Thursday, December 15, 2016

በአቶ በቀለ ገርባ ላይ መስካሪ አልተገኘም።


በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ምስክር መሰማት መስካሪ አልተገኘም።
የአቃቤ ህግ ምስክር በዝግ ችሎት ይሰማልኝ ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል።
19 የሚደርሱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በአድራሻቸው ተፈልገው አልተገኙም።
በጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀምሯል። አቃቤ ህግ ለምስክሮች ደህንነት ሲባል ምስክር የማሰማቱ ሂደት በዚግ ችሎት ይሁንልኝ ቢልም ጉዳዩን በአዳሪ ያየው ፍርድ ቤት የአቃቤ ህግን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ምስክር የማሰማት ሂደቱ በተከታታይ ቀናት የቀጠለ ሲሆን ከተከሳሽ ቤት የተገኙ ሰነዶች ላይ ተከሳሾቹ ሲፈርሙ አይተናል በማለት አቃቤ ህግ ያመጣቸው የደረጃ ምስክሮች አስረድተዋል። በእስከአሁኑ ምስክር የማሰማት ሂደት ቀጥተኛ ምስክር ወይም ይህ ተከሳሽ እንዲህ ሲናገር ሰምቼዋለሁ/ እንዲህ ሲያረግ አይቸዋለሁ የሚል እንደሆነ ተውቋል።
አቃቤ ህግ ካስመዘገባቸው ምስክሮች ውስጥ አስራ ዘጠኙ በአድራሻቸው ተፈልገው ሊገኙ አልቻሉም፤ ይህን በተመለከተ የተከሳሾቹ ጠበቆች ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ደንበኞቻቸው ከተከሰሱ 7 ወራት ማለፉንና ተጨማሪ ቀጠሮ ቢሰጥም ምስክሮቹ ይመጣሉ ብለው እንደማያምኑ ቢገልፁም ፍርድ ቤቱ ያልተመሰከረባቸው ተከሳሾች ስላሉና የተሟላ ፍትህ ለመስጠት በሚቀጥለው ቀጠሮ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ይዞ እንዲቀርብ አዘዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበርና 4ኛ ተከሰሽ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ላይ እስካሁን በነበረው ምስክር የማሰማት ሂደት አንድም ምስክር እንዳልቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል። ፍርድቤቱ ቀጣይ ቀጠሮዎችን ለመስማት ከታህሳስ 18/2009 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

No comments:

Post a Comment