Tuesday, December 27, 2016

ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ ወያኔ ኢሰባዊ ድርጊት የፈፅመ ነው ተባለ (DCESON Radio)

ጎንደር ከተማ  አንገረብ እስር ቤት አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ ቀጥሏል የተባለ ሲሆን። ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ እስከ እረፋዱ ድረስ የዘለቀ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገርባይኖርም የተገደሉ እስረኞች ስለመኖራቸው ይነገራል ።
ሜን ሸዋ መራህቤቴ አካባቢ መሳሪያቸውን ሊገፍ የሄደን የወያኔ ቅጥረኛ ድባቅ መትተው የሸኙት  ጀግኖቹ መሬዎች ሁለት ቅጥረኛ ገለው መሣሪያቸውንም ቀምተው ተሰውረዋል ተብላል። በዚህ የተደናገጠው ወያኔ ከደብረብርሃን ጭምር ሃይል አስመጥቶ  በጉዳዩ የሌሉ ብዙ ሰወችን ደብድብው ወደ 15 ማሰራቸው ተነግራል። ጀማና ውንጪት አካባቢ መንገድ እንደተዘጋጋ መረጃ ከቦታው ደርሶናል። በተጨማሪም
በደባርቅ ከተማ  ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ በሌላ ዙር ወጣት እስካዛውንት ድረስ እያሰረ መሆኑም የተነገረ ነው።
የአምቦ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ አዲስ ውጥረት መንገሱ ተነገረ
በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ።
ህወሃት እስረኞችን “አሰልጥኜ” አስመረኩ አለ፤ እስረኞቹ “ በፍፁም፣ አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ ህገ መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚሉ ኮርሶች የወሰዱ ናቸው።
ህወሃት አምስት ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን “ተመራቂዎች” በሚል መፍታቱን ይፋ ባደረገበት ቀን በተመሳሳይ አምቦ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ተሰማ።
በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ። በጊንጪ፣ በጉደር ፣በኣወዳይና ሻሸመኔ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃና አሰሳ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና ሕወሓት ስልጣን እንዲለቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሶስት የመንግስት መኪኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
በሰሜን ጎንደር በህዝቡና በወያኔ መካከል ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው 
የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄርና አቶ ሙላው ከበደ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ስናር በተባለው አካባቢ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ተከበው የነበረ ሲሆን ከዚህ ከበባ ለመውጣት ከስርዓቱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ውጊያ በማድረግ አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄር 5 የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ገድሎ እርሱም በክብር ተሰውቷል፡፡ ወያኔም እነዚህን ሁለት ሰዎች አስከሬን አይቀበርም ብሎ በጠራራ ፀሃይ መሬት ላይ አስጥቶ እንዲውሉ ቢያደርግም የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ጫና ምክንያት ህዝቡ ቃፍታ ወስዶ ቀብሯቸዋል ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ በአካባቢው ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ማይሰገን ከተባለ ቦታ ከህዝብ ጎን በመቆም አንዳነድ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አንድ የወያኔ ሰላይ የሆነና በኢንቨስተር ስም በአካባቢው የሚኖር በርሄ ጎሼ የተባለ የአገዛዙ ሰላይ ልጁና ወኪሉ በታጠቁ ሃይሎች ተጠልፈው የተወሰዱ መሆኑን አስታውቀው መረጃው ህዝብን እምባ እናብሳለን በሚል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ይህንን የህዝቡንና የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወያኔ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ከመሆኑም ባሻገር አብደራፊ ዳንሻና ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እያሰፈረ እንዲሁም በአካባቢው ያጠራጠራቸውን ሰዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ብዛት ያላቸው ሰዎችን በየጦር ካምፑ አገዛዙ በግፍ እያሰረ እየደበደበ መሆኑ ታውቋል፡፡
//በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም ተባለ
በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ተመዝግበው ሰፋፊ የእርሻ መሬትን የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አለመታወቁን ከክልሉ መሬት አሰጣጥ ጋር ተፈጥሯል የተባለን ችግር እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን ይፋ አደረገ።
ከአንድ አመት በላይ ጥናቱን ሲያካሄድ የቆየው ይኸው ቡድን በጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 623 ባለሃብቶች መካከል ለ381 ባለሃብቶች የተሰጠው ከ45ሺ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል።
የተደራረበ መሬት የተረከቡት እነዚሁ 381 ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር መውሰዳቸውንና ድርጊቱ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱም ታውቋል።
ከባለሃብቶች መካከል 29 የሚሆኑት የገቡበት አልታወቀም።ሆኖም ግን ድርጅቶቹ ምን ያህል መሬት ተረክበው እንደነበርና የወሰዱት ብድር መጠን ሳይገለጽ ቀርቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ልዩ ትዕዛዝ ጥናትን እንደሚያካሄድ ተቋቁሞ የነበረው የባለሙያዎች ቡድን በጋምቤላ ክልል ለሰፋፊ እርሻዎች ከተሰጠ 630 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ወደ ልማት የገባው ከ15 በመቶ እንደማይበልጥ ማረጋገጡን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።
የህንድ ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች በክልሉ መሬትን ተረክበው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ብድርን ከወሰዱ በኋላ የገቡበት አልታወቀም ተብላል

No comments:

Post a Comment