Thursday, December 15, 2016

አበበ ኡርጌሳ የ15 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት


አበበ ኡርጌሳ የ15 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት
ቦንብ በማፈንዳት የአንድ ሰው ህይወት በማጥፋትና ለአርባ ሰው አካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል
በ2006 ዓ.ም ግንቦት ወር የአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም በተነሳው አመፅ ወቅት በሀረማያ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እግር ኳስ በመከታተል ላይ የነበሩ ተማሪዎች ላይ ቦንብ ወርውሮ በማፈንዳንት ለአንድ ሰው ህይወት መጥፋትና ለአራባ ሰው አካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል የተባለው አበበ ኡርጌሳ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የፀረ ሽብር አንቀፅ 3 በመተላለፍ የ15 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ከአበበ ኡወጌሳ ጋር ክስ የተመሰረተባቸው አዱኛ ኬሶ፣ መገርሳ ወርቁ፣ ሌንጂሳ አለማየሁ እና ተሻለ በቀለ ቀደም ብሎ በዚሁ ፍርድ ቤት ብይን የተላለፈባቸው ሲሆን 3ኛ ተከሳሽ አዱኛ ኬሶና 4ኛ ተከሳሽ ቢሊሱማ ዳመና የፀረ ሽብር አንቀፅ 7/1 በመተላለፍ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው የኦሮመሞ ነፃነት ግንባር ጋር ግንኙነት በመፍጠር እያንዳንዳቸው የአራት አመት ከአምስት ወር ፍርድ የተላለፈባቸው ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ መገርሳ ወርቁ ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነፃ ተለቋል። 5ኛ ተከሳሽ የሆነው ተሻለ በቀለ የተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ወደ አመፅ ማነሳሳት ዝቅ ተደርጎ ተከላከል ተብሎ የነበረ ሲሆን በ10ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈቶ ክሱን የተከላከለ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ክሱን በሚገባ አልተከላከልክም ተብሎ የ1ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈርዶበታል። 6ኛ ተከሳሽ ሌንጂሳ አለማየሁ ባሳለፍነው አመት እራሱን መከላከል ሳያስፈልገው ክክሱ ነፃ መውጣቱ ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ከአበበ ኡርጌሳ በስተቀር ሁሉም ተከሳሾች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው እንዲሁም በአመክሮ ከእስር የተፈቱ ሲሆን ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት መቃጠሉን ተከትሎ ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት መውደም አቃቤ ህግ ተጠያቂ ካደረጋቸው 38 ተከሳሾች መካከል አበበ ኡርጌሳ 4ኛ ተከሳሽ መሆኑ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment