Sunday, December 25, 2016

ወ/ሮ ርስቴ ተስፋዬ የአማራ ተጋድሎን አስመልክታ በቅርቡ የሰጠቸው ሊደመጥ የሚገባ ቃለ ምልልስ


ወ/ሮ ርስቴ ተስፋዬ በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ሌሎችም ቦታዎች በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስመልክታ በግንቦት ሰባት የተነዛውን የሐሰት መረጃ ነጥብ በነጥብ እየተነተነች ምላሽ ሰጥታበታለች። ከዚህም በተጨማሪ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ትግል በወያኔ የተደፈጠጠን የአማራ ማንነት መልሶ ተገቢው ቦታ ላይ ለማቆምና ከሌሎች ወገኖች ጋር በህብረት ዲምክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት መሆኑን በስፋት መረጃዎችን እያጣቀሰች አብራርታለች።
  • ጥያቄው አማራነት ነው፣ መነሻውም አማራነት ነው፣ መድረሻውም አማራነት ነው
  • አማራ ጠላቱ ብዙ ነው፤ ከጠነከረ ግን ሁሉንም ያሸንፋቸዋል
  • ኮሽ ባላ ቁጥር አለን የሚሉት ግንቦት ሰባቶች ናቸው፣ ኮሽታነት ሳይሆን ቆራጥነት ያስፈልጋል
  • ሻቢያና ወያኔ አንድ ናቸው ይቀራረባሉም
  • አማራው በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት እንዲሁም በደኖ፣በአርባ ጉጉ፣በጉራ ፈርዳ፣ በመተከልና በሌሎች ቦታዎች ከሌሎች ተነጥሎ የተጨፈጨፈውና እትብቱ ከተቀበረበት ምድር የተነቀለው በአማራነቱና በማንነቱ ምክንያት ብቻ ነው
  • ግንቦት ሰባት የአማራውን ጥያቄ “የወረዳ ጥያቄ” ይላሉ። እንዴት ነው ከወረዳ ሳይነሱና ወረዳ ሳይዙ አገር መቆጣጠር የሚችሉት?
  • ግንቦት 7 ኪስ አውላቂ ድርጅት ነው

No comments:

Post a Comment