Wednesday, December 7, 2016

ላይ ላዩን እያየን በስሜት አንጡዝ ሰከን ብለን የለውጥ ሃይሉንና የነጻ አውጪ ድርጅቶችን ጠላቶች መንግለን እንጣል


ላይ ላዩን እያየን በስሜት አንጡዝ ሰከን ብለን የለውጥ ሃይሉንና የነጻ አውጪ ድርጅቶችን ጠላቶች መንግለን እንጣል እያልኩ ነው። ችግሩ ያለው እዚህ ጋር ነው። ካልደማመጥን ካልተከባበርን ልንዳብር አንችልም። በብሄር ተደራጀንም በሃገር አቀፍ ደረጃ ተደራጀንም ከውስጣችን የተሰገሰጉ አደገኛ ቡድኖችን ልናራግፋቸው ይገባል። አደገኛ ቡድኖቹ እንደ ኣድሃሪያውያን እንደ ደርግ እንደ ወያኔና ከነዚህም የባሱ ጭራቅ ፖለቲከኞችን ፈልፍለዋል። የለውጥ ሃይሉን የሚያናክሱ ሃይሎችን ለይተን ልንመታ ይገባል ካልሆነ እርስ በርስ እየተናከሱ ጉዞው ይቀጥላል። ውጤት አልባ መሆን ማለት ይህ ነው። በየሰፈሩ ዞር ዞር ስትል ቅጥረኞች በፖለቲካ ድርጅቶች ኣሊያም በግለሰቦች ስም ላይ ተንጠልጥለው እውነተኛ ታጋዮችን ሲያሳስቱና ሃገር ወዳዱን መስመር ሲያስቱ እያየን ነው
እነዚህ ተናካሽና አናካሽ ሃይሎች ከጀርባቸው የስልጣን ጥመኞች ስላሉ በየጊዜው ችግር እየፈተፈቱ ያጎርሱናል። የወያኔም እድሜ የረዘመው ከዚሁ ሰፈር ነው። ነጻ አውጪ ድርጅቶችና የለውጥ ሃይሎችም የሚባሉት የችግሩ መነሾ ያለው ቤተ አልባ ኢትዮጵያውያን መንደር ነው።ነገ ወያኔ ስልጣን ሲለቅላቸው የጭቆና ስርዓትን ለማወጅ ያሰፈሰፉ የ አምባገነን ቅሪቶች ናቸው።
ወያኔ ከጀርባ የሚያጦዛቸው በአንድነት ሽፋን የሚያጭበረብሩ ፖለቲከኞች በ አንድነት ስም እየነገዱ ኢትዮጵያዊነትን ለማኮላሸት ይሰራሉ። እነዚህ ሆዳሞች በፖለቲካ ድርጅቶች ስም ተደብቀው ታጋይ ሃይሎችን ለት ዝብት ይዳርጋሉ። በነጻ አውጪዎች ስም እየተጠቄሙ የለውጥ ሃይሉን ያባላሉ። መከታዎቻቸው ደግሞ ኣብዛኛዎቹ የ ኣድሃሪና የደርግ ቅሪቶች ናቸው በስሜታዊነት ያጦዟቸዋል። ልብ ብለህ ከተከታተልክ እውነታውን ታውቀዋለህ በነዚህ ሰዎች የነጻነትና የለውጥ ሃይሉ ይወነጀላል።ካልደፈረሰ አይጠራም ለማንም የማያስቡ በብሄር ስም የሚነግዱና በ አንድነት ሽፋን የሚያላዝኑ በነዚህ ሰዎች ዙረት የነጻነትና የለውጥ ሃይሉ እየተወነጀለ ነው እነዚህ ቤት ኣልባ ናቸው በየፈረንጅ ሃገሩ የተደበቁ አጭበርባሪዎች። 

No comments:

Post a Comment