Wednesday, December 28, 2016

የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ >

የአድዋ ጦርነት፤ የአፍሪቃ ሰብአዌነት፤ ለሰው ልጅ ሕሊናዌነት
[ማሳሰቢያ፡ በዚህ አርዕስት ላይ የምንወያየው የአድዋ ጦርነት ለአፍሪቃዉያን ሰብአዌንትና ለሰው ልጅ ሕሊናዌነት ያደረገዉን መስተዋጽኦ ነው። የአድዋ ጦርነት ወይም የአፂ ሚንልክ ታሪክ እዚህ ሊጻፍ እንደማይቻል ለአንባቢ በቅድሚያ ማሳወቅ ተገቢ ነው።  የአድዋ ጦርነት በውጭ አገር የታሪክ ሊሂቃን በመጠኑ ተጽፏል። ግን ታሪክ በአገሩ ሊቃን ሲጻፍ የተልየ መልክ ይሰጠዋል፤ ይህም ማለት ጸሐፊዉ ከሕብረተሰቡ አካል ስለወጣ ባህሉን፤ ዘየዉን፤ አስተሳሰቡን፤ አመለካከቱን፤  አኗኗሩን፤ በአጠቃላይ ሕሊናዉነቱን በቅጡ ያንጸብርቃል፤ ለምሳሌ እንግሊዝ የአገሩን ታሪክ የውጭ ሰው እንዲነካበት አይፈልግም፤ በዩነበርሲቲም ውስጥ ታሪክ እንዲያጠኑ የሚመለመሉ ተማሪዎች በአጠቃላይ ትምህርታቸው ከፍተኛ ዉጢት ያላቸዉን ተማሪዎች ነው። ከውጭ የመጡ ተማሪዎች የሚነገራቸው የራሳቸዉን ታሪክ እንዲማሩ እንጂ ስለ እንግሊዝ አገር ተምረው የእንግሊዝን ታሪክ እንዲጽፉ አይደረግም።  የእንግሊዝ ታሪክ እነሱ እንደሚሉት  በጣም የተከበረና የተለየ ነው፤ “የታላቁ የእንግሊዝ ታሪክ” ተብሎ በክፍተኛ ደረጃ ይቀመጣል፤ “ታላቋ ብሪታንያ” ትባላለች፤ “ፅሐይ በእንግሊዝ ግዛት አትጠልቅም”” ይላሉ። ይህም ማለት አንድ ሶወስተኛዉን የዓልም ክፍልን በቅኝ ግዛታቸው ስለአደረጉ እንግሊዝ አገር ጀምበር ስትጠልቅ ቅኝ ግዛቷ ላይ ትወጣለች። የሊላዉን አገር ታሪክ በፈለጉት ዓይነት ጽፈው ለቅኝ ተገጆቻቸው ያስተምራሉ፤ ለዚህ ነው “የታሪክ አባቶቻችን” እየተባሉ የሚጠሩት፤ ይህ አይነት አባባል እኛም አገር የተለመደ ነው፤ጥገኝነቱም  የጠበቀ ስለሆነ እነሱ ያሉትና የጻፉት ከአልሆነ  በዚህ አይነት ቢቀርብ  ተቀባይነት አይኖረዉም፤ትልቅ ያለመታደል ነው፤ ለዚህም መረጃ የሚሆነው የሚሰጠው አስተያየት ነው ። እንግዲህ እዚህ ጽሑፍ ላይ የምንመለከተው ምኒልክንና አድዋን በአንድነት አድርገን ነው። ምኒልክ ከአድዋ ተነጥሎ ሲታይ ብዙ በደል እንደሰራና ሕዝብን በኃይል አስገድዶ እንደገዛ “የታሪክ አባቶቻችን” በምንላቸው የተጻፉትን በማየት  “አድዋ የአፍሪቃ ድልና አለኝታ” የሚለዉን እንገድፈዋለን። “የከፋፍለህ ግዛ” የፖለቲካ ስልት ክግንዛቤ ስለአላስገባነው አገር፤ ሰንደቅ ዓላማ፤ አንድነት የሚለዉን ማሰሪያ አንቀጽ ተሰባብሮ እንዳለነበረ ሆኗል፤  ይህንን በተመለከተ በዚህ ጽሑፍ ዉስጥ ያስከተለዉን ጉዳት እንመለከታለን።
ይህንንም “ሁኔታ” የምንመለከተው ከታሪክ ቀንጨብ እያደረግን ነው፤ ለአደዋ ጦርነት ዋና መንስኢ የሆነው በክፍል ሁለት ላይ እነደተጻፈው የ1884-5  አፍሪቃን ለመከፋፈል በተደረገው የበርሊን ጉባኢ ነበር። በዚህ ጉባኢ ላይ ተካፋይ የነበረችው ኢጣልያን በወቅቱ ምንም የቅኝ ግዛት የሊላት አገር ስለነበረችና ግዛቷን በጋሪባልዲ አማካይነት ታላቋን ኢጣልያንን መንግሥት በ1860 ስለአስተባበረች የቅኝ ግዛት ባለቤት መሆን አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ሲሲልና በስተደቡብ የሚገኘዉን ሕዝብ አንድ ስላደረገች በቂ ኃይል ስለአገኘች ነበር። በወቅቱ የነበረው  የኢጣልያንን የቅኝ ግዛት ፍላጞትን እጅግ ክፍ ያደረገው የቢልጅያን ንጉሥ ሊዮፖልድ ነበር፤ አንድ ግለሰብ ከአንድ ትንሽ አገር ተነስቶ ትልቅ የቅኝ ግዛት አፍሪቃ ዉስጥ ሲመሰርት እንዲት ታላቋ ኢጣልያን የቅኝ ግዛት አይኖራትም  በማለትና ከሊሎች አውሮፓውያን አገሮች በመፎካከር ነው።  ሊላው ከፋፍለህ ግዛ [Divide et imperia] የተባለዉን የአውሮፓውያን ዕቅድ ስራ ላይ አውለው በጥንታዌነቷ ታዋቂ የነበረችዉን የሮማን ግዛት መልሶ  በተምሳሊቷ ታላቋን የኢጣሊያን ንጉሠ ነገሥት  መንግሥት ለማቋቋም ነበር። አውሮፓውያኖች የራሳቸዉን ጎሳዎች አስተባብረው አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ዓላማ ፤ በጎሳ ሊከፋፈል የማይችል ሕብረት ከፈጠሩ በኋላ [Divide and conquer”] አፍሪቃን በጎሳ ከፋፍለው ለነሱ ታላቅነት ተገዥ ለማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህን “ሁኔታን” የአፍሪቃ ወገኖች ግንዛቢያችው ዉስጥ ስሊለ በጎሳ መለያየቱን እንደ በጎ ስራ አድርገው ይመለከቱታል፤ የኢትዮጵያ የዘውግ አቀኝቃኞች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለጎሳቸው ተቆርቋሪ ሆነው የሚያካሂዱት የፖለቲካ  ትልቅ ነገር የሰሩ የሰሩ እየመሰላቸው ነው። የፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “ወግ” ከዚህ አያልፍም፤ ፍልስፍናቸዉም “የዘውግ አመሰራረት ስር ነቀል ስለሆነ ሊቀለበስ አይችልም” ነው የሚሉት፤ ይህ የመለስና የኢሳያስ ራዕይ ነው። እንግዲህ በዚህ ውይይታችን የምንመለከተው የአፍሪቃን የጎሳ መለያየትና የአውሮፓን ሕብረት መፍጠር ይሆናል። ውይይታችን መልካም እንዲሆንና ለመማር ጥሩ “ሁኔታ” ለማመቻቸት የምንሰጠው አስተያየት በተሰጠው መልዕክት ላይ እንጂ በመልከተኛው ላይ መሆን የለበትም፤ አንባቢ አስተያየት ለመስጠት ፍጹም የሆነ መብት አለው፤ ውይይቱ  ግን አንባቢው በስጠው  አስተያየት ላይ ከአቶኮረ ዉጢት አልባ ሆነን መማማር አንችልም፤ የወያኔ ዋናው ስራው ተሽቀዳድሞ በመጀመሪያ አፍራሽ  አስተያየት መስጠት ነው። ለዚህ አፍራሽ አስተያየት አንባቢ ቦታ መስጠት የለበትም ፤ ይህ የተባለበት ምክናያት በሁለተኝው ክፍል ላይ የተሰጠዉን በማየትና በርከት ያሉ አንባቢዎች በላኩሉኝ መልእክት መሰረት ነው፤ መልካም ውይይት]።
መቅድም
ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት የአድዋ ጦርነት የተከሰተው ኢትዮጵያና ኢጣልያን በተፈራረሙት ውሎች ምክናያት አይደለም፤ የዉሎቹ ፊርማ ሰበብ ነው እንጂ  ለጦርነቱ ምክናያት አልነበረም ፤ዉል ተፈረመ አልተፈረም ኢጣላያን የግድ ቅኝ ግዛት አፍሪቃ ዉስጥ ማግኝት ስለአለባት ጦርነቱ አይቀርም ነበር፤ ለዚህም በመረጃነት መቅረብ ያለብት  የ1884/85 በርሊን ላይ በተደረገው ጉባኢ ላይ ማን ምን ማግኝት እንዳለበት የተደረገው ስምምነት ነው። ይህ ከተባለ በኋላ ታሪኩ ቅደም ተከተሉን ይዞ ይቀርባል። የሚኒልክና የአድዋ ጦርነት ታሪክ ብዙ ቅድመ “ሁኔታዎች” ስለአሉት በአጭሩ ይጠቀሳሉ፤ እዚህ ላይ አንባቢ ታሪኩን በቅጡ እንዲመለከተው የታሪኩን አቀማመጥ በቅድሚያ ማስረዳት አስፈላጊ ነው። ታሪክ ፈጣሪ አለው፤ ያ ታሪክ ፈጣሪ አስቦበትም ሆነ ሲያስብበት፤ በአጋጣሚም ሆነ በስሊት “ሁኔታው” ሲመቻች የታሪክ ሂደቱ ይጀምራል፤ በሂደቱ እያለ ታሪክ ሊሆን አይችልም፤ መድረሽዉም ምን እንደሆነ ስለማይታወቅ ታሪካዌ ሂደቱን ሳይጨርስ ሊጻፍ አይችልም፤ ታሪክነቱ የሚታወቀው ቢያንስ ከሶወስት ትውልድ በኃሏ ነው። ለምሳሌ ዶሮዋን ተመልከት፤ እንቁሏሏን እንደጣለች ጯጩቶቻ አይፈለፈሉም፤ የሚፈለፈልበትን “ሁኔታ” ታመቻቻለች፤ ፉጡራዌ ሂደትን ተከትላ የፈለፈለችውን  እንቁላል የሚያስፈልገዉን ሙቀት በመስጠት ጯጩቹ  እንዲፈለፈሉ ታደርጋለች፤ ይህ ፉጡራዌ ሂደት ነው፤ አንባቢ በድጋሜ መመልከት ያለብት “ሁኔታን” ነው፤ ዶሮዋ የምትወልደዉን እንቁላል በየግዜው ከተበላባት ጯጩቾቻን የምታገኝበት “ሁኔታ” አይኖርም፤ “ሁኔታ” ወሳኝ ነው። በተጨማሪ አንባቢ በትኩረት ማወቅ ያለበት የታሪኩን  የአጻጻፍ ዘዴ ነው። ሁለት ዓይነት ታሪክ አለ፤ በተለምዶ የሆነ ያልሆነዉን ተጽፎ ታሪክ ሆኖ ሲቀርብ የሚያስክትለው ጥፋት ከፍ ያለ ነው፤ ታሪክ የሕብረተሱቡ ያለበትን “ሁኔታ” የአለፈዉን ስሕተት የሚያበት መስተዋት ስለሆነ ከዚህ ታሪክ ከአልሆነ ታሪክ የሚያገኝው ትምህርት ሳይሆን ጥፋትን ነው። የሁለትኛው  ታሪክ አጻጻፍ በታሪክ ጸሐፊዎች ሲጻፍ ልዩ ቦታ ይኖረዋል፤ የታሪክ ቧለሟዩም ትልቅ ኃላፊነት ስለአለበት የተከሰቱትን “ሁኔታዎች” ከነባር ቅርስ ጋር እያመሳከረ አፈ ታሪኩና ንግርትን እያገለለ ምክናያቶችን እየመረመረ የሕብረተሰቡን ሕሊናዌነት ከነባር “ሁኔታ” ጋር እያገናዘበ በጽሑፍ ይመዘግባል፤ ቅድመ “ሁኔታ” እንዲት እንደተፈጠረና ለሕብረተሰቡ ያስገኘውን ጥቅም ወይም ጉዳት በሂሳብ ተሰልቶ በሚዛን ተመዝኖ ይቀርባል፤  ለዚህ ነው “ታሪክ የሕብረተስብ መስተዋት” ነው የተባለው፤ ደግሞም “ስህተቱን ከታሪክ ያልተማረ ሕበረተሰብ መጨረሽው ጥፋት” ነው የሚባለው። እዚህ ላይ  ከፕሮፌሰር መሳይ ከበደና ከሚስተር  ሬኔ ለፎርት ጋር ትንሽ  ቆይታ ከአደረግን በኋላ ወደ ሚኒልክና አድዋ  ጦርነት እንገባለን፤ ከፕሮፌሰሩ ጋር መወያየት ያስፈለገበት ጉዳይ እሳችውና የዘውግ አቀኝቃኞች ሚኒልክን የሚመለከቱት በተለምዶ የሚነገርዉን አፈ ታሪክና ጥራት በሊለው የዘውግ ፍልስፍናን መሰረት በማድረግ ነው፤ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታን ተወያይተን እስምምነት ላይ የማንደርስበት ምንም ምክናያት አይኖርም፤ ግን ሚስተር ለፎርትን እዚህ ውይይት ላይ ማቆየቱ አግባብ አይደለም፤ ምክናያቱም ጽሑፋቸው ከኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የፖለቲካ “ሁኔታ” ጋር ምንም ግንኙነት ስለሊለው ነው፤ ጽሑፋቸው ምናልባት ለብጎ አድራጊ አገሮች ወይም  ለልማት ገንዘብ አበዳሪ ባንኮችና  [ለዓለም ባንክ] ለአትራፊ ነጋዴዎች  ያለዉን “ሁኔታ” ሊያስረዳ ይችል ይሆናል፤ ስለዚህ እዚህ ላይ  ሚስተር ለፎርትን እንሰናበታቸውና ውይይታችን ከፕሮፌስሩና አክራሪ ብሕሬተሰበኞች ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር ይሆናል፤ በተረጋጋ መንፈስና ቅን በሆነ ልቦና ከተወያየን  በኃሏ በታሪካዌ ሂደት አንድ አገር፤ አንድ ሰንደቅ ዓላማ፤ አንድ በሒር የሚባልበት “ሁኔታ” ሊፈጠር ይችላል፤ የውውይቱን መነሻና መድረሻ  ስለማናውቀው በትዕግስት እንጠብቀው። ከሁሉ አስቀድመን ለዉይይታችን ከታሪክ እየተቀነጠቡ የሚቀርቡትን ታሪካዌ “ሁኔታዎች” የሚመረምር መላ ምት እንመለከታለን፤ የመላ ምቱ መሰረት ቋንቋ ነው፤ ቋንቋው በሚገባ ስለዳበረ “ልብ ወለድ” ወይም “አፈ ታሪክ” ወይም “ንግርት” ወይም እንደ “ተረት” የሚነገሩትን ከመረጃ ጋር የሚቀርቡትን ታሪካዌ ሂደትን ለይቶ ለማየት ያስችላል፤ ለምሳሌ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ እንዲት እንደገባ የሚመረምር በቋንቋ የዳበረ መላ ምት እንመልከት፤
እንግዲህ  አንባቢ እስከ አሁን  ድረስ በአደረገው የውውይት ጉዞ በቂ የሆነ ታሪካዌ ግምገማና “ሁኔታን” መርማሪ [ሐታቲ] መላ ምት ስለ አዳበረ ከዚህ በላይ የተጻፈዉን “ሐተታ” [ምርምር] “ሐትቶ” [መርምሮ]  በዋቢነት የቀረበውን ጽሑፍ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ለመግባቱ መነሻ “ታሪክ” መሆኑንና ያለመሆኑን ሊመረምር [የሐትት] በቂ “ችሎታ” ይኖረዋል ብዮ እገምታለሁ፤ ይህ ግምት ነው፤ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ እዚህ ላይ ዉይይታችን ከፍ ባለ ደረጃ እንዲያድግ በማለት “ሐተተ” የሚለዉን የግዕዝ ቃል ግሥ  እርባታዉን ማሳየት ለአንባቢው ምርምር ይረደዋል፤ እንግዲህ  “ሐተተ” የሚለዉን አርእስት ወስደን የግሡን እርባታ [እርባ ግሥ] እንመልከት፤ “ሐተተ” [መረመረ] “የሐትት” [መረመረ] “ይሕትት” [ይመረምር] “ሐቲቶት” [መመርመር] “ሐታቲ” [የመረመረ] “ሐታቲያን” [የመረመሩ] “ሐታቲት” [የመረመረች]  “ሐታቲያት” [የመረመሩ] “ሕቱት” [የተመረመረ] “ሐታቲ” [መርማሪ] እያለና በገቢር በተግብሮ እያሰረ በአር ዕስት ተከፍሎ በአዕማድ ተጠቅሎ በዕቢይ በንዕስና በደቂቅ አንቀጽ እየገባ “ሁኔታን”  የሚመረምር የግሥ እርባታ ነው። ቋንቋው በሚገባ ዳብሯል፤ አገር ፤ መንግሥት ፤ ሕብረተሰብ  ትምህርት ቤት ፤ ቤኖር ከዚህ የበለጠ “ሁኔታን” መርማሪ መሳሪያ የለም። ከዚህ በላይ የተጻፉቱን “ቅድመ “ሁኔታዎች” አሉ ብለን በመጠኑ ምርምራችንን እንቀጥል፤ ክርስትና ወደኢትዮጵያ ገባ በተባለብት ዓመት [334 ዓ.ም] ነበረ የተባለዉን በዕብይ አንቀጽ እንመዝግባቸው፤  “አገር” ፤ “ወደብ”  ፤ “ቤተመንግሥት” ፤ ቤተ መጻሕፍት” ነበሩ እንበል፤ በአንጻሩ ደግሞ በንዕስ አንቀጽ ደረጃ “ነጋዴ”  “ወጣቶች”  “ሽፍቶች” ነበሩ እንበል፤ እንግዲህ በዓብይና በንዕስ አንቀጽ ያሉትን ስንመረምር “በገቢርና”  “በተገብሮ” የተደረጉትን  ያለምንም ስህተት ማግኝት እንችላለን፤ ኢትዮጵያ የሚባል አገር አለ፤ ወደብ ከአለ የግድ የባሕር ኃይል አለ ማለት ነው፤ በወደቡ ላይ የሚተላለፍ ንግድ ከአለ ፅጥታ አስካባሪ አካል አለ፤ እንግዲህ በዋነኛነት የምናየው “ቤተመንግሥቱንና” ቤተ “መጻሕፍት” ነው፤ እዚህ ላይ ጥያቄው በምን አይነት “ሁኔታ” ነው እነዚህ ሆለት የሶርያን ወጣቶች የቤተመንግሥትና የቤተ “መጻሕፍት” ሃላፊ የሆኑት? በተለይ “መጽሐፍት” ቤቱ የሚነግረን በጽሑፍ የተጻፉ ጽሑፎችን የያዘና ታላቅ የሥነ ጽሑፍን ዕውቀት የተከማቸበት ቦታ መሆኑን ነው፤ ወጣቱ ፍሬሚናጦስ [Frementius] በምን ዕውቀቱ ነው ለዚህ ስራ የተመረጠው? ቋንቋዉን አይችልም ፤ ስለ ቤተ መጻሕፍት ቤትም የሚያቀው ነገር የለም ። በምን “ሁኔታ” ነው ፍሬሚናጦስ [Frumentius] አንድ የባሕር ኃይልና ወደብ ያለው አገር የቤተ መንግሥቱ ዋና አማካሪና ደግሞም የወጣቱ ንጉሥ እንደራሴ ሊሆን የቻለው? ይህንን “ሁኔታ” ሊፈጥር የሚችል ምክናያት አይኖርም፤ በተጨማሪ ለታሪኩ መጀመሪያ እንዲሆን የተሰጠው ቀን 334 ዓ.