Tuesday, December 13, 2016

የለውጥ ጉዞው ዙሪያው በጠላት መከበቡን መንቃት ያስፈልጋል።


በፍቅር በአንድነት በሕዝቦች እኩልነት እስካላመንን ድረስ ዙሪያህ የተከበበው በጠላቶችህ እንደሆነ አትዘንጋ።
ኢትዮጵያ ዜጎችዋ የርስበርስ ትምምናቸው ከመጡበት የዘመናት የመተጋገዝ ያኗኗር እሴታቸው ክፉኛ እየተንሸራተቱ እንደመጡ የኬንያ ምሁራን ጥናታቸውን ዋቢ ኣድርገው እየተናገር ነው። እንግዲህ ነገ ለሚወለደው ችግር ከወያኔ ቀጥሎ የሚወነጀለው ማን ነው???  በፍቅር በአንድነት በሕዝቦች እኩልነት እስካላመንን ድረስ ዙሪያህ የተከበበው በጠላቶችህ እንደሆነ አትዘንጋ።የለውጥ ጉዞው ዙሪያው በጠላት መከበቡን መንቃት ያስፈልጋል። ካልንቃህ ስትሳድብ ዋል።እውነት መንገዷን ስታለች።ፍቅር ወደ ገደል እየተምዘገዘገ ነው። አንድነት እየተሰነጣጠቀ እየተወሻሹ መኖር ልምድ ሆኗል።ተስፋ በውሸታሞች እጅ እየተዘራች ነው።
– ሁሉም የራሱን ጭብጨባ እንድታጨበጭብለት ይፈልጋል።ካልሆነ ስድብ ያዥጎደጉዳል።
– ሁሉም ራሱ የሚያዋርዳችውን ሰዎች አብረህ እንድታዋርድለት ይፈልጋል።ካልሆነ ኣንተ ትዋረድበታለህ።
– ሁሉም በራስ መተማመኑን ሸርሽሮ ለፕሮፓጋንዳ እንደሚያቶሶቱስ አንተን እንድታቶስቱስ ይፌልጋል።ካልሆነ አሉባልታውን ሲነዛ ይክርማል።
– ሁሉም ምክንያታዊና ሃሳብን በሃሳብ የማሸንፍ ስልት ስለማይክትል የተጻፈ ሁሉ ላይ ሲሞጣሞጥ ይውላል።ካልሆነ የስትረስ በሽታው ያሻቅባል።
– ሁሉም የምትጽፈውን ያጣጥላል ራሱ ይመጣብህና ሲለማመጥህ ከርሞ አብረኽ ው እንድትንሸራታት ይፈልጋል። ካልሆነ ያላዝንብሃል።
– ሁሉም ትላንትና በደርግ እና በሃይሌስላሴ እሱና ቤቴሰቦቹ ተጠቃሚ ስለነበሩ ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከነግብረ አበሮቹ ሃገር ሲበዘብዝ ሁሉም ሌባና አምባገነን መሆናቸውን ስትነግረው ሊበላህ ይደርሳል።ካልሆነም ያኮርፋል።
– ሁሉም ስለመቻቻልና ስለመከባበር ስትነግረው እርስ በርሱ ይወነጃጀላል ይፍራርጃል። ከኛ በላይ አዋቂ ላሳር ይልሃል ካልሆነ ይዘረጥጥሃል።

No comments:

Post a Comment