Sunday, December 25, 2016

የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አስደንጋጭ እንዲሁም አዝናኝ ወሬዎች


የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አስደንጋጭ እንዲሁም አዝናኝ ወሬዎች  – ሚኪያስ በ. ወርዶፋ  
ፒኤስጂ 36 ሚሊዮን ፓውንድ በሆነ የዝውውር ሂሳብ ድራክስለርን ሲነጥቃቸው ቁጥ ብለው ከማየት ውጪ ምንም ማድረግ ያልቻሉት የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ “ክለባችን ተጨዋቾችን ለማማለል የክለቡን የለውጥ ሂደት እንጂ ገንዘብ አይጠቀምም።” በሚል የሰጡት አስተያየት ከንዴት የመጣ ንግግር አስመስሎባቸዋል፡፡ (ዘ ጋርዲያን)
ሳውዝአምፕተኖች ለሆላንዳዊው ተከላካያቸው ቨርጂል ቫን ዲጂክ 60 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ የለጠፉበት ሲሆን ነገር ግን በመጪው የጥር የዝውውር መስኮት ለሽያጭ ለማቅረብ እቅድ እንደሌላቸው ታውቋል፡፡ (ቴሌግራፍ)  
ማንችስተር ሲቲ በመጪው ጥር ለዝውውር ትልቅ ብር እንደማያወጣ የክለቡ አሠልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ ተናገረ፡፡ (ዘ ጋርዲያን)
ኤቨርተኖች ሜምፈስ ዲፔይንና ሞርጋን ሽንደርሊንን ለመውሰድ ለዩናይትድ መደበኛ  የሆነ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው፡፡ (ቴሌግራፍ)
ዴቪድ ሞይስ በአሰልጣኝነት ዩናይትድ ቤት በነበሩበት ወቅት ክርስቲያኖ ሮናልዶን፣ ጋሬዝ ቤልንና ሴስክ ፋብሬጋዝን ለማስፈረም አስበው የነበረ ቢሆንም ከሀሳባቸው በተቃራኒው ቤልጄማዊውን ማርዋን ፊላኒን አሰፈርመዋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)
ማንችስተር ሲቲዎች ሜሲ ከክለቡ ባርሴሎና ጋር ሊያደርገው የነበረው የዝውውር ንግግር በቆመበት በመቅረቱ ሜሲን ለማስፈረም እየተከታተሉት ይገኛል፡፡ (ማርካ ሰንን ጠቅሶ እንደፃፈው)   
ከሰዓታት በፊት የዝውውር ስምምነታቸውን ለማጠናቀቅ ወደ ክሪስታል ፓላስ የልምምድ ማዕከል ያመሩት ሳም አላርዳይስ ስምምነታቸውን ጨርሰው የንስሮቹ አዲሱ (ከስር በምስሉ እንደሚታየው) አሠልጣኝ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል፡፡ (ዘ ጋርዲያን)
የማንችስተሩ ተከላካይ ማርኮስ ሮሆ በ 14 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ የስፔኑ ቫሌንሺያ የጥር ወር የዝውውር ኢላማ መሆኑ ታውቋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሮይ ሆድሰን ሲያሰለጥኗቸው የነበሩት የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በአውሮፓ ዋንጫ ከአይስላንድ ጋር በነበራቸው የሁለተኛ ዙር ግጥሚያ “ትንሽ ፈርተው እንደነበር” ይፋ አደረጉ፡፡ (ታይምስ)
ማንችስተር ዩናይትዶች የ 35 ዓመቱን ዛላታን ኢብራሂሞቪችን በክለባቸው ለማቆየት የተጫዋችነት ህይወቱ ካበቃ በኃላ የአሰልጣኝነት ሀላፊነት ሊሰጡት አስበዋል፡፡ (ዴይሊ ስታር)
የዳኒ ዌልቤክ ከጉዳት አገግሞ ወደ ቡድኑ ዳግም መመለሱ ለአርሰን ቬንገር ተጨማሪ አዲስ መሳሪያ እንደሚሆናቸው ተነገረ፡፡ (ዘ ጋርዲያን)
የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ ቡድናቸውን ለቆ ወደ ስቶክ ያመራውና ማክሰኞ ምሽት በሊጉ ግጥሚያ የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ወደ አንፊልድ የሚመለሰውን አማካኝ ጆ አለንን ብቃት ቡድናቸው እንዳጣው ተናገሩ፡፡ (ዴይሊ ኤክስፕረስ)
ትናንትና ምሽት በተደረገ የፍጻሜ ግጥሚያ ኤሲ ሚላን ተቀናቃኙን ጁቬንቱስን በመለያ ምት በማሸነፍ የሱፐርኮፓ ኢጣሊያን ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡ (ዘ ጋርዲያን) 
በመጨረሻም … 
የዩናትዱ አለቃ ጆሴ ሞውሪንሆ ሞርጋን ሽንደርሊን ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን አምነዋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)
ሳም አላርዳይስ ክሪስታል ፓላስን ከመውረድ አደጋ እንዲታደጉት በመጪው ጥር ወር ለተጫዋች ዝውውር የሚያውሉት 20 ሚሊዮን(ከስር በጋዜጣው ምስል ላይ እንደሚታየው) ፓውንድ ተመድቦላቸዋል፡፡ (ዴይሊ ስታር)

