የማረካትን እና በጋለሞታነት በጉልበት የያዛትን ኢትዮጵያን አብረዉ የሚራገሙ ፈሪዎች ተነስተዋል::የአባታቸዉን ሀገር እና የአባታቸዉን ሚስት ከወራሪዉ እና ከጸረ ኢትዮጵያዊዉ ወያኔ ማላቀቅ ሲገባቸዉ ብሎም ክብሯን መመለስ ሲገባቸዉ እናታቸዉን ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ እያሉ እየሰደቧት ነዉ::ወያኔን እንጅ እናታቸዉ ኢትዮጵያን ማስተዋል የተሳናቸዉ ፈሪዎች ወያኔን ለማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት የሚል ፍልስፍና ታጥቀዋል::ቤቴ በትኋን ተወሯል እና ቤቴን አቃጥለዋለሁ ይሉሃል::ከዚያስ ? ስትላቸዉ ከዚያ እማ እፍርስራሹ ላይ ትንንሽ ጎጆዎችን አቆማለሁ ብለዉህ ቁጭ:: የተሰራዉን ቤት ከወራሪ ማላቀቅ ያቃተዉ ፈሪ ቤት አፍርሼ ቤት እሰራለሁ ይልሃል:: ይሄ መታመም ነዉ::ይሄ ፍርሃት ነዉ:: ይሄ አለማስተዋል ነዉ::
እግዚአብሄር እራሱ ኢትዮጵያዊነትን ልጄ ያለዉ ቅዱስ ነገር ነዉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉን ማንነትህን መልቀቅ ወደ መጨረሻዉ የመሸነፍ ጠርዝ መሄድ ብቻ ሳይሆን ወደ ሽንፈት እንጦርጦሮስ መዉረድ ነዉ ብለህ ብትነግራቸዉ እግዜር እራሱ የለም ይሉሃል::ወይም ጠላት እንደነገራቸዉ መጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለዉ ኢትዮጵያ ይሄ አሁን ያለዉ ኢትዮጵያ አይደለም ብለዉህ ቁጭ::እንዴታ ? ገና መጽሀፍ ቅዱስ ትርክቱን ሲጀምር የግዮን ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከባል ብሎ የሚያስረግጠዉ እኮ ይህችኑ የኛኑ ቅድስት ኢትዮጵያን ነዉ የተባሉ እንደሆነ ይከፋሉ::ወይ በቂ እዉቀት ወይም በቂ ወኔ ያስፈልጋል::አጼ ቴዎድሮስ 179 አመታታ በመሳፍንት ተረጋግጣ እና ተከፋፍላ የነበረች እናት ኢትዮጵያን ሊያድኗት ፎክረዉ ሲነሱ “የኢትዮጵያ ባል : የእየሩሳሌም እጮኛ” ብለዉ መፎከራቸዉን እና ኢትዮጵያን እነ ራስ ስሁል ከበተኗት ብኋላ በብዙ ድካም ሊሰበስቧት ብዙ ዋጋ ለመክፈል ጀግኖች እንደነበሩ ያስታወስካቸዉ እንደሆነ አንዳንዱ ያኮርፋል:: ጥሬ ሀቁ ግን አጼ ቴዎድሮስ እና ሌሎችም የአለም ጀግኖች እንዳደረጉት ጠላት በሀይል እና በእዉቀት ብቻ ይነቀላል እንጅ አገር አጠፋለሁ : ድንበር አፈልሳለሁ ተብሎ ስለ ተፎከረ አይጠፋም::
ይልቅ እናት ኢትዮጵያን ከጠላቷ ከወያኔ ማላቀቅ እና የተከበረች ሀገር ማድረግ ብቸኛዉ መፍተሄ ነዉ::ጀግና አባቶች የገነቡትን መሰረት ወደ ታላቅ መሰረትነት ማሸጋገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነዉ::ለጊዜዉ በብሄሬ ተደራጅቼ ወይም በኢትዮጵያዊነት ተደራጅቼ ወያኔን እንደመሰለኝ እፋለማለሁ ማለት መብት ነዉ::ግን ጥቂት ነገር መሳት ነዉር ነዉ::አንደኛ ወያኔ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት መሆኑን መካድ ነዉር ነዉ::ሁለተኛም ኢትዮጵያን ከወያኔ ማላቀቅ ሲገባ ኢትዮጵያን አጥፍቼ ነዉ ወያኔን የማጠፋዉ ብሎ መነሳት ነዉር ብቻ ሳይሆን ስንፍናም ነዉ:: ሶስተኛም ወያኔ የዚህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ጠላት መሆኑን በገሃድ እየተናገረ እና እያስመሰከረ ወያኔን የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ማለት ታላቅ ሀሰት ነዉ::
ወያኔ የኢትዮጵያ እዉነተኛ ጠላቷ ሲሆን ይሄ እዉነታም ሲመነዘር ወያኔ የአማራዉም: የኦሮሞዉም : የጉራጌዉም : የሶማሌዉም: የደቡቡም : የአፋሩም የሁሉ ኢትዮጵያዊ መሰረታዊ ጠላት ነዉ::ስለሁለት ነገር::አንድም ማንም ወያኔን ተቃዉሞ ቢነሳ ወይም እንደሚቃወም ወያኔ እርግጠኛ ከሆነ የሚደርስበት ድምሰሳ አንድ ነዉ::አንድም ኢትዮጵያን ወያኔ ድምጥማጧን አጥፍቶ ሲያፈርሳት የሚፈጠረዉ ትርምስ አሁን አንዳንዶች ቁጭ ብለዉ እንደሚያስቡት አንድን ወገን የሚጎዳ ሳይሆን መላዉ ኢትዮጵያን ወደ ፍጹም ሲኦልነት የሚከት እና መሰረታዊ ትርምስ የሚያመጣ ነዉ::በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጎጅ ነዉ::ወያኔም የሚፈልገዉ ይሄንኑ ነዉ::ከዚህም የከፋ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላትነት ከቴም የለም:: በታሪክ ከተመዘገቡት የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ሁሉ የከፋዉ ጠላት ማለት ይሄ ሀይል ነዉ::

አማሮፎቢያ (መቀሉ አየለ)




እኒህ ትምህርት ጠልተው አሮጌ ጠመንጃ ይዘው በረሃ ያደጉ መደዴ ፍየል ጠባቂ ሁሉ፤ በቁጥር ሰላሳ ያህል ሆነው ዋሻ ውስጥ ሳሉ በአንድ ሻለቃ የደርግ ጦር ድንገት ቢከበቡና መውጫ ቢያጡ ለቀናት ያህል ያለ በቂ ምግብ መቆየታቸው የተነሳ የሚበሉት አልቆ ጠኔ ሲይዛቸው እርስ በእርሳቸው የተበላሉ በላዬ-ሰብዕ መሆናቸውን በማስረጃ ተደግፎ ወጥቶ አንብበናል።የዘመን ተውሳኮች ተባይ እንደወረሳቸው እንዲሁ ያለ መጫሚያ ወደ መሃል አገር ሲዘልቁ “አማራ ጠላት ነው” ከምትል አንዲት ቃል ሌላ የሚያውቁት ምንም ነገር አልነበራቸው። ዛሬ ገንዘብ መዝረፍ ብቻ ሳይሆን ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ የተገዛ “የትምህርት ደረጃ” ከስማቸው አጠገብ ለጥፈው መኖራቸው በውስጣቸው የሚሰማቸውን የበታችነት ቁስል ሊያክላቸው አልቻለም። እነርሱ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ተቀምጠው አንድ ጎጃሜ ሎተሪ አዙዋሪ መጥቶ ትኬት ሲሸጥላቸው የሚያሳይ ፎቶግራፍ ወደ ህዝቡ በመርጨት እንደ ገደል ማሚቶ ተመልሶ ለራሳቸው የሚያስተጋባ ተራ ፕሮፓጋንዳ ከመሆን ባለፈ በማንኛውም ጤነኛ ዜጋ ላይ ቅንጣት ታህል ነጥብ የማያስቆጥር የወረደ “ጀብዱ” በመስራት “እኛም በዘመናችን እንዲህ ነን” ለማለት ሞክረዋል። እውነታው ግን ስር በሰደደ የበታችነት ነቀርሳ የሚሰቃዩ መሆናቸውን በአንክሮ ማረራገጡ ነው።አንዳርጋቸው ጽጌን የመሰለ የዘመናችን ቸኮቬራ ማንበርከክ የተሳናቸው ድውያን የውርደታቸው ልክ መጨረሻ ቢያጣ ነው እንዲህ ሲሆኑ የምናያቸው። 
