Tuesday, December 27, 2016

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 16 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያ በአገዛዙ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ችግር ከሕግ አንጻር ለመተንተን ያስቸግራል ዝም ብሎ ሕገ ወጥ ነው ማለት ብቻ ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት የስርኣቱን በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍ አይገልጽም ሁኔታው ግራ የሚአጋባ ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ነው …በውጭ ያለው ወገን የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአገር ውስጥ ባለው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ለውጥ የምንፈልግ ከሆነ በውጭ ያለነውም ልዩነትን አቻችሎ ለውጡን የሚያግዝ እርምጃ ካልወሰድን በተዘዋዋሪ የእና ድክመት የስርኣቱ ጥንካሬ እየሆነ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል ባቻ ሳይሆን…> የሕግ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ በለንደን ኪል ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ)
<…በአገር ቤት የታሰሩት መስዋዕትነቱን ለመቀበል ወስነው ሲታገሉ እና ደግሞ ችግር ላይ አሉትን እስረኞችና ቤተሰቦቻቸውን በኣልን አስታከን እንድናስብ ነው ጥሪ ያደረግነው። ይሄ በዚህ ብቻ አያበቃም ሌሎችንም ለመደገፍ መነሳት አለብን…> እናት እናትዬ ከዳላስ  ለእስረኞች በጎ ፈንድ ለጀመሩት ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረት ከሰጠችን ማብራሪያ
<…ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እየተደበደቡ ቶርች እየተደረጉ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ስለተሰቃዩ ቶርች ያደርጋቸው ስርኣት ምስክር ወረቀት እየሰጣቸው ነው።ቶርች አድርጎ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ነው። በአገር ቤት ይሄን ጭካኔ ተቋቁመው እየታገሉ ነው ። እኛ እዚህ በአሜሪካና በአውሮፓ ያለን ኢትዮጵያውያን በዚህ ወቅት እንኳን ተገቢውን ድጋፍ ልናደርግ እስረኞችን ልናስባቸው ይገባል የእኛ ጥረት 20 ዶላር ለ አራት መቶ  በሚል ስምንት ሺህ ለመሰብሰብ ነው ይሄ ጥረት በሌሎችም መቀጠል ስርኣቱ ድምጻቸውን ለሚያፍናቸው መደገፍ አለብን…> ናትናኤል አስመላሽ ከኦክላሆማ ለእነ ዳንኤል ሺበሺ በጎ ፈንድ ዕርዳታ ለማሰባሰብ ለጀመሩት ጥረት

የማርሽ ቀያሪው ፥ለበርካታ አትሌቶች መንገድ ጠራጊው እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር እሳዛኝ እና አስገራሚ ገድሎች(ዝክረ ምሩጽ ይፍጠር)
ኮማንድ ፖስቱና ግፉን እንዳይናገሩ ያሰራቸው ንጹሃን ጉዳይ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)
ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር ያደረግነው ቃለ መተይቅ ተከታይ ክፍል(ያድምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የአማራ ገበሬዎች በሕወሓት አገዛዝ የተከፈተባቸውን የጦርነት ጥቃት እየመከቱ ድል እየተቀዳጁ ነው
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በማንኛውም ሰዓት አፍኖ ለመወሰድ ከሌሎች እስረኞች ተነጥሏል
የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ያሳየው ችልተኝነት ቤተስቦቻቸውን አስቆጣ
“ያለ ወላጅ አባት የገና በዓልን ለሶስተኛ ጊዜ ማክበር በጣም ይስማል”የታዳጊ ልጃቸው ምናቤ አንዳርጋቸው ብሶት
አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ግብጽ ተቃዋሚዎችን አደራጅታ እያስጠቃችን ነው በማለት ካይሮን ዳግም ወነጀሉ
“እኛ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም”የግብጽ የው/ጉ/ሚ/ር መግለጫ
በቨርጂኒያ የሞቱት ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አገዳደል ግንኙነት እንደሚኖረው ፖሊስ አስታወቀ
ድርጊቱን ፈጸመውን ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል
የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህሩ ስዩም ተሾመ  እና ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው ከተፈቱ በሁዋላ ስለ እስሩ በመጠኑ ገለጹ
ኤርትራዊው ሚሊየነር በተደራጁ የኡጋንዳ መኮንኖች ታፍነው ተገደሉ
የሕወሃት/ኢሕአዲግ መንግስት ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ያባረራቸው የደ/ሱዳኑ ም/ል ፕ/ት ዶ/ር ሪክ ማቻር ደ/አፍሪካ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኑ ተባለ
“ማቻር ስልካቸው ይበረበራል፥ወደ መጸዳጃ ቤት ሲሄዱ ይነጠቃሉ”ምንጮች
ሌሎችም 
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠርከምሽቱ 630 ሰዓትእስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ01405770140 በስልክ ማዳመጥይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻእንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment