Saturday, December 3, 2016

የአየር ወለዱ መሃንዲስ ሜጀር ጄነራል ደምሴ ቡልቶ


Eyob Zeleke's photo.
የአየር ወለዱ መሃንዲስ
ሜጀር ጄነራል ደምሴ ቡልቶ
/በኢዮብ ዘለቀ/
በወርሃ ነሐሴ 1953 ዓ.ም፤ አስራ ዘጠኝ ሰዎችን ያሳፈረውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ዲሲ 3 አውሮፓላን በበረራ ላይ እንዳለ በቀድሞው አጠራር በየረርና ከረዮ አውራጃ ፤ዳለቻ በሚባል ስፍራ ላይ ተከሰከሰ፤ አውሮፓላኑ ወድቋል የተባለበት ስፍራ ለነፍስ አድን ስራ የሚመች ባለመሆኑ አየር ወላዶችን በዚህ ስፍራ ላይ በፓራሾት ማውረድ ግድ ሆነ ፤ አየር ወለዶቹ በዚህ የነፍስ አድን ስራ ላይ በመሰማራት የብዙዎችን ተሳፋሪዎች ህይወት ለማዳን ቻሉ ፤ በዚህ ካባድ ግዳጁ ላይ በመሰማራት የወገንን ህይወት ከታደጉልን አራት የአየር ወለድ አባላት መሃከል የያኔው የመቶ አለቃ ደምሴ ቡልቶ የኃላው ሜጄር ጆነራል ደምሴ ቡልቶ አንዱ ነበሩ ።
ከቢልቻ ወንዝና ፎየታ ተራራ በስተጀርባ፤ ሙገር አካባቢ በምትገኘው ገጠራማ ቀበሌ በ1926 ዓ.ም የተወለዱት ስመጥሩ የአየር ወለዱ መሃንዲስ ሜጀር ጀነራል ደምሴ ቡልቶ ከልጅነታቸው አንስቶ ወታደር የመሆን ምኛት ነበራቸው ፤ የክቡር ዘበኛ ጦርንም ሲቀላቀሉ ገና ልጅ ሳሉ ነበር።
Eyob Zeleke's photo.
እኝህ ቆፍጣና አየር ወለድ ወታደራዊ ትምህርታቸውን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭው አለም በተለያዮ ቦታዎች ተከታትለዋል ለአብነት ያህልም በአሜሪካን ሀገር ፎርት ቤኒንግ ጆርጂያ የእግረኛ ጦር አመራር ትምህርት ቤት ገብቶ ተመርቀዋል ፤በእስራኤል ሃገር የአየር ወለድ ጦር ስልጠናንም ተከታትለዋል ።በተለያዮ ወታደራዊ ተልእኮዋች ላይ በመሰማራት ግዳጃቸውን በብቃት ተውጥተዋል ፤ ለ 71 ጊዜ ከአየር ላይ በፓራሾት ወደምድር ዘለዋል ፤ከ38 ዓ.ም በላይ የሚወዷት ሃገራቸውን ኢትዮጵያን በውትድርና ሙያ ያገለግሎት እኝህ ስመጥር ጀነራል በግንቦት ወር 1981 ዓ.ም ኮለኔል መንግስቱ ሀይለማሪያምን ለማስወገድ በተደረገው መፈንቅለመንግስት አስመራ ላይ መገደላቸው ይታወቃል ።

No comments:

Post a Comment