Friday, December 23, 2016

ባለሙያ” ተሳዳቢዎች Tadesse Biru Kersmo


“ባለሙያ” ተሳዳቢዎች 
የኢህአዴግ መጽሄት የሆነው “አዲስ ራዕይ” በቅርቡ በመጣው በመስከረም-ጥቅምት 2008 እትሙ “በሶሻል ሚዲያ ምህዳሩ ተሳትፎዓችንን በማሳደግ ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ” የሚል ጽሁፍ አውጥቷል። ይህ ጽሁፍ የኢህአዴግ ካድሬዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በፌስ ቡክ የተቀናጀ ዘመቻ እንዲያደርጉ ይወተውታል።
ከሁለት ዓመታት በፊት የህወሓት አገዛዝ 235 “ባለሙያ ተሳዳቢዎችን” አሠልጥኖ ማስመረቁ በወቅቱ ዜና ተሰርቶ ነበር። እኔም ይህ “ባላሙያ ተሳዳቢዎችን” የማሰልጠን ልምድ ከቻይና የተወሰደ ስለመሆኑ፤ “የቻይና 50 ሣንቲም ፓርቲ” ታሪክን ጠቅሼ ለኛም ስላለው እንደምታ “ናይ ፌስቡክ ተፃረፍቲ (የፌስ ቡክ ላይ ተሳዳቢዎች)” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ጽፌ ነበር፤ ማንበብ ለምትፈልጉ ይህንን መጣጥፍ በርዕሱ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ።
ከሁለት ዓመት በኋላ ይኽ ርዕስ በአቢይ አጀንዳነት መነሳቱ ያለምክንያት አይደለም፤ ኃይለማርያም ደሳለኝ በ UN ስብሰባ ጭምር ያነሳው ርዕስ መሆኑን ልብ ይሏል።
ከአገዛዙ የስለላ ድርጅቶች የማገኛቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፌስ ቡክ አንዱ አቢይ የትግል ሜዳቸው ሆኗል። የአንድነት፣የመኢአድ እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን በመግዛት ፓርቲዎቹን እንዳሽመደመዱ ሁሉ አንዳንድ “ስም ያላቸው” የፌስ ቡክ ጸሀፊያንን በመገልበጥ ሜዳውን ለመቆጣጠር አቅደው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ዋና ዋና “የትግል ስልቶቻቸው”
(1) አርበኞች ግንቦት 7፣ ግንቦት 7፣ ኢሳት፣ ሻዕቢያን፣ ኤርትራንና ግብጽን አሳክረው ማቅረብ፣
(2) ለአማራ የሚከራከሩ መስለው ኢትዮጵያዊነትን ማደብዘዝ።
(3) ፌስ ቡክ በአማራ፣ በኦሮሞና በትግራይ ዘረኛ ዘለፋዎች እና ስድቦች እንዲቆሽሽ ማድረግ፣
(4) በዲሞክራሲያዊ ትግል ጠንካራ አቋም የያዙ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ስም ማጥፋት፣
መፍትሄ
1. ማኅበራዊ ሚዲያን በተለይም ፌስቡክን ለእነሱ አለመልቀቅ፤ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በመሳቀቅ ፋንታ መዝናናት።
2. ናይ ፌስ ቡክ ተፃረፍቲዎችን ማስነወር፤ “ሥራቸው” ምን ያህል አዋራጅ እንደሆነ መንገር፤ እነሱን በማብሸቅ መዝናናት።
3. ከእነሱም መካከል ልባሞች አይጠፉምና ምስጥራዊ ግኑኝነት መመሥረት ሆኖም በቀላሉ አለማመን።

No comments:

Post a Comment