Monday, December 12, 2016

በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወይዘሮ ብርቱካን ተደራራቢ ወንጀል በመንግስት ደጋፊዎች ተቃውሞ እያስነሳ ነው።


Ethiopian Ambassador Birtukan Ayano Dadi and her husband, Yohannes Admassu Haile, hosted a reception at the Chateau Laurier May 28 to mark the 24th anniversary of downfall of the Dergue regime and 50 years of diplomatic relations with Canada. (Photo: Ulle Baum)
በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወይዘሮ ብርቱካን ተደራራቢ ወንጀል በመንግስት ደጋፊዎች ተቃውሞ እያስነሳ ነው = ተሃድሶ ላይ ነኝ የሚለው የወያኔው ቡድን በወንጀል የተዘፈቁ ዲፕሎማቶቹን ቀለም እየቀባ ከማስቀመጥ ከስልጣናቸው ሊያስወግድ ይገባል የሚሉ አቤቱታዎች በዝተዋል። በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወይዘሮ ብርቱካን ተደራራቢ ወንጀል በመንግስት ደጋፊዎች ተቃውሞ እያስነሳ ነው። ሲሉ የተሃድሶው ትውልድ ኣባላት የሚባሉ ኢሕአዲጋውያን በማህበራዊ ድረገጽ ይፋ አድርገዋል።ግለሰቧ ከቦታዋ ተነስታ ለሕግ እንድትቀርብ ፊርማ ሊሰባሰበ መሆኑ ተሰምቷል። የቴዎድሮስ አድሃኖም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ነፍጎ በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ማተኮር ዲፕሎማቶች በስልጣናቸው እንዲባልጉና በሕገወጥ ስራ ላይ እንዲሰማሩ በሩን ከፍቷል የሚሉት የወያኔ ካድሬዎች የወርቅነህ ገበየሁ የቴሃድሶ አብዮት አምባሳደሯን እንዲውጣት እየዌተወቱ ይገኛሉ።
አምባሳደር ብርቱካን ኣያኖ ዳዲ በጉዲፈቻ የወስዱትን የባላቸውን የወንድም ልጅ በከፍተኛ ኢሰብዓዊነት በሞላው መንገድ ሲበድሉት ኖረው የጀመረውን ትምህርት አቋርጦ ወደ ኢትዮጵያ የገጠር መንደሩ እንዲመለስ በማድረግ ተስማምተው የፈረሙትን የራሳቸው ኣገዛዝ የሕግ ውል ስልጣናቼውን መከታ በማድሬግ መጣሳቸውን በተመለከተ ኤቤቱታ እየቀረበባቸው ሲሆን ይህን ተከትሎ ኣምባሳደሯ በሃሺሽ ንግድና በሕገወጥ የቪዛ ዝውውር ውስጥ ዲፕሎማትነታቸውን መከታ በማድረግ መሳተፋቸውን ከኤምባሲው ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።
ተሃድሶው ሊገመግማት ይገባል በስልጣን ባልጋለች የሃገሪቱን መልካም ገጽታ ኣበላሽታለች የሚሉት የወያኔ ካድሬዎች መሳቂያ መሳለቂያ ሳታደርገን ከቦታዋ ልትነሳ ይገባል የሚሉ ሮሮ እያሰሙ ነው።በካናዳ ለሚኖሩ የተለያዩ ዲፕሎማቶችና የካናዳ መንግስት ሰራተኞች የተለያዩ ግብዣዎችን በማድረግ እያግባቡ ለሕገወጥ ስራቸው እንደሚጠቀሙባቸው የኤምባሲው ዲፕሎማቶች ይናገራሉ። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የተለያዩ ሪፖርቶች ቢደረጉም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዝምታን መርጧል።
ከኣምባሳደሯ ጋር በሽርክና ሕገወጥ የሃሺሽ እና የቪዛ ስራ የሚሰሩ ደላሎች የወያኔ ካድሬዎች በሴትዬዋ ላይ ያነሱትን ኣቤቱታ እንዲሰርዙ በማግባባት ላይ ይገኛሉ። የወያኔ ካድሬዎች ኤምባሳደሯ ከቦታዋ ተነስታ በሕግ ፊት እንድትቀርብ ፊርማ ማሰባሰብ ሊጀምሩ መሆኑ ታውቋል። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment