በቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት በስሙ በተሰየመው ኣደባባይ ላይ ተቀርጾ የሚገኘው የቦብ ማርሊ ሃውልት ሊፈርስ ነው
የአደባባዩ ኣለቦታው መገንባት የትራፊክ ፍሰቱን የተጨናነቀ በማድረጉ በሌሎች ስፍራ ሲደረግ እንደቆየው አደባባዩን ኣፍርሶ በትራፊክ መብራት ለመተካት እንደታሰበ እና ይህም እቅድ ወደ ተግባር ከመገባቱ በፊት ግን ፡ ተለዋጭ ቦታ እንዴት ይሰጠው እና በምን መልኩ ይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል ።
ይህ የቦብ ማርሊ ሃውልት መገንባቱን ተከትሎና እስከዛሬም ድረስ የሃውልቱን እዛ ቦታ መገኘት በሚደግፉና በሚቃወሙ የህብረተሰብ ክፍሎች መሃከል ብዙ ኣሉታዊና አወንታዊ አስተያየቶች ሲሰነዘሩበት የቆየ አጨቃጫቂ ሃውልት ነው ። ከቦብ ማርሊ የበለጠ ለዚች ሃገር ሰርተው በዋና መንገድ ላይ የተሰራ አደባባይ እና ሃውልት ይቅርና ትንሽ ጎዳና በስማቸው ያልተሰየመላቸው ሰዎች እያሉ ለሃገራችን ይሄ ነው የሚባል ፋይዳ ላልሰራ ሰው ለምን ሃውልት ይቆማል በሚሉት እና ድምጻዊውን እንደ የጥቁሮች ነጻ ኣውጭና የነጻነት ታጋይ አድርገው በሚቆጥሩት መሃከል ያለው ውዝግብ ሳይቆም ሃውልቱን ከስፍራው ለማንሳት መታቀዱ ታውቋል

No comments:
Post a Comment