Wednesday, December 21, 2016

ሕወሓት ”የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ” ሊገነባ ነው


ሕወሓት ”የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ” ሊገነባ ነው
መቼስ ፌስ ቡክን ለፈጠረ ሰው ምስጋና ይግባውና የጥቂት ቡድኖች ስብስብ የሆነው የሕወሓት መንግስት የሚሰራቸውን ግድያ ፣እስራት፣ማሰቃየት፣ዘረኝነት፣ስርቆት፣ሙስና፣ዘር ማጥፋት፣በቪዲዮና በፎቶ ጭምር በአይናችን ለማየት ችለናል. ከዚህ ቀደም ይህ ክፉ ስራውን ህዝብ የሚያውቅበት ዘዴ አልነበረም. አሁን በአንድ ጫፍ የሰራው ክፋት በሌላው ጫፍ በደቂቃዎች ከነምስሉ ይደርሳል. በአሁኑ ሰአት ከ4 ሚሊዮን በላይ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ በመኖሩ ሕወሓትን በእጅጉ አሳስቦታል .
ሕወሓቶቹ ልከዋቸው ጠ/ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ሳይቀር ሄደው የአለም መንግስታትን ፌስ ቡክ አስቸገረን አንድ ነገር አድርጉልን እስከማለት ደርሰው ተስቆባቸው ተመልሰዋል. ባገኙት ሚዲያ ሁሉ ፌስ ቡክ ውሸታም ነው አትመኑት፣ጽንፈኛ ነው፣ግጭት ይቀሰቅሳል ይላል. እሱን ትታችሁ ” ለማ ” በመባል የሚታወቀውን ” ልማታዊውን ” ኢ.ቢ.ሲ እና ፋና ሬዲዮን ተከታተሉ. ታማኝ ምንጭ እነሱ ናቸው እያለ ነው. ፌስ ቡክን ለማፈን ብዙ ሚሊዮን ዶላር አውጥተው መጀመሪያ ከቻይና ቀጥሎም ከጣሊያን ካምፓኒዎች ጋር ሞክረዋል. አሁን ሲጨንቃቸው ” የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ” የሚባል ሊያቋቁሙ ነው እንደሆነ በሪፖርተር ጋዜጣ የታህሳስ 12 እትም ወጥቷል. ወጣቱም በማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት እየታቀፈ ”ለማ ”ን ብቻ እንዲመለከት ታስቧል.
ሕዝብ አስተዋይና የበሰለ ነው. የሚያየውን የሚሰማውን ያውቃል. ያመዛዝናልም. ይህንን ተመላከት ይህንን አትመልከት ማለት ንቀት ነው. የህዝብን ልብ ለማግኘት የአንድ ብሄር የበላይነትን አጥፍቶ ፍትህን እኩልነትን ዲሞክራሲን የሃብት ፍትሃዊነትን ማስፈን እንጂ ማከላከል መፍትሄ አይሆንም. ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ከ60ሽህ የሚበልጡ ሰዎች በአመለካከታቸው ምክንያት ታስረዋል. እነተመስገን ደሳለኝ፣በቀለ ገርባ፣አንዳርጋቸው ጽጌ፣ዶ.ር ፍቅሩ ማሩ…ሌሎችም በፈጠራ ክስ ታስረው በጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው አሉ. ብዙዎች በባህርዳር፣በነቀምት፣በጎንደር ጎዳናዎች ደማቸው መፍሰሱ እውን ነው. አናሳ ጎሳዎቹ ከአቅማቸው በላይ በሃብት አብጠዋል ባለፎቅ አስመጭና ላኪ ባለስልጣን መሆናቸው አይካድም. ይህን እውነት በ ”የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ” ልንደብቀው አንችልም. ህዝቡ አሁንም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ከበፊቱ በበለጠ ሊከታተል መረጃን ሊቀባበል በስፋት ሊጠቀምበት የሚያውቀውን እውነት ሊለጥፍ ይገባል. ረጅም እድሜ ለማህበራዊ ሚዲያ

No comments:

Post a Comment