Wednesday, December 28, 2016

ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተዋል።

Minilik Salsawi sitt bilde.አገር የጋራ ነው።ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተዋል። የተለየ ወይንም ብቻውን የተቀደሰ ኢትዮጵያዊ የሚባል ነገር የለም። ኢትዮጵያዊ ሁሉም እኩል ነው። ማንም ከማንም በዜግነት አያንስም አይበልጥም። ግለሰቦችን ይሁን ድርጅቶች ራሳቸውን ልዩ ኢትዮጵያዊ ልዩ አገር አስተዳዳሪ፣ ልዩ የነጻነትና የመብት ታጋይ ልዩ አገልጋይ አድርገው የሚያስቡትን ነገር ማቆም ካልቻሉ በልፋት ላይ ትልቅ አደጋ አለው። እኛን ብቻ ስሙን። እኛን ብቻ እዩ። እኛን ብቻ አንብቡ።እኛ እንድምንልው ሁኑ። ለሃገር ሐሳቢ ሃገር ወዳድ እኛ ብቻ ነን ከኛ በላይ ላሳር እየተባለ ሌላውን ለማግለልና ለማንኳሰስ የሚደረገው ሩጫም ሌላው አደጋ ነው። ኢትዮጵያዊነትን ራሳቸው እንደሚያድሉት የእርዳታ እቃ አድርገው የሚያስቡ አደገኛ ቡድኖችንና ጀሌዎቻቸውን አገር የጋራ መሆኑን አስረግጠን ልንነግራቸው ይገባል። አገር የጋራ ነው። ወያኔ የሕዝብ ጠላት ነው። #MinilikSalsawi

No comments:

Post a Comment