Friday, December 30, 2016

​​ህወሓት ፀረ ወጣት!

ቃልኪዳን ካሳሁን (ከኖርዌይ)

(ቃልኪዳን ካሳሁን)
በህወሓት የሚመራው መንግስት ኢትዮጵያና ህዝቦቹን በሃይል ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በወጣቶች ላይ የሚያድርሰው በደል ተነግሮና ተፅፎ አያልቅም። በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ ስርዓቱ በወጣቱ ክፍል ላይ እያሳደረ ያለው እንግልት ቀላል የሚባል አይደለም። በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወጣቶች ስለሀገራቸውም ሆን ስለህዝባቸው ፍትህና ነፃነት እንዲሁም እኩልነት በሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል ውስጥ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዓት ያደረጉ፣ በየማጎሪያ ቤት ሆነው ዋጋ እየከፈሉ ያሉ፣ ሀገርንና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ተሰደው ስንት መከራና ስቃይ የሚፈራረቅባቸው እንዳሉ መዘንጋት የለበትም።
ይህ ስርዓት ስለህዝባቸውና ስለሀገራቸው ጉዳይ ያገባና የሚሉትን ወጣቶች ማሳደዱን ከቀን ወደቀን እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዳልሆነ ለዚህ ብዙ ማሳያዎች መግለፅ ይቻላል። ከተወሰኑ ወራት በፊት የህወሓትን አገዛ በቃኝ በማለት ህዝባዊ እንቢተኝነት ለማዳፈን የተጠቀመው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰለባ የሆኑ አብዛኛው ወጣቶች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ መከራና ስቃይ እየተቀበለ ያለው ወጣት ቀላል የሚባለ አይደለም።
ከአስቸኳይ ጊዜያ አዋጁ በፊትም ሆን በኋላ ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች በህወሓት ማጎሪያ ቤት ሆነው ይህ ነው የማይባል ዋጋ እየከፈሉ ነው ያሉት። እነዚህ ወጣቶች ከስርዓቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት አላቃታቸውም፤ ነገር ግን ስርዓቱ የለየለት ፋሺስታዊና አምባገነናዊ ስርዓት ስለሆነ ለስርዓቱ አለመገዛታቸው ትልቅ ዋጋ እያስከፈላቸው ይገኛል። እነዚህ ወጣቶች ስለሀገራቸውና ስለህዝባቸው ሲሉ ቀላል የማይባል አሻራ እያሳረፉ ይገኛሉ። በህወሓት ማጎሪያ ቤት ውስጥ ወድ ህይወታቸውን አሲዘው እንደሆነ ሁላችንም ልንረዳ ይገባል።
ህወሓት ፀረ ወጣት ነው! ሲል ለጎልማሳውና ለአዛውንቶች የተመቸ ስርዓት ነው ማለቴ አንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል። ህወሓት ፀረ ህዝብ፣ ፀረ ሀገር እንዲሁም ፀረ ታሪክ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ህወሓት ፀረ ወጣት ነው ስል ስርዓቱን በሚቃወሙት ወጣቶች ብቻ ዙሪያ ተነስቼ አይደለም። ህወሓት ስርዓት አገልጋይ የሆኑ ወጣቶችንም በጥቅማጥቅም በመደለል ለስርዓቱ እንዲገዙ በማድረጋቸው ስለህዝብና ስለሀገር ያላቸው ስሜትና ሞራል እንዲጠፋ አድርገዋል፤ እያደረጉም ነው:: ለዚህም ነው ህወሓት ፀረ ወጣት ስርዓት እያልኩ ያለሁት።
የዛን ዘመን ጀግኖች አባቶቻችን ወጣት ሆነው ይቺህ ትልቅ ሀገር “ኢትዮጵያን” ያስረከቡልን እነሱም በዛን ዘመን ወጣት ሆነው ተዋግተው፣ ታግለው እንዲሁም ወድ ህይወታቸውን መሰዋት ከፍለው ነው አሁን የምንኖርባት ሀገር እንደ ሀገር እንድትጠራ ያደረጏት:: ህወሓቶች ስለ ነገው ሀገር ተረካቢ ወጣት ሳይሆን ጭንቀታቸው ስልጣናቸውን ከእጅ እንዳይወጣ ነው ጭንቀታቸው። ስለዚህ ህወሓትና ስርዓቱ ለዚህ ዘመን ወጣቶች ፀረ ወጣት ናቸው።
ዛሬም እንደሻማ እየቀለጡ ለሌላው ብርሃን እየሆኑ ያሉ ወጣቶችን እየተመለከትን ዝም ከማለት ከጎናቹሁ በመቆም እነሱም ሆነ እኛም በሰላምና በፍቅር የምንኖርባትን “ትልቁ ኢትዮጵያን” ከዚህ ፋሽስታዊና አምባገነናዊ ስርዓት ለማላቀቅ ዋጋ እየክፈለ ባለው ወጣቶች ስም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ።
ጊ ዜ ው አ ረ ፈ ደ ም!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
ቃልኪዳን ካሳሁን (ከኖርዌይ

No comments:

Post a Comment