ም የተባለው ዘመን የፈጠራ እንጂ በዕውነት በዘያ ዘመን አንድ ሃይማኖት ተቀባይነት አግኝቶ  በአንድ ዘመን ወይም ዓመት ግዜ የነበረዉን ቤተ መቅደስ በከመ ቅስፈት ቤተ ክርስቴያን ብሎ ሊለዉጥ አይችልም፤ ስለዚህ በመረጃነት የቀረበው የልብ ወለድ “ታሪክ” እንጂ “ሁኔታ” ፈቅዶ በተግባር የሆነ “ታሪክ” አይድለም። ነባር ቅርስ እያለ ምን አልባት ሳይሆን  አይቀርም በሚል መላ ምት የተጻፈ ታሪክ ነው። እዚህ ላይ ክርስትና መግባቱንና ያለመግባቱን ሳይሆን በምን አይነት ሁኔታ እንደገባ ማወቅ አስፈላጊ ነው ምክናያቱም የሕብረተሰቡ ታሪክ ስለሆነ። መነሻ ፤ መንደርደሪያ፤ መድረሻ የሊለው ታሪክ ሊሆን አይችልም፤ የሕበረተስቡንም ሕሊናዉነት ምን እንደሆነ አይገልጽም፤ ከክርስትና በፊት ለብዙ ዘመናት መቅደስ ያለው አገር፤ ሥነ  ጽሑፉ ዳብሮ በመጻሕፍት ቤት የተለያዩ ጽሑፎችን ያከማቸ ሕብረተሰብ በአንድ ሶርያን ወጣት አማካይነት ክርስትናን ተቀበለ ለማለት ያስቸግራል [ሙሉ ታሪኩን ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ይመልክቱ–የጥንታዌት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አቅጭር ታሪክና ስነ ሥርዓት፤ ክፍል አራት  December 19, 2016]
እዚህ ላይ ሰፋ ያለ  መግለጫ የተሰጠበት ምክናያት የኢትዮጵያ ታሪክ “ተረት” ነው፤ ከመቶ ዓመት በፊት ኢትዮጳያ የምትባል አገር የለችም ነበር፤ “ሚኒልክ በኃይል የደቡቡንና የሰሚኑን ሕዝብ ቀጥቅጦ”  የፈጠራት አገር ነች በማለት ንግርትና አፈ ታሪክ እንደ ታሪክ ሆኖ የሚጻፍበትና  የሚነገርባት አገር ስለ ሆነች ነው፤ በእንደዚህ አይነት “ሁኔታ” ላይ ሆኖ ታሪክን ከነባር ቅርስ ጋር እያገናዘቡ ለመጻፍ አስቸጋሪም ቢሆንም ጢኔኛ ሆኖ ለሚወለደው ትውልድ ማሳወቅ ታሪካዌ ግዲታ ነው፤ የዘውግ አቀኝቃኞችና ጥገኛነትን አክራሪዎች የታሪካችንን መላ ምት የተለየ መለኪያ ያስፈልገዋል፤ የታሪክ አባቶቻችን አላሉትም” እያሉ እንድሚያዋዱቁት አውቀን ከባሕላችን በመነጨውና በቅጡ በዳበረው ቋንቋችን ለልጅ ልጆቻችን የታሪክ ቅርሳችንን እናስቀምጣለን። እንግዲህ የመላ ምታችንን ብቁነት ከአስተካክልን በኃላ የምኒልክንና የአድዋን ቅድመ “ሁኔታውች”  ከታሪክዌ ሂደት ላይ ቀንጠብ እየተደረገ ይቀርባል።
ምኒልክና አድዋ የቅድመ “ሁኔታዎች” ዉጢት ናቸው። የሰሎሞናዌ ሥረወ መንግሥት በዛጓው ቢተ አገዛዝ ከተወሰደ ከመቶ ዓመት በኃላ በይኩኖ አምላክ በ1270 ዓ ም  ተመልሶ ሲመሰረት የኢትዮጵያ ግዛት ከአትበራ እስክ ፑንት መሆኑን ነባር ቅርስ ይመስክራል፤ በአፈ ታሪክ የሚነገርለት ፕሬሰተር ጆን [Prester John] የሚባል ንጉሥ እንደ ነበር በሞላ አውሮፓ ይነገር ነበር፤ ነገር ግን ይህ ንጉሥ  የኢትዮጵያ ወይስ የሕንድ  ይሁን በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም፤ ንግርት ነው፤ ሆኖም ይኩኖ አምላክ በ1270 እስከ 1277 በአለው ግዜ ዉስጥ ከክርስቲያን ተጋዲያዎች [Crusaders] ጋር ለመገናኝት ሞክሮ እንደነበር ይነገራል፤ ከንግርት በላይ ምንም ተጨባጭ ቅርስ የለም። ነገር ግን አምደ ጽዮን [1314—44] ግዛቱን እስከ ቀይ ባሕር አስፋፍቶ በቁጡጡሩ ስር እንደነበር የሚያስረዳን በቂ መረጃው ልጁ ሰይፈ አዕራድ [1344—77] ከክርስቲያን ተጋዳዮች ግንኙነት አድርጎ ኢትዮጵያዊያኖችን በኢየሩሳሊም  በቂ ድጋፍ ለመስጠት አስፍሮ እንደነበርና ይዞታዉም በኢትዮጵያ ቅርስነት እስከ አሁን ድረስ እንዳለ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ግዛትም ከንጉሥ ዳዌት እስከ ዘርዓ ያዕቆብ ድረስ ተስፋፍቶ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል፤ ነገር ግን በልብነድንግል ዘመነ መንግሥት [1508-40] የኢትዮጵያ ግዛት ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሂደ፤ ለዚህም ዋነኛ ምክናያቱ በዳዌትና  በልጁ ዘርዓ ያዕቆብ ግዜ የአንድ ሰንበት የሁለት ሰንበት ጥያቄ በቤተ ክርስቲያኑ ዉስጥ ለብዙ ግዜ ሲያከራክር ስለነበረና ደግሞም የኢትዮጵያ መንግሥት ከክርስታያን ተጋዳዮች ጋር መተባበርና በኢየሩሳሌም ዉስጥ ድጋፍ ሰጭ ኃይል ማስቀመጥ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ የእስልምና እምነት አስፋፌዎች አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ስለ አገኝት የኢትዮጵያን ግዛት ቀይ ባሕርን፤ ኢርትራን፤ ጂቡቲን፤ በአጠቃላይ የሕንድ ውቃያኖስ አዋሳኝ የሆኑትን ወደቦች በመያዝ እስልምና ወደ መሐል አገር እንዲገባ በማድረግ ለግራኝ መሐመድ መነሳት ትልቁን መስትዋጽኦ አድርገዋል። እዚህ ላይ ለአንባቢ ሳይጠቀስ የማይታለፍ ታሪክ ቢኖር ለእስልምና ሃይማይኖት መቋቋም ኢትዮጵያ ትልቁን ሚና መጫወቷን ነው፤ በመጀመሪያ ነቢዩ መሐመድ በሕጻንነቱ ወላጆቹ ስለሞቱ እንደ እናት ሆና ያሰደገችው ባሕርዋ የምትባል ሲት ነበረች፤ ታሪኩ እንዲህ ነው፤ በዘመኑ የአረብያን ግዛት ኢትዮጵያ ታስተዳድር ነበር፤ ነገር ግን የባሕር ወደቧና የጦር ኃይሏ በሮማን መንግሥት ኃይል እየቀነሰ ስለመጣ የግድ የአረብን ግዛት መተው ስለነበረባት ኢትዮጵያውታ ባሕርዋ ጥቂት ከቀሩት  ኢትዮጵያዉያን አንዷ ነበረች፤ በዚህ አጋጣሚ የስድስት ዓመቱን ወጣት እንደ እናት ሆና አሳድገዋለች፤ በኃሏም ለአቅመ አዳም ደርሶ ነብይ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ተደርጎለታል፤ ይህውም የየጎሳው ባላባቶች ነቢዩን በማሳደድ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት እምነቱን በነጻነት እንዲከተል አድርጋለች፤ ነቢዩም የእስልምና ሃይማኖቱን ሲመሰርት በተነሳው ጦርነት