Tuesday, December 27, 2016

በለገጣፎና ለገዳዲ ለአመጽ የሚቀሰቅስ ወረቀት በትነዋል በሚል በርካታ ወጣቶች ታሰሩ | የአማራ ወይም ኦሮሞ ወጣት መሆን በኢትዮጵያ ወንጀል እየሆነ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በለገጣፎና ለገዳዲ አካባቢ ሕዝቡን ለአመጽ የሚቀስቀስ ወረቀት በትነዋል በሚል በርካታ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
የሕወሓት መንግስት የውጭ መንግስታት ጫና ሲያበረቱበት የተወሰኑ ሰዎችን ፈትቶ ታዛዥ መሆኑን ለማሳየት ከሞከረ በኋላ እንደገና ከተፈቱ ሰዎች በ እጥፍ የሚሆኑ እየታሰሩ መሆኑ ታውቋል::
በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙት ለገዳዲ እና ለገጣፎ አካባቢ የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸውን የት እንደሚደብቁ እንደማያውቁ የሚናገሩት ምንጮቻችን በዚህ አካባቢ የሚኖሩት ወጣቶችም ለስደት እየተዳረጉ መሆኑም ተሰምቷል::
የሕወሓት መንግስት በአሁኑ ወቅት በርካታ ወጣቶችን እስር ቤት ገብቶ በማሰቃየት ሕዝቡን ለማሸማቀቅ እየተጠቀመበት ነው የሚሉት ምንጮቻችን በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ኦሮሞ ወይም አማራ ወጣት ሆኖ መገኘት ወንጀል ነው ብለዋል:: በየማሰቃያ እስር ቤቶች ውስጥም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች መከራቸውን እያዩ ይገኛሉ::

No comments:

Post a Comment