Thursday, December 22, 2016

ሰሜን ሸዋ መራህቤቴ አካባቢ መሳሪያቸውን ሊገፍ የሄደን የወያኔ ቅጥረኛ ድባቅ መትተው ሸፍተዋል።


የሽዋ አማራ እየተነሳ ነው!
ጎንደር እረፍት የለም!
ሰሜን ሸዋ መራህቤቴ አካባቢ መሳሪያቸውን ሊገፍ የሄደን የወያኔ ቅጥረኛ ድባቅ መትተው ሸፍተዋል። ጀግኖቹ መሬዎች ሁለት ቅጥረኛ ገለው መሣሪያቸውንም ቀምተው ተሰውረዋል። የተደናገጠው ወያኔ ከደብረብርሃን ጭምር ሃይል አስመጥቶ አብይ አጠጪ ናችሁ በማለት በጉዳዩ የሌሉ ብዙ ሰወችን ደብድብው ወደ 15 አስረዋል። ጀማና ውንጪት አካባቢ መንገድ እንደተዘጋጋ መረጃ ከቦታው ደርሶናል።
***************
ጎንደር እረፍት የለም!
ዛሬ በሳንጃ አካባቢ ሙሴ ባምብ በተባለ ልዩ ቦታ መሳሪያ ሊያስወርዱ ከሞከሩት የወያኔ ቅጥረኞች ውስጥ ሁለቱን ገሎ ጫካ ገብቷል።
ጎንደር ከተማ ውስጥ ደግሞ አንገረብ እስር ቤት አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ ቀጥሏል። ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ እስከ እረፋዱ ድረስ የዘለቀ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ስለደረሰ ጉዳት እያጣራን ነው።
በደባርቅ ከተማ ደግሞ ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ በሌላ ዙር ወጣት እስካዛውንት ድረስ እያሰረ ነው።
ዳባት መግቢያ በር ላይ ወደ በንከር ወደሚወስደዉ መንገድ ላይ ተጨማሪ ከመከላከያ ዉጭ ፌደራል ወታደር ተጨምሯል። ምክንያቱም የወያኔ መከላከያ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ነው።
#የጀግናው ጎቤ የወያኔን ከበባ ድባቅ መቶ መውጣት ጎንደር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተወደሰ ነው። በማህበራዊ ሚዲያም የኢትዮጵያውያንን ቀልብ ገዝቶ ዘልቋል።
ጎጃም በቋፍ ነው! ስማ ወሎ!
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment