የኑሮን ጉዳይ የሚረሳ ፖለቲካ … ለአሜሪካም አላዋጣም፤ ለኢትዮጵያማ… ዮሃንስ . ሰ.
1 የዶናልድ ትራምፕ መፍትሄ፣- ቢዝነስ እተዳከመ፣ ስራ አጥነትና የኑሮ ቅሬታ የተባባሰው፣ በመንግስት ምክንያት ነው፡፡
ስለዚህ …- ያበጠውን መንግስት አስተነፍሳለሁ (ታክስእቀንሳለሁ)፡፡ ነገረኛውን መንግስት አደብ አስገዛሁ (ቁጥጥሮችን አሰርዛለሁ)፡፡ ተናካሹን መንግስት እገራለሁ (የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻዎችን እገታለሁ)፡፡
2. የአገራችን ፖለቲከኞች መፍትሄስ?- በኢኮኖሚ ውስጥ የመንግስት ድርሻ እየገዘፈና እያበጠ መቀጠሉ ጉዳያችን አይደለም፡፡
ለሁሉም አይነት ችግር፣ የመንግስት ቁጥጥር መፍትሄ የሚሆን ይመስለናክ፡፡ ‹‹የአካባቢ ጥበቃ”፣ የአገር ወግ ሆኗል – የኢቢሲ የዘወትር ዜና የአካባቢ ጥበቃ ዜና ነው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው አገሬው በዓመፅ ሲታመስ ብቻ ነው፣ የስራ አጥነት የኑሮ ችግር፣ ዋና የፖለቲካ ጉዳይ እንደሆነ የሚገባን፡፡ እስከ ነሐሴ እስከ መስከረም ድረስ፤ በደንብ እየተገነዘብነው ነበር፡፡
ግን ረሳነው … በጥቂት ሳምንታት ውስጥ፡፡
ለበርካታ ወራት የዘለቀው የተቃውሞ፣ የግጭትና የአመፅ ማዕበል፣ አገሪቱን እያንገራገጨ ወደ አስፈሪ ትርምስ ሲነዳት አይተናል፡፡ ይሄ የማስጠንቀቂያ ወይም የትንበያ መረጃ አይደለም፡፡ በእውን ሲከሰት ያየነው የዘመናችን ታሪክ ነው፡፡ አስፈሪነቱ ወይም አሳሳቢነቱም አከራካሪ አልሆነብንም፡፡ የቀውሱ መንስኤዎች ምንድናቸው የሚለው ጥያቄ ላይ ግን የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡
በአንድ በኩል፣ “የፖለቲካ ነፃነት አለመስፋፋቱ ወይም መጥበቡ የቀውስ መንስኤ ሆኗል” የሚሉ አሉ፡፡ እውነት አላቸው፡፡
በእርግጥ፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው፣ ፍሬቢስ የብሄረሰብ የቋንቋ ወዘተ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ይሄ .. ኑሮን የረሳ የፖለቲካ ቁማር ነው፡፡ በዓመት 100 ሺ ኢትዮጵያዊያን፣ በየመን በኩል የሚሰደዱት፣ የብሄር ቋንቋን ወይም በብሄረሰብ ኮታ የተሾሙ ባለስልጣናትን ፈልገው አይደለም፡፡ ይልቅስ ቁምነገር እንነጋገር፡፡
እውነት ነው፤ … የፖለሪካ ነፃነትን ደረጃ በደረጃ ለማስፋፋት ጥረት ካልተደረገ፣ ውሎ አድሮ ቀውሶች መፍጠራቸው አይቀርም፡፡ በስልጣኔ ጎዳና ለመራመድ፣ የፖለሪካ ነፃነት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን፣ “ህዝቡ ነፃነትን ይፈልጋል” እያልኩ አይደለም። የነፃነት ፍላጎት እንዲህ በቀላሉ የሚፈጠር ነገር አይደለም፡፡ የስልጣኔ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም ግን “ህዝቡ ነፃነት ያስፈልገዋል” በሚል ሀሳብ መስማማት ይቻላል፡፡
ሌላኛው ሀሳብ፣ ስራ አጥነትና የኑሮ ቅሬታ፣ የቀውስ መንስኤ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው። በዚህ ሀሳብ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ “በየዓመቱ በአማካይ ከ2 ሚ. በላይ በየስራ እድሎችን ፈጥረናል” ሲሉ የነበሩት የኢህአዴግ መሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናትም ጭምር፤ “ስራ አጥነትና የኑሮ ቅሬታ … የቀውስ መንስኤ ሆነዋል” በማለት ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ጥሩ ነው፡፡ የቀውስ መፍትሄ ለማበጀት፣ የቀውሱን መንስኤ መገንዘብ ያስፈልጋልና፡፡
ችግሩ ምን መሰላችሁ? ቀውሱ ትንሽ ረገብ እያለ፣ ሳምንት በሳምንት ሲተካ፣ ለስራ አጥነትና ለኑሮ ቅሬታ የሚሰጡት ትኩረት እየቀነሰ መጥቷል። ለዚህም ኢቢሲን መመልከት ትችላላችሁ፡፡ በስራ አጥነት ችግሮች ላይ ያተኮሩ ዜናዎችና ዘገባዎችን አታገኙም፡፡ በተቃራኒው፣ በየእለቱ በኢቢሲ ፈፅሞ የማይጠፋ ዜና ምን መሰላችሁ? የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ … የሰሜን ዋልታ በረዶ መጥበብና መስፋት፣ የህንድ የአየር ብክለት፣ የአሳ ነባሪዎች ቁጥር፣ ወዘተ…
እነዚህ ሁሉ፣ የአካባቢ ጥበቃ የተለመዱ ዘመቻዎች ናቸው፡፡ ለነገሩ በአለማቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ (በአየር ንብረት ዘመቻ ወይም በአረንጓዴ ልማት ዘመቻ…)፣ “ኢትዮጵያ ዋና መሪ እየሆነች ነው” በማለት በየእለቱ የሚያሰማን ኢቢሲ አይደለም? ከኢቢሲ የማናገኘውና የማንሰማው ነገር ደግሞ አለ፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ ወይም አረንጓዴ ልማት ማለት፣ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦችን ማውገዝ ማለት እንደሆነ ኢቢሲ አይነግረንም፡፡ በተቃራኒው፣ ግድብ መገንባትን በመተው፣ በግማሽ የሚያንስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት፣ እጥፍ ያህል ውጪ የሚፈጁ የነፋስ ተርባይኖች እየተገዙ የድሃ አገር ሃብት ይባክናል፡፡
በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን በመተው፣ ከእጥፍ በላይ ወጪ የሚጠይቁና በባትሪ የሚሰሩ መኪኖችን መጠቀም አለብን ይላል – የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ፡፡ የባትሪ ቻርጅ ማድረጊያ ማሽኖችን በየቤቱ ለመትከል ሌላ ብዙ ወጪ፣ በስምንት ሰዓት ቻርጅ የሚደረገውን ባትሪ በአራት በአምስት ዓመት ለመለወጥ ሌላ ወጪ፣ ሌላ ብክነት።
ይህም ብቻ አይደለም፡፡ “የከብቶች እበትና ከሆዳቸው የሚወጣ ትንፋሽ፣ የአለምን አየር ይበክላል” በሚል ሰበብ፣ የከብቶችን ቁጥር በግማሽ መቀነስ ያስፈልጋል ይላል- የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው፡፡
በእንዲህ አይነት፣ ኑሮን የረሱ፣ እልፍ ፀረ ብልፅግና ዘመቻዎች፣ የአለም መሪ መሆን ምን ማለት ነው? ይሄ፣ የሚያስፈራ እንጂ የሚያስጨፍር ጉዳይ አይደለም፡፡ ምናልባት፣ ‹‹በአካባቢው ጥበቃ ዘመቻ አማካኝነት፣ ለድሃ አገራት በየአመቱ 100 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ይመደባል›› የሚል ወሬ ላይ ተማምነው ይሆን?
ይሄ ሞኝነት ነው፡፡ “በእዳ የተዘፈቁት የአውሮፓና የአሜሪካ መንግስታት፣ እንዲህ አይነት ገንዘብ በየአመቱ ይመድባሉ” ብሎ መተማመን፣ ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም – ከሞኝነት በቀር፡፡ እውነታው ደግሞ ከዚህም ያልፋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ተከስተዋል፡፡ ከአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ ጋር ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ራሱ፣ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ግን ይሄ ብቻ አይደለም። “የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻዎችን ለመከላከል ወይም ለማርገብ እታገላለሁ” ብለው ለዜጎች ቃል ገብተዋል፡፡ “በባራክ ኦባማ ዘመን የታወጁ የአካባቢ ጥበቃ መመሪያዎችንና ክልከላዎችን እሽራለሁ” በማለትም በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡
ደግሞም፣ ቃላቸውን ወደ ተግባር እንደሚቀይሩ ከወዲሁ ማሳየት ጀምረዋል፡፡ ማምረራቸው አይገርምም፡፡ በታክስ ጫና፣ በቢሮክራሲ ቁጥጥርና በአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ ሳቢያ፣ የአሜሪካ ኢንዱስትሪ ተብረክርኳል፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት፣ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር በአርባ ሚሊዮን ቢጨምርም፤ በኢንዱስትሪ አማካኝነት የሚከፈቱ የስራ እድሎች አልጨመሩም፡፡ ጭራሽ በአስፈሪ ፍጥነት የስራ እድል ቀንሷል፡፡
ከ18 ሚሊዮን በላይ የነበረው የፋብሪካ ሰራተኞች ቁጥር፣ ዛሬ ወደ 12 ሚሊዮን ወርዷል፡፡ በመኪና ምርት ዝነኛ የነበረችው የዲትሮይት ከተማ፣ የዚህ ውድቀት ምልክት ናት፡፡ ፋብሪካዎች እየተዘጉ፣ ነዋሪዎች ከከተማዋ እየለቀቁ፣ ከአመት አመት ኦና እየሆነች መጥታለች፡፡ ከ400 ሺ ገደማ መኖሪያ ቤቶች መካከል፣ ወደ 100 ሺ የሚጠጉት፣ ነዋሪ አልባ ሆነዋል፡፡ ቤት ለመግዛት የሚመጣ ሰው የለም፡፡
በዚህ የውድቀት አቅጣጫ … በስራ እጥነትና በኑሮ ችግር የተቆጡ አሜሪካዊያን በእጅጉ እየበዙ በመምጣታቸው ነው፤ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ያሸነፉት፡፡ ቢዝነስ እንዲስፋፋና የስራ እድል እንዲፈጠር … ታክስ እቀንሳሁ፣ መመሪያዎችን እሰርዛለሁ፤ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻዎችን እገታለሁ በማለት፣ ብዙ ድጋፍ አግንተዋል፡፡
ለቅስቀሳ ያህል ብቻ ሳይሆን፣ ከምራቸው እንደሆነ ማወቅ ይቻላል? አዎ፡፡ ምልክቶች አሉ። የአገሪቱን የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ እንዲመሩ፣ በዶናልድ ትራምፕ ለሹመት የታጩት ማን እንደሆኑ ማየት ነው፡፡ “በኤጀንሲው የታወጁ የክልከላ መመሪያዎችን በመቃወም ተወዳዳሪ የላቸውም” የተባሉ የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ ናቸው ለሹመት የታጩት፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻን እንዲመሩ ሳይሆን፣ ዘመቻውን እንዲገቱ ነው የታጩት፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡
በተባበሩት መንግስታት አማካኝነት የሚካሄዱ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻዎችንም ለመግታት ያሰቡ ይመስላል፡፡ በዩኤን የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ በትራምፕ የተመረጡት ኒኪ ሄኪ፣ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻን በመቃወም የሚታወቁ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡

No comments:
Post a Comment