በ 77 ዓ/ም ድርቅ ከአንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን እልቂት ጀርባ፣ ከእነዚያ የገዛ ቆዳቸው ከሰፋቸውና ከሰለሉ እጆች ጀርባ ለአለም የተገለጠው እውነት ያ-ኩሩ! የወሎ ገበሬ እንኩዋን እንደ ደደቢት በላየሰቦች የሰውን ስጋ ሊበላ ቀርቶ እርም ነው የሚለውን የአህያውን ስጋ አልሞከረውም፤ ይልቁንም በወተቷ ልጆቼን ያሳደገች ላም አንገት ላይ እንኳን ሳይቀር “ቢላዋዬን አሳርፍ ዘንድ የአባቶቸ አምላክ፤ የአምላከ እስራኤል እርግማን፤ በእኔ ላይ የለም” እያለ ከከብቶቹ በፊት ወደ መቃብር መወረዱ ነበር።

የማጠቃለያው እውነት ደግሞ በምንም መመዘኛ በእዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት, የለበሱት የሃር ከረባት የማያደምቃቸው፣ የደረቡት የሱፍ ኮት የማያሞቃቸው፣ የተጣበቁበት ዙፋን ምቾት የማይሰጣቸው ድውያን አንድ ላይ ቢሰፈሩ የዚህን አንድ ኩሩ ጎጃሜ የመንፈስ ልዕልና ጫፍ ላይ የማይደርሱ መሆናቸውን ነው። ዛሬም በራሱ የሚኮራ፣ የአቸናፊነትን ስነ ልቦናን የታደለ፣ ከማንነት ወደ ሰውነት ደረጃ ያደገ ኩሩ ፣ባለችው እረክቶ የሰላም እንቅልፉን የሚተኛ፣ከራሱ ጋር የታረቀና ለራሱ ክብር ያለው ባለታመብ ነው። በዚህ ሁሉ እርብርብ ውስጥ አልሰበር ያለውን ይኽን የሞራል የበላይነት ነው እንግዲህ ይኽ ወራዳ ስርዓት “ትምክህተኝት”፣ “ነፍጠኝነት” እያለ የሚፈርጀው።
 

የአባይ ጸሐዬ መስሪያ ቤት ጥናት እጅጉን አስቂኝ መሆኑ ተገለጸ




ፈላጭ ቆራጭ ከሆኑት የህወሓት ባለስልጣናት መካከል አንዱ በሆኑት አቶ አባይ ጸሐዬ ዋና ዳይሬክተርነት የሚመራው የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ‹‹አካሔድኩት›› ባለው ጥናት ላይ፣ ‹‹የአስፈጻሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ዋነኛ ማነቆ ነው፡፡›› ሲል አስቂኝ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ዴሞከልራሲዊ ስርዓት እንዳይሰፍን ማነቆ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የአስፈጻሚ አካላት ጣልቃ ገብነት መሆኑን የገለጸው የአቶ አባይ ጸሐዬ ተቋም፣ ራሱን ከችግር ፈጣሪነት ማንጻቱም ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በስርዓቱ ውስጥ የአዛዥነት ስፍራውን የተቆናጠጠው ህወሓት፣ በወህኒ ቤቶች፣ በፖሊስ ጣብያዎች እና በመሰል አስፈጻሚ አካላት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የፈለገውን ዓይነት ውሳኔ እንደሚወስን ይታወቃል፡፡
ከጄነራል እስከ ገራፊ ድረስ ህወሓቶች በተቆጣጠሩት ስርዓት ውስጥ ጥናት አካሔድኩ ብሎ የተሳለቀው የአቶ አባይ ጸሐዬ ተቋም፣ ጣቱን ወደ ሌሎች በመቀሰር በሀገሪቱ ላይ እና በህዝቧ ላይ ከተፈጸሙት በደሎች ራሱን ለማንጻት መጣሩ እንዳስገረማቸው ጥናቱን የተከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡ የሀገሪቱ ቁጥር አንድ ችግር ፈጣሪ የሆኑት አቶ አባይ ጸሐዬ፣ መልሰው ራሳቸው የመፍትሔ ጥናት አጥኚ በሆኑበት ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ለውጥ ሊመጣ እንደማይችልም ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡ እንደ ህወሓት በአስፈጻሚ አካላት ስራ ጣልቃ የሚገባ እንደሌለ የሚገልጹት እነዚሁ ታዛቢዎች፣ የህወሓት አጃቢ የሆኑት ብአዴን እና ኦህዴድ ደግሞ ለህወሓት ጣልቃ ገብነት መሳሪያ መሆናቸውን ታዛቢዎቹ ያክላሉ፡፡
‹‹ምክር ቤቶች፣ መገናኛ ብዙኃን እና የሕዝብ ማኅበራት መብቶቻቸውን በተቀመጡ ህጎችና በህገ-መንግሥቱ መሰረት የመጠየቅና ፊት ለፊት መጋፈጥ ላይ ክፍተቶች አሉባቸው፡፡›› ያሉት አቶ አባይ ጸሐዬ፣ የተጠቀሱት አካላትም ሆኑ ሌላው ማኅበረሰብ መንግስትን ፊት ለፊት ያለመጋፈጥ ችግር እንደሚስተዋልበት ተናግረዋል፡፡ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች መንግስትን ፊት ለፊት የተጋፈጡ ተቃዋሚዎች፣ ግንባራቸውን በጥይት ተመትተው በተገደሉበት ሀገር፣ አቶ አባይ እና ጥናታቸው አስመሳይነታቸውን ከማሳበቅ በቀር ፋይዳ እንደሌላቸው አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ ጋዜጠኞች መንግስትን ለምን ተቻችሁ ተብለው 18 ዓመት በሚፈረድባቸው ሀገር ውስጥ፣ ስለ መገናኛ ብዙኃን ደካማነትም አቶ አባይ ተናግረዋል፡፡ ነጻ ሚዲያ በሌለበት ሀገር ውስጥ ሚዲያዎችን የወቀሰው የአቶ አባይ ጥናት አስቂኝ ሆኗል፡፡
ከህዝባዊ ተቃውሞ ወዲህ ሁሉ ነገሩ የተመሳቀለበት ህወሓት፣ የተበላሸውን ለማስተካከል ጥረት እያደረገ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሆኖም ነገሮች እንደቀደመው ጊዜ ሊሔዱለት አለመቻላቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በጥናት እና በመሰል ጉዳዮች ሌሎችን በመውቀስ ራሱን ለማዳን ጥረት ሲያደርግ የሚስተዋለው ህወሓት፣ እንደለመደው የተወሰኑ ባለስልጣናትን ዞር በማድረግ ቆዳውን ገልብጦ ለመምጣት የሞከረባቸው አጋጣሚዎች ብዙ መሆናቸውን የሚገልጹ ወገኖች፣ ዘንድሮው የተጋፈጠው ተቃውሞ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደከበደው እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ፡፡