ምክናያት በመጀምሪያ እስልምና የተቀበሉትን ለደሕንነታቸው ብሎ የላካቸው ወድ ኢትዮጵያ ነው፤ ይህ አፈ ታሪክም ንግርትም አይደል፤ እውነተኛ ታሪክ ነው፤ ለዚህም በመረጃነት ሊቀርብ የሚገባው ነቢዩ ለተከታዮቹ ኢትዮጵያ ባለውለታና ታላቅ ታሪካዌ አገር ስለሆነችና ለሰው ልጅ ሁሉ ተምሳሌት ነችና እንድትነኳት በሎ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለስምንት መቶ ዓመት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ኢትዮጵያን አልነኩም፤ ይህንን የማያውቅ የአስልምና ሃይማኖት አባት አይኖርም።
እንግዲህ አንባቢ ይህ ውይይት በተሟላ ታሪክ  ላይ ሳይሆን ቀንጠብ እየተደረገ የቀረበ  የዘውግ አቀኝቃኞችንና የጽንፈኛ ብሒረተሰበኞችን ወግ ለማስተካከል  መሆኑን ማወቅ ግዲታ ነው፤ የዘውግ አቀኝቃኙን ፕሮፌሰርና አክራሪ ብሒረተሰቦኞችን አስተካክላለሁ ማለት ዘበት ነው፤ ከዚያም አልፎ በሰማይ ላይ እንዳለችው ላሟን መሆን ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን አንድ ሕብረተሰብ እንደ ተለያየ  ሕብረተሰበዎች አድርገው ስለበከሉት ሕዝብ ይህንን አፈ ታሪክና ተረት በታሪክ አምድ አድርገን  ለማስተዋወቅና ለማስተካከል ነው፤ ሰሚና አንባቢ ከተገኝ የሕብረተሰባችንን አንድ ነት ለማዳን የተደረገ ሙክራ ነው። ደግሞም ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው ምን ይታወቃል በውይይት የማይፈታ ነገር የለም፤ ምናልባት ተቀራርበን  ታሪካችን በዉጭ ኃይል እንደተጻፈው ሳይሆን እውነተኛዉን ታሪካችንን መሰረት አድርገን ቅሪታችንን  እንፈታው ይሆናል፤ እዚህ  ላይ ትልቁን ጥንቃቄን ማደረግ ያለብን አሁን ባለው ሥርዓት ተጠቃሚዎችና ጥገኝነትን በሚያጠብቁ  ልሂቃን እንዳንወናበድ ነው።  በምንባቡ እንዳንሰላች የሶወሰትኛው ክፍል እዚህ ላይ ይቆማል። ከላይ እንደተጠቀሰው የሚስተር ሬኒ ለፎርት ወግ እዚህ ላይ ስልተጠናቀቀ የአራተኝው ክፍል አርዕስት የሚሆነው “የመሳይ ከበደና የጽንፈኛ ብሒረተሰበኞች ወግ”  ይሆናል። በአራተኛው ክፍል የምንወያይበት አርስዕስት “የቀይ ባሕር መወሰድ፤ የእስልምና ሃይማኖት መስፋፋት፤ የግራኝ መሐመድ መነሳት፤ የኢትዮጵያ ግዛት መፈራረስና የልብነ ድንግል መንግሥት መዳከም፤ የዘመን መሳፍንት ዘመን፤ የሚኒልክ ዘመነ መንግሥት ይሆናል። በተጨማሪ ብዙ ክፍሎች ስለሚቀሩ አስተያየቶች ቢቆዩ ይመረጣል፤ ሆኖም እዚህ በቀረበው ላይ መስተካከል አለበት የሚሉት ከአለ ለመማር ስለሆነ ይጠቅማል ብዮ እገምታለሁ። ትምህርታዌ ውይይት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

No comments:

Post a Comment