Thursday, December 8, 2016

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የሰጠችውን ማስጠንቀቂያ አራዘመችው።


አሜሪካ በኢትዮጵያ የተከሰተውን የፖለቲካ ቀውስና የሕዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ የሰጠችውን ማስጠንቀቂያ አራዘመችው። አሜሪካ ከሕዝብ ተቃውሞና ከኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ ምንም እንቅስቃሴ ማድሬግ እንደማይቻል ገልጻ ማንኛውም የመገናኛ ዘዴዎች ኢንቴርኔትና ሞባይል ዳታን ጨመሮ በሃገሪቱ መንግስት እንደተቆለፈባቸው ገልጻለች። ኤምባሲዋን ጠቅሳ በሃገሪቱ ያለው አለመረጋጋትና የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ማድረጉንና በሃገሪቱና ሕዝቡ ላይ ስጋት ስለጣለ የጉዞ ማስጠንቀቂያው መራዘሙን ተናግራለች። በወያኔ የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዲፕሎማቶችንም እንደሚመለከት ይታወቃል። 

No comments:

Post a Comment