Friday, December 23, 2016

ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። Olympic Medalist Athlete Miruth Yifiter Died


ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። Olympic Medalist Athlete Miruth Yifiter Died
 
ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር አገሩን ያስጠራ ብርቅ ኢትዮጵያዊ በካናዳ ቶሮነቶ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፉን አረጋግጠናል ። በ1972 ዓ.ም በሞስኮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 እና 5000 ተወዳድሮ ሁለት ወርቅ በማስመዝገብ ማርሽ ቀያሪው በመባል ይታወቃል። 1964 ዓም በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡
አትሌቱ 1965 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታ አንድ ወርቅ በ10,000 እና አንድ ነሐስ በ5000 ሜትር ለሀገራችን አስመዝግቧል፡፡ በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በ5000እና በ10,000 ሁለት ወርቅ በማስመዝገብ ድንቅ ብቃቱን ያሳየ እና የሀገራችን ስም በአለም ያስጠራ አትሌት ነው። አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ባጋጠመው የጤና ችግር በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ህይወቱ አልፏል። ነፍስ ይማር ። ለመላው ኢትዮጵያውያን ፅናቱን ይስጠን ።
Miruth Yifiter Died
Miruth Yifiter Died

No comments:

Post a Comment