Wednesday, December 7, 2016

የመንግስት ካድሬዎች በሐርቡ ከተማ ሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙት እስራትና አፈና ቀጥሎል


የመንግስት ካድሬዎች በሐርቡ ከተማ ሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙት እስራትና አፈና ቀጥሎል
የመንግስት ካድሬዎች በሐርቡ ከተማ ሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙት እስራትና አፈና ቀጥሎ በትላንትናው እለት 5 ( አምስት ሙስሊሞች ታፍነው ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል የሐርቡ ከተማ የbbn ምንጮቻችን ዛሬ በላኩት መረጃ እንዳስታወቁት የሐርቡ ከተማ ሙስሊሞችን እያዋከቡና እየዘረፉ የሚገኙት አቶ አሸብር ፣ አቶ ጀማልና ኮማንደር መሀመድ የተባለት የመንግስት ካድሬዎች የከተማዋን ሙስሊሞች እያንገላቱ እንደሚገኙ ታውቆ በትላንትናው እለት ከሰአት ቡሃላ
1) ሸህ ሰኢድ መሀመድ 2) ሸህ አብዱ ጦይብ
3) ኢስማኢል ሰኢድ
4) አህመድ አልሃዲ
5) ሙስጦፋ ዳውድ
የተባሉትን የሐርቡ ከተማ ሙስሊሞች አፍነው በመውሰድ በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው የቃሉ ወረዳ ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሰሯቸው ለማወቅ ተችሏል
እነዚሁ ሙስሊሞች ከሳምንት በፊት ለዝያራ ወደ ገርባ እና ደጋን ከተማ በመሄድ ላይ ሳሉ ሚጢቆሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደህንነቶች ታግተው ተይዘው የገርባና ደጋን ወንድሞቻችሁ ጋር ዝያራ ማድረግ አትችሉም በሚል ለአንድ ቀን ያክል ታድረው እንደተለቀቁ በቢቢኤን መዘገቡ ይታወሳል
ለጫት መገዣና ጉቦ የሚሆን ገንዘብ ካልሰጣችሁን እናስራችኋለን በማለት የሐርቡ ከተማ ሙስሊሞችን በተለይም ነጋዴዎችን እያስፈራሩ የሚገኙት እነዚሁ አቶ አሸብር ፣ አቶ ጀማልና ኮማንደር መሀመድ የተባሉት የመንግስት ካድሬዎች ግዜው የኛ ነው እንኳን ማሰር ቀርቶ ተኩሰን ብንገድል ጠያቂ የለንም ምን ታመጣላችሁ እያሉ በሙስሊሞች ላይ በግልፅ እንደሚዝቱ ተጨምሮ ለማወቅ ተችሏል
መረጃውን ያደረሰን ሁድ ሁድ የተባለው የሐርቡ ከተማ ምንጫችን ነው ኢንሻ አላህ ተጨማሪ መረጃዎችን በምሽቱ መደበኛ ፕሮግራማችን ላይ ይዘን እንቀርባለን

No comments:

Post a Comment