Tuesday, December 27, 2016

የ21ኛው ክፍለ – ዘመን የአማራ ይሁዲ (ማተቤ መለሰ ተሰማ) (ማተቤ መለሰ ተሰማ)

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ ከጀርመኑ ናዚ ሺህ ጊዜ የከፋና በዚህ ዘመን ሰው ያደርገዋል ተብሎ የማይታስብ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።
ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን ህዋሃት ገና ከመነሻው በማንፌስቶው አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው። በማለት አስፍሮና እቅድ ነድፎ እየሰራበት የመጣ ከመሆኑም በላይ ህዝብን ሳያፍሩ መለስ ዜናዊ ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሳሞራ የኑስና ተፈራ ዋልዋ በአግኙት አጋጣሚ ሁሉ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃየማኖት ተከታዩን ላይነሳ አርቀን ቀብረነዋል በማለት ሲነግሩን ኖረዋል። የጥፋት መልዕክተኛው ቡድን ህዋሃት ከደደቢት ተነስቶ እየተስፋፋ ሲሄድ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀስበት ወቅት ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረገው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለወያኔዎች ግን ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ በመልቀም ጨፈጨፋቸው።
ህጻንና ሽማግሌ እንኳን ሳይመርጥ በጅምላ እየርሽነ በመቅበር የቀጠለው። በውጊያ ወቅት የሚማርከውን ወታደርም ዘሩን በመጠየቅ አማራ ነኝ ያለውን በመግደል ሌላውን ግን ፍላጎቱን እየጠየቀ ወደቤቱ ይልከው፣ ወይንም ከጎኑ ያሰልፈው ነበር። ይህን እንድል የመንፈው ጉልበት የሆነኝ በአይኑ ያየ ሰው ስላረጋገጠልኝ ነው። ማስረጃየ አሁንም በህይወት ስላለ ቀን ሲወጣ ወይንም እንደኔ ከሃገር ሲሰደድ ምስክርነቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚናገር ለደህንነቱ ስል በስም አልጠቅሰውም። ታሪኩ እርጅም ነው ግን በአጭሩ ላቅርበው።
ነገሩ እንዲህ ነው በደርግ ዘመን በዚያኔ አጠራር ነው የምጠቀመው። በጎጃም ክፍለሃገር፣ በቆላ ደጋዳሞት አውራጃ ውስጥ ከሚገኙ 7 ወረዳዎች መካከል ቡሪ ሽህኩዳድና ጓጉሳ ወንበርማ ወረዳ። ነዋሪ የሆኑ ኦሮሞኛን ከአማርኛው እኩል የሚናገሩ ሰዎች በርካታ ናቸው። ከዚህ ማህበረስብ መካከል 2 ወንድም አማቾች ታፍሰው ወደ ብሄራዊ ውትድርና ይገባሉ። የወጣቶቹ ግዳጅም ትግራይ ክፍለሃገር ይሆናል። በአንድ የተረገመች ቀን ግን ሁለቱም ይማርኩና በሺ ከሚቆጠር ሌላ ምርኮኛ ጋር ይቀላቀላሉ። ዋል አደር እንዳሉም የህዋሃት ባለስልጣናት ምርኮኛው ወደስፈረበት በመሄድ።
ዘሩን እየጠየቁ አማራ ነኝ ያለውን ለብቻ ከሌላ ብሄርስብ ነኝ ያለውን ለብቻ ሲያሰልፉ። ከጎጃም ለሄዱት ወንድም አማቾች ተራ ይደርስና መጀመሪያ የተጠየቀው ታናሹ አማራንኝ ስላለ የአማራው ምርኮኛ ወዳለብት እንዲስልፍ የደርጋል። ታላቁ ሲጠየቅ ኦሮሞ ነኝ በማለቱ ቋንቋን እንዲያወራበት ተደርጎ አቅላጥፎ ስለሚናገር ሰልፉ ከሌሎች ጋር ይሆናል። በዚህ ሁኔታ ማጣራቱ እንዳለቀ አማራነኝ ያለው መርኮኛ እንዲገደል ተወሰነበትና በመትረየስ ተረፈረፈ። ሌላው ግን ቅድም እንዳልሁት ፍላጎቱ እየተጥየቀ ተስናበተም አብሮ ለመታገል የወሰነም ተስለፈ። ወንድሙ አማራነኝ በማለቱ ሲገደል እሱ ኦሮሞነኝ በማለቱ የተረፈው ከተስናባቾቹ አንዱ ሆንና በወሎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ እኔ ያኔ ደብረብርሃን ስለነበርሁ ተቀብየው የተወሰኑ ቀናት እኔጋ አርፎ ስለነበር ነው ድርጊቱን ያጫወተኝ። ሌላው ህዋሀት ከተማራኪ ወታደሩ ውስጥ አማራውን እየመረጠ በመግደል እንደመጣ የሚያሳየው መረጃ አንድም የአማራ ምርኮኛ ወታደር እንደ እነ አባዱላ ገመዳ፣እንደነ ኩማ ደመቅሳ፣እንደነ ባጫ ደበሌ፣ እንደነ አለማየሁ አቶምሳ ወዘተ አብሮት እየስራ ያለ አንድም አማራ አለመኖሩ ነው።ምክናያቱም የተማረከውን አማራ ሁሉንም እየግደለ ነው የመጣውና። ህዋሃት በትግል ላይ ሳለ በትግራይ ክፍለሃገር ይኖሩ የነበሩ አማራወችን ብቻም አልነበርም እይገደለ የመጣው።
የወልቃይት፣ ጠገዴና የአርማጭሆ ነዋሪ የሆነውንና ይህንን ለም ቦታ ወደትግራይ ስንከልለው እኛ ጎንደሬ እንጅ ትግራይ አይደለንም በማለት ተቃውሞ ሊያስነሳብኝ ይችል ይሆናል ብሎ የገመተውን ሁሉ በስውር እየገደለ በመቅበር ነው የምጣው። ታምራት ላይኔ እንዳለው ህዋሃት በጦርነቱ ወቅት የአማራ ክልልን ውሱን መሰርተልማት እያፈራረስ፣ ንብረቱን ጠረጴዛና ወንበር ሳይቀር እየዘረፈ ወደትግራይ በማጋዝ ነው አዲስ አበባ የገባው። ወያኔ በምዕራባውያን ሃአገሮች ሙሉድጋፍ የኢትዮጵያን መንግስትነት በትረ ስልጣን ከጨበጠ በኋላም የመጀመሪያ ስራው ያደረገው። ሌላው ኢትዮጵያውያን በአማራው ሕዝብ ላይ እንዲነሳ መቀስቀስ ነበር። ለዚህም አመች ሆነው የተገኙት በአማራው ስም ሲነግዱና ደሙን ሲመጡ አጥንቱን ሲግጡ ሲያስግጡ የኖሩት ሁለቱ ባንዳዎች ማለትም ታምራት ላይኔና ዳዊይት ዩሃንስ ነበሩ። ያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረው ታምራት ላይኔ በሃረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሴ፣ በአፋርና በሶማሌ ከልሎች። አፈጉባኤ የነበረው ዳዊይት ዮሀንስ ደግሞ በጅማ፣ በወለጋ፣ በኢሉባቦር ወ.ዘ.ተ. እየተዘዋወሩ። ይህ አማራ የተባለ ነፍጠኛ ለመቶ አመታት ሲዘርፍህ፣ ሲገፍህ ሲያሰቃይህ ኖሯል። ኦሮሞውን ከብት፣ ሱማሌና አፋሩን ሽርጣምና ግመል ጎታች እያለ ሲያሸማቅቅህ ኖሯል። አሁን ሜዳውም ፈረሱም እነሆ አማራው ከናንተ መሃል ምን ይሰራል፣ በማለት ቀስቀስው እንደተመለሱ። በአሰቦት ገዳም፣ በበደኖ፣በወተር፣ በጋራሙለታ፣ በገለምሶ፣ በአንጫር፣ በዳኖለቡ፣ በወፌ ዳንሴ፣በዳጉ፣ በጨሪቻ፣ በበዴሳ፣ በድሮባ፣ በአሬሌ፣ በደደር፣ ወዘተ። እንዲሁም ኢሰመጎ ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው በአርሲ በአርባጉጉ፣ አውራጃ በአስኮ፣ በጉና፣ በጮሌ ወረዳዎች አማራው እየተመረጠ ህጻናትና ነፍስጡር ሴቶች ሳይቀር። አነገቱ በሰይፍ እየተቆረጠ፣ እራሱ በፋስ እየተፈለጠ፣ ሆዱ በሳንጃ እየተዘነጠለ፣ ከእነ ህይወቱ በገደል እየተጣለ፣ ከሁለት መቶሺህ በላይ አማራ ያለ እርህራሄ አልቋል። በዚህ ወቅት አሶሳ ውስጥ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠር አማራ ከያለበት ተሰብስቦ በሳርቤት ውስጥ እንዲገባ ተደርጎና በር ተዘግቶበት በእሳት ተቃጥሏል።
በጣም ዘግናኙ ደግሞ ከተጨፈጨፈው አማራ ውስጥ ከአካሉ የተቆረጠውን ስጋ እንዲበላ መደረጉ ነው። የገዛ ስጋውን (የእራሱን ስጋ) እንዲመገብ ከተደረጉት መካከል ጋራ ሙለታ ውስጥ በእህል ንግድ ትተዳደር የነበረችዋና ጡቷን ቆርጠው ካበሏት በኋላ የገደሏት እታፈራሁ ዳኘ ተጠቃሽ ናት። በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ። በደቡብ ክልል ከጉራ ፈረዳ 75000። ከቤንሻጉል ክልል በመተከልና ከማሽ ዞኖች 25000 በድምሩ 100000 መቶሺህ አማራ በመብራት እየተፈለገ ለዘመናት ለፍቶ ያጠራቀመውን ሃብት ንብረቱን ተዘርፎ እንዲባረር ተደርጓል አሁንም ማፈናቀሉ እንደቀጠለ ነው። ታምራት ላይኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር በነበረበት ባንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር። “የትምክተኛውንና ነፍጠኛውን የአማራ ስርዓት እንዳይመለስ አድርገን አሰናብተነዋል። ምናልባት እኛ በህይወት እያለን፣ በታምር እንደሚመለስ ከተረዳን ግን ቅድሚያ “መሰረቴ ነው የሚለውን ክልል” ውስን መሰረተ ልማቱን ዶጋ አመድ አድርገን ተጨማሪ ሊማሊሞ ገደል እናስረክበዋለን። ገደል ላይ ደግሞ ምን ያህል ሊቆይ እንደሚችል እድሜ ካለን የምናየው ይሆናል። ሌላዉ አለ ታምራት ቀጠለና፣ ሌላዉ ነፍጠኛው የአማራ ተመልሶ አንገቱን እንዳያቀና ጭራቅነቱን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ልጆች ለማሳወቅ በመደበኛ ትምህርት መስጠት መንግስታዊ ግዴታችን ነው።”በማለት ነበር የዛተው። ጸረ አማራው ታምራት ላይኔ በአማራው ላይ ያለመውን ጥፋት የመተግበር እድሉን ቢያጣም።
የምግባር ጓዶቹ እራዩን አሳክተውለታል። ማለትም በልማትና በሃብት ክፍፍል አምስት ሚሊዮን የማይሞላው የትግራይ ህዝብና ከሃያ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የአማራ ህዝብ ልዩነት የሰማይና የምደር ያህል የተራራቀ ነው።ባሳለፍነው እሩብ ምህተ አመት ውስጥ በአማራው ክልል ከዳሽን ቢራ በቅር እዚህ ግባ የሚባል ዘመናዊ ኢንዱስትሪ አልተተከለም። ትግራይ ክልል ግን ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪ የተጥለቀለቅች ናት። ለማዕከላዊ መንግስት ምንም አይነት ፈሰስ የማያደርገውና ለትግራይ ልማት ብቻ የሚስራው የ53 ቢሊዮን ብር ሃብት ያካበተውና 70 የተለያዩ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎ የሚገኘው ኢፈርት። ግዙፎቹን ኢንዱስትሪዎች ማለትም ሞሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካን፣ መስፍን ኢንጅነሪንግን፣ ሱር ኮንስትራክሽንን፣ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን፣ ጉና ቢዝነስን፣ ኢዛና ወርቅ፣ ሜጋ ኔት ኮርፖሪሽን ወዘተ በሃገሪቷ ገንዘብ ተቋቁሞ ጥቅሙ ግን ለትግራይ ብቻ ከመሆኑም በላይ እንኝህ ድርጅቶች ከባንክ የተበደሩት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በተበላሽ ብድር እንዲመዘገብ ይደረጋል እንጅ አንድ ሳንቲም እንኳን ለአበዳሪው ባንክ ተመልሶ አያውቅም። ሌላው የፌዴራሉ መንግስት አመታዌ በጀት ሲመድብ በህዝብ ብዛት አራትና አምስት እጥፍ ከሚበልጡት ከአማራና ኦሮምያ ክልሎች በእጥፍ የሚበልጥ ገንዝብ ነው ለትግራይ ክልል የሚመደበው።
እዚህ ላይ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ትግራይን በማንጻጸሪያነት ሳነሳ የትግራይን ህዝብ በመጥላት አይደለም። የህዋሃትን ክፋትና ጥፋት ለማሳየት እንጅ። ለነገሩ ወያኔ ጥቂት የማይባል የትግራይ ነዋሪን። አማራ ጠላትህ ነው በማለት አሳምኖታል። ምክናያቱም በአቶ አለም ሰገድ አባይ ጥናታዊ ጽሁፍ ወይንም መጻፍ ላይ የትግራይ ህዝብ ጠላትህ ማነው ሲባል 81% አማራ ነው እንዳለ ተመዝግቧል። አማራው ግን የትግራይን ህዝብ ጠላት ብሎ አያውቅም። አማራው በጅምላ የሚታረደው፣ በገፍ የሚፈናቀለውና ከምር የተገፋው በሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊና አካባቢ በቻ አይደለም። ክልልህ ነው በተባለውም በከፋ ሁኔታ የቀጠለ ነው እንጅ። የአማራ ክልል መሪ ሆኖ ለረጅም አመት የገደለው ያስገደለው ያሰደደው አዲሱ ለገሰ ። የስራ መጀመሬያ ያደረገው። አማራው በማንንቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ፣ አንገቱን እንዲደፋ ሞራሉ፣ ምግባራዊ ድፍረቱና ሰባዊመብቱ ከውስጡ እንደጭስ እየተነነ እንዲጠፋ ለማድረግ በአንድ ወይንም በሌላ መንገድ ከማህበረሰቡ የተገለሉ፣ እንደነ አለምነው መኮንን አይነት ታሪካቸውን ለጥቅማቸው፣ ሰብናቸውን ለሆዳችው አሳልፈው የሸጡ ባንዳ ዎችን በመመልመል በዘለፋና በስድብ አሰልጥኖ በማሰማራት ህዝብን በጀምላ ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ጥገኛ፣ ቢሮክራት ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ውርጀብኞችን በስፋት ማሰራጨትን ነበር።
በቀጣይ በአመት ሁለት ጊዜ እርጭት በማካሄድ ላይ ያለውን በአማራ ክልል ከረጅም አመታት ጀምሮ የነበረውን የወባ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጠቅላላ በመዝጋት ከ1984 እስከ 1987 ድረስ የወባ ወረርሸኝ ገብቶ ከአንድ ቀበሌ በቀን ከ10 እስከ 15 የሚደርስ ሰው እየሞተ ቀባሪ እንኳን ያጣበት ሁኔታ ሲከሰት በአዲሱ ለገሰ የሚመራው የአማራ ክልል መንግስት እንደ መንግስት አንድም የመከላከል ሙከራ አላደረገም። በወባና ሌሎች ሰው ሰራሽ በሸታወች ያለቀው አማራ ሳያንስ ቀሪው ደግሞ እንዳይወልድ በጤና ተዋልዶ ፕሮግራም ሰበብ አሁንም በየትኛውም አካባቢ ያልተሞከረውን፡ የአማራ ወንድ አርሶ አደሩን በገንዘብ በማባበል፣ እንቢሲል መሪትህን እንነጥቅሃለን እያሉ በማስፈራራትና በማስገደድ ወደፊት ዘር እንዳይተካ የዘር ብልቱን በሀኪሞች እንዲነኮላሽ በማድረግ። ሴቱ እንዲመክን መርፌ በመውጋት የዘር ማጥፋት ዘመቻውን በከፍተኛ ደረጃ አካሂደውበታል። ዛሪም ይህ እኩይ ድርጊት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም በሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴን ለትግራይ ለማድረግ ነባሩን ህዝብ ማጥፋት፣ የሚተርፍ ካለም ማዳቅል የሚል መሪ ፕሮግራም በመንደፍ ማምከኑም ሆነ መግደሉ በከፋ ሁኔታ ቀጥሏ። ከሞትም ሆነ ከመምከን የምትተርፍ ሴት ካለች ተገድዳ ከትግራይ ተወስዶ ለሰፍረው ወንድ ሶስተኛም ሆነ አራተኛ ቅምጥ ሆና እንድትወልድ በመደረግ ላይ ነው። በሌላ በኩል ነግዶ አደሩን በዝባዥ፣ ጥገኛ ባለሀብት በማለት።
እንደ ዶሮ ከጉልበቱ በላይ ለብሶ ያለመጫሚያ የሚኳትነውን አርሶአደር ደግሞ ቢሮክራት፣ ንክኪ በማለት፡ ንብረትና መሪቱን በመንጠቅ፡ ቅዬውን እየለቀቀ እንዲሰደድ፡ በማድረጋቸው 1993 ዓ.ም ህግና መንግስት ያለ መስሎት፡ አዲስ አበባ ድረስ ተጉዞ ፒያሳ ከሚገኜው ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመስፈር የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር እየተፈራረቀበት እራብና ጥም እያሰቃየው ፍትህ ቢለምንና ቢማጸን ከወያኔ መንግስት ያገኘው መልስ ድብደባ እስራትና ግድያ ነበር። በዚህ ወቅት ከ80 የማያንሱ ሰዎች ለአቤቱታ እንደወጡ በወያኔ ደህንነቶች ታፈነው የት እንደደረሱ እስካሁን አይታወቅም። የተረፈው ሕይወቱን ለማሰንበት ሲል ወደወለጋ በመሄድ ጦማደር መሪት መርጦ ስፍሮ መኖር ሲጀምር ደገሞ የወያኔ ካድሪዎች ወራሪ ጠላት የመጣበት በማስመሰል የአካባቢ ኗሪ የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነውን ማህበረሰብ ቀስቅሰው በማስነሳት ከአማራ ክልል ሄዶ በሰፈረው ህዝብ ላይ ጦርነት አስከፍተው ሴትና ሕጻናትን እንኳን ሳይተው በጅምላ በመጨፍጨፍ ከ6000 ያላነሰ የአማራ ህዝብ እንዲያልቅ ተደርጓል። ከዚህ ተርፎ ምንም ንብረት ሳያንጠለጥል ሚስት የባሏን፣ ባል የሚስቱን፣ወላጅ የልጁን፣ ልጅ የወላጁን፣ እሪሳ እየተራመደ አባይን ተሻግሮ ጎጃም ቡሪ ከተማ ሲሰፍር የማስተናገድ ሃላፊነት የነበረባቸው የአማራ ክልል ባለስልጣናት ዞር ብለው አለማያት ብቻ ሳይሆን ግብርሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡት እርዳታ ፈጥኖ እንዳይደርስ ቢሮክራሴያዌ መሰናክል በመፍጠር በርካታ መዳን የሚችሉ ቁስለኞች እንዲሞቱ አድርገዋል።
