በምስራቅ ሃረርጌ ቁምቢ ወረዳ ዛሬ በሕወሓት መንግስት ጀነራሎች ይደገፋል እየተባለ የሚነገርለት የሶማሊ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ በምስራቅ ሃረርጌ ሚኖ ወረዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ፖሊሶች ጋር በፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::
እንደምንጮቹ ዘገባ በምስራቅ ሃረርጌ ቁምቢ ወረዳ ሚኖ ከተማና አካባቢው በነበረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ ከ10 የማያንሱ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተነግሯል:: ከምስራቅ ሃረርጌ ቁምቢ ወረዳ ነዋሪዎችም ሆነ ከሶማሊያ ልዩ ኃይል ወታደሮች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ቆስለዋል::
በአካባቢው የተነሳው ይኸው ግጭት ከክልሎች ድንበር መስፋፋት ጋር በተነሳ የማንነት ጥያቄ ነው ሲሉ ምንጮች ቢናገሩም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ግን “የትንንሽ የጎሳዎች ጸብ ግጭት” ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል::
ምስራቅ ሃረርጌ ቁምቢ ወረዳ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ውጥረቱ እንዳየለ ነው:: የሶማሊያ ክልል ወታደሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች በየፊናቸው ተፋጠው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
No comments:
Post a Comment