Tuesday, December 27, 2016

ከዲሲ ግብረ-ኃይል የተሰጠ ማሳሰቢያ: “አሁንም የወያኔ ባለስልጣናትን ባረፉበትም ሆነ በረገጡበት ቦታ እየተከታተልን ማጋለጣችንን እንቀጥላለን”

ከዲሲ ግብረ-ኃይል የተሰጠ ማሳሰቢያ
የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሐይል በሰሜን አሜሪካ በወያኔ አጀንዳ ላይ ተጽዕኖውን አጠናክሮ ይቀጥላል እንጂ በወያኔ የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳ ቅንጣት ብዥታ ውስጥ እንደማይገባ ለኢትዮጵያውያን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል።አሁንም የህወኅት ባለስልጣኖችም ሆኑ ተላላኪዎቻቸው ባረፉበትም ሆነ በረገጡበት ቦታ የዲሲ ግብረሐይል እግር በግር ተከታትሎ እያከናወኑ ያሉትን ወንጀል ለዓለም ህዝብ ለማጋለጥ በትጋት ስራውን እንደሚፈጽም ቡድኑንም ብዛት ባላቸውና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ለነጻነት ናፋቂው ህዝባችን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።
ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ “ላሜ ቦራ” ብለው እንደሚጠሩት ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ያም ማለት በፈለጋቸው ጊዜ የሚያልቡት “ጥገት” ማለት ነው ፤ይህ ደግሞ የዲሲ ግብረሐይል በአሜሪካን አገር እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ፈጽሞ የሚታሰብ እንደማይሆን ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።ድል ለነጻነት ሃይሎች።
ነጻነት ለተጠማው ህዝባችን።
በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሐይል።

No comments:

Post a Comment