በእነዚህና የመሳሰሉ የረቀቁ የዘር ማጥፋት ዘዴዎች ያለቀውን አማራ በተመለከተ ከዛሪ አምስት አመት ገደማ በፊት በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ሪፖርት 2.4 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ እንደተወገደ ለፓርላማው በኩራት ተገልጿል። በተዘዋዋሪ የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻችን በእቅዱ መሰረት ግቡን እየመታ ነው የሚል ሪፖርት እንደሆነ ነው ለእኔ የሚሰማኝ። እውነቱ ግን በወያኔ የተገደለውና
የተሰደደው፣ በእየ እስር ቤቱ የታጎረው ቢደመር 2.4 ብቻ ሳይሆን 5 ሚሊዩን ይደርሳል። ወንዱ የዘር ብሉቱ በመኮላሽቱ፣ ሴቷ አምካኝ ክትባት መርፌ በመወጋቷ የመከነው 10 ሚሊዮን በድምሩ በዚህ 26 አመት ውስጥ 15 ሚሊዮን አማራ አልቋል ማለት ይቻላል። አማራው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ባይከፈትበት ኖሮ በአሁኑ ወቅት ከ35 እስከ40 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። በአኳያው በደርግ መንግስት ኤርትራን ጨምሮ የትግራይ ህዝብ ብዛት 5 ሚሊዮን እንኳን አይሞላም ነበር። ዛሪ ግን የትግራይ ህዝብ ብዛት ብቻውን 4,316,988 ደርሷል። የአማራው ህዝብ በወያኔም ሆነ በሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኑ እንዲህ እስከመጨረሻው ዳር ድረስ ሊገፋ የቻለበት ምክናያት ምንድን ነው? እንደዚህ በእየቦታው የሚሳደደው፣ የሚገደለው፣ የሚዘረፈው፣ የሚገፈፈው፣ የሚዋረደው ለምንድን ነው? ምን ስለአጠፋ ነው? አስቀድሞ የተሰራ በደል ካለስ? ያሁኑ ትውልድ የቅድመ አያቱን እዳ መክፈል አለበት ወይ? ደግሞስ የትኛው መሪ ነበር አማራና ዛሪ አማራ እዳ ከፋይ የሚሆነው። ፕሮፌስር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ በሚል እርዕስ ባሳተሙት መጽሃፋቸው። አማራው በወታደርነት ለእናት አገሩ አጥንቱን ከመከስከስ፣ ደሙን ከማፍሰሥ በቀር ገዥ ሆኖ እንደማያውቅ ሲያስረግጡ እንዲህ ብለዋል።
አማራው ከሰለሞናዊው ስርወ.መንግስት ጀምሮ ዋናው የስልጣን ባለቤት እንደነበር ተቆጥሮ ከሲቪልም ሆነ ከወታደራዊ ስልጣን ተገልሎ 40 አመት ሙሉ ለዘር ጥቃት ሲጋለጥ፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰቃይና ሲገደል ኖሯል። እውነቱ ግን አማራው ኢትዮጵያን እንደ ስርወ.መንግስት አልገዛም እንዲያውም ባለፉት 700 አመታት ከአማራው ይልቅ ኦሮሞው የስልጣን ባለቤት ነበር። ወዘተ እያሉ አማራው የሚወነጀልበትን አግባብ የሞግታሉ። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ የአማራው ባልበላው ሲወገዝ፣ ባልስራው ሲኮነን፣ ከየአቅጣጫው ይህ ሁሉ ማት ሲወርድበት ለምንድን ነው ዝም ብሎ የተቀመጠው? በእውነት ወያኔ እንደሚለው ፈሪና ሽንታም ስለሆነ ነው? በእውነት አማራ እራሱን መከላከልና ቃታመከፈት፣ ምላጭ መሳብና አልሞ መተኮስ የማይቸል ደካማ ፍጡር ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ዘወትር እንደ ስራት አልባ የጉንዳን ሰራዊት በአእምሮዬ እንደተተራመሱ መልስ ሳያገኙ ቀንን ቀን፣ እየተካው የማያቋርጠው የወራት ጎርፍ እያጋፈለ አልፎ ጊዜ በነበር ጢሻውስጥ በመስረግ ላይ ነው።
እዚህ ላይ ከሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ግጥም አንድ ስንኝ ልዋስ አትንኩኝ ባይ ነበር እስከ ትናንትና እረ እግዚወ በሉ ወዴት ሄደ ጀግና እንዳሉት እኔን እንደሚገባኝና በታሪክ እንደማውቀውም አማራው ኢትዮጵያዊ። ትናንት ከእራሱ አልፎ ሀገር ሲወረር ድንበር ሲደፈር ቀድሞ ደርሶ ከአእምሮ፣ ከጉልበት፣ ከጊዜና ከገንዘብ ባሻገር የአካልና የህይወት መሷእትነት ሲከፍል የኖረ ነበር። ባለፉት 42 አመታት ግን ቀኝህን ሲመታህ ግራህን አቅርብለት እንደሚለው ስብከተ ሃይማኖት አይነት አቋም በማራመዱ ተፈርቶ ሲከበርባት በኖረባት አገሩ ተንቆ ከመጠላትና እራሱን መከላከል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሷል። ለምን? ካልን ይህነን ጥያቄ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሊመልሰው የሚገባ ነው ብዬ አስባለሁ። ጥንት አባቶቻችን አነበሶች ነበሩ እኛስ ድመት ሆነ ምንድን ነው ነገሩ እንደተባለው ከእያቅጣጫው እንደዚህ ሲገፋና ይህ ሁሉ የግፍ አዝመራ ሲወቃበት ዝም ብሎ እንዲቀበል ያደረገውን ነገር አንጥሮ በማወቅ ለምን ማለትን መጀመርና ተደራጅቶ ዘሩን ጭርሶ ከመጥፋት መከላከል በአማራነቱ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተገዶ የሚገባበት ሃቅ ይመስለኛል።
የከፋው ሲያለቅስ ደስ ያለው ሲዘፍን ያለው ሞልቶት ሲያፈስ የሌለው ሲለምን እንዳሉት ከቡር ዶ/ር አዲስ ዓለማየሁ ወያኔዎች ሲዘፍኑ ሞለቷቸው የውጭ ሃገር ባንክን በገንዘብ ሲያጨናንቁ አማራው ግን 26 አመት ሙሉ በርሀብ፣ በእርዛት፣ በሰው ሰራሽ በሽታ፣ በዱላ፣ በጎራዴ፣ በሳንጃ፣ በጥይት በገደል፣ በእሳት ወ.ዘ.ተ እንደቅጠል እረግፏል። የተረፈውም ነገ ምን ይደርስብኝ ይሆን በማለት ስጋው በስጋት አልቆ።
ያለምንም በህይወት የመቆየት ዋስትና ቀጣይ መጻቱን በመጠባበቅ ላይ ነው። ዛሪ ዘርቶ መቃሚያ፣ የሚሆነውን መሬቱን ተነጥቆ፣ ወልዶ መሳሚያው፣ ዘሩ መክኖ፣ ፊትም መኖሪያ በኋላም መቀበሪያ ሃገር ተነፍጎና እስከመጨረሻው ተገፍቶ በገዛ ሀገሩ ላይ ስደተኛ ሆኖ ነው ያለው አማራው። እንግዴህ ከዚህ የከፋ ምን እስኪመጣ እንዲጠብቅ ይሆን አማራው በዘሩ መደራጀት የለበተም የሚባለው።???? ነገሩ በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት አያምም ነው። አማራው እኮ የሚደራጀው የፖለቲካ ስልጣን መቆናጠጥ  እፈልጋለሁ፣ የዲሞክራሴ መብት አጥቻለሁ፣ ወይንም እገነጠላለሁ ብሎ አይደለም። እነዚህ በአሁኑ ወቅት ለአማራው ኢትዮጵያዊ ቅንጦቶች ናቸው። የአማራው ትግል የህልውና ትግል ነው፣ የአማራው ትግል ዘርን ጨርሶ ከመጥፋት የመከላከል ትግል ነው፣ የአማራው ትግል በህይወት የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው።
ይሁዲዎች ልክ እንደ አማራው ህዝብ በሁሉም ሲገፉ፡ እራሽያና ኢትዮጵያ ከለላ ሰጥተዋቸው ነበር። አማራውን ግን በወደቀ እንጨት ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ። ቤተክርስቲያን ወይንም መስጅድ እንደገባች ውሻ የሁሉም ክንድ መሞከሪያና አፍ መፍቻ ነው የሆነው፡፡ ይሁዲዎች ዘራቸው ሳይጠፋ ለዛሪው ደረጃ የደረሱት በዝምታ ሳይሆን እራሳቸውን በመከላከላቸው ነው። አማራውስ ዘሩ እንደ ዳይኖሰር ከምድረ ገጽ ጨርሶ ሳይጠፋ ተደራጅቶ መታገል የለበትም ወይ????? ሃገሩን አልከዳ ወገን አልበደለ፣ ምነ እንዲህ ተገፋ ኢትዮጵያን ባለ። እንዲህ ተነገረ በድፍረት ተወራ፣ ሽንታም ነህ ተባለ ዝም ሲል አማራ። አዎ! ሽንታም ነበር እጅግ ዘረ ብዙ፣ አገር አስከባሪ በደሙ በወዙ። በእርግጥ የአማራው ማህበረሰብ ማንነቱ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። የዘር፣ የሃይማኖት የቋንቋ ልዩነትንም አያውቅም።
አማራውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ደምና ስጋ ናቸው። አንዱ ካለ አንዱ የማይኖሩ። ወያኔ በድርጊት ፕሮግራም ነድፎ እየሰራበት ያለውም ትልቁ ስራው ኢትዮጵያን ለማጥፋት በመጅመሪያ አማራንና የኦርቶዶክስ እምነትን ማጥፋትን ነው። ከላይ እንዳልሁት እነመለስ፣ ሳሞራ፣ ሰብሀትና ተፈራም ሲነግሩን የኖሩትና ከመለስ እልፈት በኋላም ቀሪዎቹ እያቀነቀኑት ያሉት ይኸንኑ ሃቅ ነው። አውቃለሁ መራር ነው መራብ መጠማት፣ ቁስሉ አይጸናም እንጅ እንደመጠቃት። አይደል ያለው አበባው በክራሩ። መናቅና መጥቃት አጥንት ድረስ ሰርስቶ በመግባት ያማል፣ ይጠዘጥዛል። ደግነቱ ፈዋሹ መዳህኒት ያለው በታማሚው እጅ መሆኑ ነው። እሱም አሜን ብሎ አለመቀበልና እንቢ ማለት።
አሁን በአማራው ነገድ እጅ ላይ ያለው አማራጭ 2 ብቻ ነው። እሱም 1ኛው ወያኔ የጀመረውን የአማራውን ዘር በማጥፋት እቅዱን ይፈጽም ዘንድ ከፊሉ በምን ቸገርኝ ገመድ ታብቶ እጁን አጣጥፎ መቀመጥ። ከፊሉ ደግሞ እንደስራወር ግንበኛ በአምልካክት ተለያይቶ በሃሳብ ተራርቆ በመቆም ዘርም፣ ሃይማኖትም፣ ሃገርም ሲጠፉ መመልከት ሲሆን። 2ኛው ደግሞ የሌላውን አማራ ለምን ይደራጃል ጫጫታ ጆሮ ሳይሰጥ። የጎንዮሽም ሳይራገጥ። ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደጎን በመተው መነሻውን ነገዱና ዘሩን ከጨርሶ መጥፋት መከላከል። መድረሻው የኢትዮጵያ አንድነትን አድርጎ በመደራጀት ፈርጣማ ክንድ ፍጥሮ ዘርንም፣ ሃይማኖትንም ኢትዮጵያንም ከጥፋት መታደግ የሚሉት ናቸው። አዎ!!! አማራው እስካሁን አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ በመለሳለሱ በሁሉም ወገኑ በሁሉም አቅጣጫ እስከመጨረሻው ጠርዝ ድረስ ተገፋ። ከወገኑ ተለይቶ እንደበግ ታረደ፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሞት ተፈረደበት። ሽንታም ነህም ተባለ አጥንት የሚሰብር ስድብና ሞራልን የሚገድል ውርደት ደረሰበት፡ በአገሩ ላይ ስደተኛ ሆነ። በየሄደበት ተናቀ ተደቀደቀም። አይበቃም ወይ፡????
ኢሜል matebemelese@yahoo.com

No comments:

Post a Comment