ወያኔ እና ሻዕቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ! ቢለያዩም ስለ አማራ ከሆነ ሁሌም አንድ ናቸው ! ኄኖክ አሺጥላ
አማራይ ሃድጊ ወዲ ሰበይቲ
ሪኢካዮ ዶ እድቂ ናይ ተጋደልቲ
ሪኢካዮ ዶ እድቂ ናይ ተጋደልቲ
«አማራ አህያ የሴት ልጅ
አየኸው ወይ ትጥቅ የተጋዳዮች »
አየኸው ወይ ትጥቅ የተጋዳዮች »
ይህንን ዘፈን ሻዕቢያዎች አማሮችን ሲያባርሩ የዘፈኑት ዘፈን ነበር። ጉራጌ ወይም ኦሮሞ ብለው አልነበረም የዘፈኑት። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ሰራዊት አማራ ብቻ ነበርን? የጦር አዛዦቹ እና አማካሪዎቹ በአብዛኛው ኤርትራዊያኖች፥ የትግራይ ሰዎች ፥ የደቡብ ሰዎች እና ኦሮሞዎች አልነበሩምን?
የአስመራ ተፈናቃዮች ይህንን ዘፈን የት ነው የምታስታውሱት ? የቃኘው ልጆች ? የ 35ኛ ክፍለ ጦር ( ገጀረት ) ልጆች ? የ 12ኛው ብርጌድ ልጆች ? ትዝ ይላችኋል ?
ሲቆይ ይረሳል!
ሲቆይ ይረሳል!
የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ( ቁስለኞች ) እንዴት እንደሞቱ ትዝ ይሏችኋል? በቆሻሻ መኪና ከነ ህይወታቸው እንደተቀበሩ ታውቁ ይሆን? በኤርትራ ይኖሩ የነበሩ አማሮች ከኤርትራ ሲባረሩ አህያ ኮፍያ እና ከረባት አልብሰው « ነይ ዘመዶችሽን ሸኚ» ብለው በአደባባይ አማራን ከአህያ ጋ ማዛመዳቸውን ረሳነው ? የመቀሌ ትግሬዎች ከኤርትራ የተባረሩ አማሮችን በድንጋይ ይደበድቡ የነበረውንስ ረሳነው ? ዛሬ ማን ከማን ተሽሎ ነው እያወዳደርን ያለነው ?
የአማራ ህዝብ ( በይበልጥም የአማራ ልሂቃን ) ይህንን እውነት ወደፊት መጥቶ ለማስረዳት ስንት ዘመን እንጠብቃችሁ ? የአማራ ወጣቶች « ሲደምቅ እንገባለን» ከሚል አመለካከት ወጥታችሁ ህዝባችሁን ከጥፋት ለመታደግ የምትነሱበትን ቀን ንገሩን ? !!!!!
አማራ ፈሪ አይደለም! አማራ ቂመኛ ህዝብም አይደለም! በደሉን ግን አይረሳም!
ኤርትራ የአማራ ህዝብ መቀበሪያ እንጂ መጠናከሪያ አይደለችም ! አማራ በራሱ ምድር ፥ በራሱ ቋንቋ እና በራሱ ህዝብ መሃከል የሚያደርገው ትግል ነው ነፃ የሚያወጣው!
ኤርትራ የአማራ ህዝብ መቀበሪያ እንጂ መጠናከሪያ አይደለችም ! አማራ በራሱ ምድር ፥ በራሱ ቋንቋ እና በራሱ ህዝብ መሃከል የሚያደርገው ትግል ነው ነፃ የሚያወጣው!
ወያኔ እና ሻዕቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ! ቢለያዩም ስለ አማራ ከሆነ ሁሌም አንድ ናቸው !
አማራ ተነስ!
ኄኖክ አሺጥላ
No comments:
Post a Comment