ምንሊክ ሳልሳዊ – ቀና አስተሳሰብን የመሰለ ነገር የለም!! ጆሮውን እና አፍንጫውን ግጥም አድርጎ ጠቅጠቆ ደፍኖ የጥላቻ ፖለቲካ የሚ*ሳ በማሕበራዊ ድረገጽ እንደ አሽን ፈልቷል። ይህ ከሆነ ታዲያ አንድነት ሃይል ነው ፍቅር ያሽንፋል ብሎ መስበክ ለምን አስፈለገ መጀመሪያ ችግርን መመርመር ያስፈልጋል ችግር ሳይመረመር መፍትሄ አይመጣም።
ችግርን መርምሮ መፍትሄ ኣለመፈለግ ዳግም ችግር ከመፍጠሩም አልፎ ወደ ንትርክ ይወስዳል። ጭፍን ጥላቻ ይሁን ጭፍን ድጋፍ ለሃገር አይበጅም። ለዚህም ነው ሰከን ብሎ መደማመጥ መከባበርን እና መቻቻልን ይፈጥራል የምንለው። በኢሕአዴግም ይሁን በተቃዋሚዎች\በለውጥ ሃይሉ በኩል የእርስ በእርስ ሽኩቻውና የጎንዮሽ ውጋቱ የተንሰራፋው ሀገራዊ ራእይ ላይ አትኩሮት አለማድረጉ እየሰፋ በመምጣቱ ነው።
ስለ ኢትዮጵያ የምንል ወገኖች ጉዳዩን በጥልቀት እና በቅንነት ብናበጃጀው የተሻለ ነው።ካልሆነ ነገም እንደዛሬ ይሆንብንና መጣፊያው ያጥረናል። ለውጥ አስተሳሰባችንን መቀየር ይሻል፡፡ በጎታች አስተሳሰብ ከተያዝን የለውጥንም መምጣት የኋሊት እንጎትተዋለን፡፡ #ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment