Wednesday, December 21, 2016

ከስኳር በሽታ ጋር በተገናኘ የሚመጣ የአይን ችግር


ከስኳር በሽታ ጋር በተገናኘ የሚመጣ የአይን ችግር
————————————————————
ከስኳር ጋር በተገናኘ የሚመጣ የአይን ችግር በአገራችን እየጨመረ ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ፡፡
ከስኳር ጋር በተገናኘ የሚመጣ የአይን ችግር በወጣቶች እና በመካከለኛ እድሜ ላሉ ሰወች አይነ ስውርነትን ከሚያመጡ ዋና ዋና ችግሮች አንዱ ሲሆን የሚመጣውም በስኳር በሽታ ምክንያት ቀጫጭን የአይን ውስጥ(retina) የደም ስሮችን በመጎዳታቸው ነው፡፡
የስኳር በሽታ አይን የሚጎዳው ቀስ በቀስ ስለሆነና የህመም ስሜት ስለሌለው ታማሚው አይን ምርመራ ካላደረግ አይኑ ላይ ችግር እየደረሰ እንደሆነ ሊያውቅ አይችልም፡፡እንዲሁም በሽተኛው ስኳር እንዳለበት ከማወቁ በፊት ምልክቱ ሊኖር እና አይንን ሊያጠቃ እንደሚችል ልንገነዘበው ይገባል፡፡ የስኳር በሽታው እድሜ እየጨመረ ሲሄድ የአይን ችግር የማምጣት እድሉም እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ከስኳር ጋር በተገናኝ የሚመጣ የዓይን ችግርን ሙሉ በሙሉ መከላከል ባንችልም
1. የደም ውስጥ የስኳር መጠን በመከታተል እና በመቆጣጠር
2. የደም ግፊትን ፣ የልብ ችግርን፣የሰውነታችንን የቅባት መጠን በመቆጣጠር
3. ተከታታይ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ
4. ሢጋራ ባለማጨስ እና
5. ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ የዐይን ምርመራ በአይን ህክምና ባለሙያዎች በማድረግ እይታችንን መጠበቅ እንችላለን፡፡

No comments:

Post a Comment