የኤቨርተኑ አለቃ ሮናልድ ኩመን አይን የሚገባና አማካኛቸውን ሮስ ባርክሌይንና የቶትነሀሙን ሙሳ ሴሴኮ የሚያሳትፍ ትልቅ የዝውወውር ስምምነት ለመፈፀም አስበዋል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)
የቤኔፊካው ተከላካይ ቪክተር ሊንድሎፍ ወደ ማንችስተር ቤት ለማምራት መቅረቡን የአንድ የዩናይትድ ደጋፊ ያቀረበለትን የቀያዮቹ ሴይጣኖች ማሊያ ላይ ፊርማውን በማኖር ተጨማሪ ጥቆማ ሰጥቷል፡፡ (ዴይሊ ኤክስፕረስ)  
የዩናይትዱ የ 31 ዓመት አጥቂ ዋይኒ ሩኒ የቻይናን ሊግ እንዲቀላቀል ከሁለት የቻይና ሊግ ክለቦች የአለም ሪከርድ የሆነ ሳምንታዊ የ 700,000 ፓውንድ ክፍያ ቀርቦታል፡፡
ከሰሞኑ የቼልሲው አማካኝ ኦስካር በ 52 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቻይና ማምራቱ እርግጥ የሆነ ሲሆን የቦካ ጁኒየርሱ የቀድሞ የዩናትድ አጥቂ ካርሎስ ቴቬዝም ሪከርድ የሆነ ሳምንታዊ 615,000 ፓውንድ ክፍያ ቀርቦለት ወደ እዛ ማምራቱ እርግጥ የሚሆን መስሏል፡፡
በሞሪንሆ ስር ቋሚ ተሰላፊነትን የማግኘት ነገሩ አስተማማኝ ያልሆነውና ካለፉት አመታት ጀምሮ አቋሙ መውረዱ በጣም እያስተቸው የሚገኘው ሩኒ አዲሱን የአለም ሪከርድ ክፍያ የሚቀበል ከሆነ ዝውውሩ ቀጣዩ የቻይና ክለብ ሊግ ተጫዋች ይሆናል፡፡
ነገር ግን የገበያ ዋጋው 10 ሚሊዮን ፓውንድ የሆነው ሩኒ በመጪው ጥር ክለቡን ለቆ ወደ ቻይና ያመራል የሚለውን ነገር ላይ ውሀ የሚቸልስ ነገር ከፊቱ ተደቅኗል፡፡
ይህ እንቅፋትም በዩናትድ ቤት 248 ጎሎችን ያስቆጠረው ሩኒ የቦቢ ቻርልተንን በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ብዙ ጎል በማስቆጠር የተያዘውን ሪከርድ ለመጋራት በአንድ ጎል ብቻ አንሶ መቀመጡ ነው፡፡
ስለዚህም ይህን 43 ዓመት የተያዘ ሪከርድ ከመጋራት አልፎ ሪከርዱን ሳይሰብር ዩናይትድን ይለቃል ማለት የሩኒን የአልሸነፍም ባይነት ባህሪ መዘንጋት ይመስል፡፡ (ዴይሊ ሚረር)

No comments:

Post a Comment