Saturday, December 17, 2016

ብሞትም እንዲቀብረኝ ልጄን ቢለቁልኝ ደስ ይለኛል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት


“ብሞትም እንዲቀብረኝ ልጄን ቢለቁልኝ ደስ ይለኛል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ታስሮ ይገኝበታል በተባለው ዝዋይ እስር ቤት እንዳጡት ሲገልጹ የቆዩት ቤተሰቦቹ በዛሬው ዕለት በዐስረኛ ቀኑ እንዳገኙትና ለአምስት ደቂቃ እንዳዩት ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። እናቱ ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳው ታማሚ መሆናቸውን ገልፀው የእስር ጊዜውን ስለጨረሰ በአመክሮ እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት ባለቤት እና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት በጹሑፍ ሥራዎቹ “በሀሰት ወሬ መንዛት” በሚል ክስ ቀርቦበትና “ጥፋተኛ” ተብሎ የተፈረደበትን የሦስት ዓመት እስራት ለመጨረስ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ይገኛል።
በዚህ ማረሚያ ቤት ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር እንዳስቆጠረ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንደም አላምረው ደሳለኝ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገረው፤ በዛሬው ዕለት ዝዋይ እስር ቤት ወንድሙን ፍለጋ የሄደው ለመሞከር እንጂ አገኘዋለሁ በሚል ተስፋ አልነበረም።
ጽዮን ግርማ የጋዜጠኛ የመስገን ደሳለኝን እናትና ወንድሙን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

No comments:

Post a Comment