Monday, December 12, 2016

የእለቱ የሰሜን ጎንደር ግንባር ዳሰሳ = ይፋት ዳር ዳር እያለ ነው


የእለቱ የሰሜን ጎንደር ግንባር ዳሰሳ
ይፋት ዳር ዳር እያለ ነው?
ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓ.ም.
፨የወያኔ ሃይል ወደ ቆላማው ወገራ በሳንጃ በኩል ቆርጠዉ ሊሄዱ ሲሉ ቆላ መረባ ላይ ህዝቡ ተኩስ ገጥሞ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሰባቸው የወያኔ ሃይል ወደ መጡበት እግሬ አውጭኝ ብለው ተመልሰዋል።
፨ዛሬ ጥዋት ዳባት ከተማ አረደጃን ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ በሰሞኑ ለሞቱት የወያኔ ልዩ ሀይል ቤተሰቦች መርዶ አረዷቸዉ እለቅሶ በለቅሶ ሁኗል።የሟች ቤተሰቦች ህዝባችን መካከል ፍጅት እየፈፀመ ስለሆነ ደማችንን የምንመልሰዉ ከመንግስት አካል ነዉ ብለዋል።
፨ከሰኞ ጀምሮ የዳባት ወረዳ የወያኔ ቅጥረኛ ካቢኔዎች አብረዉ ከመከላከያ ጋር ቆላ እንዲወርዱ ትእዛዝ ተሰጠ። በፍርሃት ተውጠዋል።
፨አርማጭሆ ብዙ የወያኔ ልዩ ሀይል ተገድለዋል ስለዚህ የሚመራው አካል ስሌለለ ለጊዜው ዝምታን መርጠዋል።
፨ሰሞኑን የተቀሰቀሰውን የዛሪማ እና አድርቃይ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመግታት ወያኔ የተለያዩ በሮች ላይ ፍተሻ ተጀምሯል። ጥንቃቄ ይደረግ።
፨ሰሜን ሸዋ ይፋት አካባቢ እንደሰማሁት ወያኔ ሰብስቦ ሚኒሻውን ሁሉ አበል እየሰጠ ታጠቁ ሲላቸው ማንን ልንገድልበት ነው የሚል መልስ እንደሰጡ ሰምቻለሁ እና ይፋት ላይ ትንሽ ኮሽታ ነው የሚፈልጉት…ከቦታው የተላከ መልእክት…
ሙሉነህ ዮሃንስ

No comments:

Post a Comment